Get Mystery Box with random crypto!

አደራ ሚስጥር ነው (ሀምዲ ) አደራ ሚስጥር ነው አሁን ምነግርሽን አትንገሪ ለ ሰው ልቤ አን | የግጥም ቃላቶች ✍

አደራ ሚስጥር ነው (ሀምዲ )

አደራ ሚስጥር ነው
አሁን ምነግርሽን አትንገሪ ለ ሰው
ልቤ አንቺን ለመርሳት
ስምሽን ለመዘንጋት አቅም እንዳነሰው

ከሌላ ሰው ጋራ በያዝሽው ቀጠሮ ቀድሜ እንደምገኝ
ጠ ሽ.... ጠ ሽ
የሚል ምላሳም ስሊፐር በሰማሁኝ ቁጥር መምጣትሽን የምመኝ

ሴት ማስቲካ ነፍታ ባፈነዳች ቅፅበት አንቺ እንደ መሰልሽኝ
የ ቀኑ ሳያንስሽ በ ህልም ኮርኩረሽ ለብቻ እንዳሳቅሽኝ
..
እንዲ እንዲ መሆኔን
አደራ አትንገሪ ሕዝብ አያላግጥብኝ
አንቺ ግን መብትሽ ነው እንዳሻሽ ሳቂብኝ

ሳቂብኝ የኔ ዓለም....
ከዚህ ጣርያ በላይ አሽካክተሽ እንደ ጉድ
እረ ወዴት ልሽሽ....
ይሄው ደግሞ ታየ ያ ስስታም ስርጉድ

አካሌ ወኔ አጣ....
አንቺን ሊረሳበት የቋጠረው ሃሞት በ ድንገት ፈሰሰው
ወጣችልኝ ብዬ ዋሽቻለሁ እና
ይህንን ሚስጥሬን አደራ አደራ አትንገሪ ለ ሰው

@Ham_Di