Get Mystery Box with random crypto!

ጥቁሩ ነጥብ ከእለታት አንድ ቀን አንድ ብልህ ሰው ተማሪዎቹን ሰብስቦ አንድ ትንሽ ጥቁር ነጥብ | የህይወት ቁልፍ🔐🔑

ጥቁሩ ነጥብ

ከእለታት አንድ ቀን አንድ ብልህ ሰው ተማሪዎቹን ሰብስቦ አንድ ትንሽ ጥቁር ነጥብ እየሳለ ግልጽ የሆነ ትልቅ ወረቀት አሳያቸው። እንዲህ ሲልም ጠየቃቸው። -'' ምን ይታያችኋል ''? ሁሉም በአንድ ላይ ''ጥቁር ነጥብ'' ብለው መለሱ። እርግጥ ነው ጥቁር ነጥብ ይታይ ነበር በወረቀቱ ላይ ነገር ግን ከጠቢቡ ሰውዬ እይታ ግን መልሱ የተሳሳተ ነበር።

ለምን አትሉም??

ጠቢቡ ሰው እንዲህ አለ። - ያንን ነጭ ወረቀት ማየት አትችሉም?አላቸው - በጣም ግዙፍ ነው, ከዚያ ጥቁር ነጥብ እጅግ ይበልጣል አላቸው! ከዛን ሁሉም ጠቢቡ ሰውዬ ሊያስተምራቸው የፈለገውን ሀሳብ በመረዳት ልክ እንዳልሆኑ አወቁ።

ማጠቃለያ
: ይህ በእኛ ህይወት ውስጥም ተመሳሳይ ነው። አብዛኞቻችን በሰዎች ላይ የምናየው የመጀመሪያው ነገር መጥፎ ነገር ሊሆን ይችላል ፤ምንም እንኳን ብዙ ጥሩ ነገሮች ቢኖሩም ጥቂት ሰዎች ብቻ ያንን "ነጩን ወረቀት" ወዲያውኑ ያዩታል። እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው እ ለማንኛውም ዕይታችንን እናስተካክል፤ ከትንሹ ነጥብ ይልቅ ትልቁን ነጭ ወረቀት ማየት ይሁንልን። Just Be Postive , it doesn't cost you!!

ናol ነኝ
ሰናይ ሰንበት

የህይወት ቁልፍን.. ይቀላቀሉ

#share
Join: @yehiywetqulfoch
Join: @yehiywetqulfoch