አውቃለሁ ∞∞∞∞∞∞∞∞ #በረከትዘውዱ መንገድ ስትሄጂ ወይም ደሞ ቆመሽ ፣ ወይ ስራ ላይ ሆነሽ በነገር ተጠምደሽ ፣ ሁሌም ይሰማኛል እንደማላገኝሽ ። ህዋ ላይ ሳትወጪ ፣ ባህርን ሳትረግጪ ፣ ደመና ሳትቀዝፊ ፣ ቤርሙዳን ሳታልፊ ፣ እዚው ቅርቤ ሆነሽ ፣ ብቻ ይሰማኛል እንደማላገኝሽ ። ልቤ ናፍቆት አጥሮት ፣ አይኔ እምባ አምልጦት ፣ ቀልቤን ሀሳብ ውጦት ፣ ይሰማኛል ብሶት ፣ ያንቺን አለም ሌላ አድርጌ እስላለሁ ፣ ብከንፍ ላልደርስብሽ ብቻ እራመዳለሁ ፣ እንደማላገኝሽ እውነት ግን አውቃለሁ ። አለመድረሴን ባውቅ መንገድ አያስቀረኝ ፣ እንዴት እቀራለሁ ፍቅር እያከነፈኝ ፣ ስራመድ ስዳክር አቅም እያጠረኝ ፣ ያለመቅረት መንገድ የት ይሆን ሚያደርሰኝ ፣ ልቤ እያወቀው እንደማላገኝሽ ፣ ታድያ ለምን ይሆን የማፈላልግሽ ። @yegtm_hywet @yegtm_hywet 389 views#بروتزجودو, 05:35