Get Mystery Box with random crypto!

​​ መልካሙ ዶክተር ┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉ የመጨረሻ ክፍል ፍቅር ምነው ደከምክ እ | የ ፍቅር ቃል ♡ⓛⓞⓥⓔ♡

​​ መልካሙ ዶክተር
┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉
የመጨረሻ ክፍል


ፍቅር ምነው ደከምክ እንዴ አልከት.... መልስ የለም ፍቅር እናውራ እኔ እንደዚህ አይነት ቀልድ አልወድም አልኩት መልስ የለም... በድንጋጤ ጩኸት ለቀኩት... የሰፈር ሰዎች ሁሉ መምጣት ጀመሩ... ቀድሞ የመጡ ወንዶች እኔን ከእዩኤል አጠገብ አንስተው እነሱ ምን እንደሆነ ማድረግ ጀመሩ... ተውኝ እዩኤል ምንም አልሆነም ብዬ ማልቀስ ጀመርኩኝ አንዲት እናት ልጄ አሁን እዩኤል አልፏል ከእንግዲህ ተመልሶ መምጣት አይችልም ጠንከር በይ አሉኝ እራሴን ሰትኩኝ... ከዛ በኋላ የሆነውን ነገር ብዙም ማስታወስ አልችልም፣ ብቻ ምንም ስሜት የሌላኝ ኦና ሆንኩኝ ከአይኔ እምባ ይወርዳል አፌ ግን በዝምታ ተወጠ ትላንት በህመም ጊዜ በዶ የነበረው ቤት በሞቱ ቀን ሞላ ትላንት በህመሙ ጊዜ ቤት ውስጥ በሩን ዘግቶ ይኖር የነበረ ሰው ሁሉ ዛሬ በሞቱ ቀን መጥቶ ስራ መስራት ማልቀስ ጀመረ.... በህይወት እያለ ዞር ብሎ እንኩዋን አይቶ የማያውቁ ሰዎች ዛሬ ለሞተ ስጋው ይሁን ወደ አምላኩ ለሄደው ነብሱ እኔ አላውቅም ብቻ ሽር ጉድ ይላሉ ይሄ ባህል ግን ምን አለ ብለወጥ? ለነገሩ ይሄ ባህል ሳይሆን እርግማን ነው የሞተውን ሰው መቅበሩ ጥሩ ነገር ቢሆንም ከመቅበር ይልቅ ግን በህይወት እያለ መርዳት የተሸላ ነገር ነው። አበድኩኝ ወዲህ ወዲያ አልኩኝ... የኔ እምባ የኔ እብደት ግን አንዴ ለሄደው ሰው ምንም እርዳታ መስጠት አልቻለም እዩኤል ልቤን ተስፋዬን ሁሉንም ነገሬን ይዘው ማንም ወደ ማይቀርበት መቃብር ወረደ። እኔም ትዝታውን ፍቅሩን አደራውን ይዤ ብቻዬን ቀረሁ... ህይወት አንደወዛ ልክ እንደ ቀልድ በቀላሉ እንደዚህ መጨረሻውን አገኝቶ ይሄዳል ብሎ ማን አስቦ ያውቃል? ሁሉም በሀብት ላይ ሀብት በጥላቻ ላይ ጥላቻ ለመጨመር እንቅልፉን ትቶ ቀን ማታ ሳይል ይሮጣል እንጂ! ማን ጥላቻን በፍቅር ለማለውጥ ሮጦ ያውቃል? ለቅም በቀል ሲል እረፍት አጥቶ ይኖራል... ,ህይወት ግን እንደዚህ ናት በጣም በጣም አጭር! ሞት የሚባል ነገር አለ ከብዙ ህልም ከብዙ እቅድ ከብዙ ምቾት በአንዴ መጥቶ ሁሉንም ትተህ ና እንሂድ የሚል ጀግና ማንም እንቢ ማለት አይችልም ታድያ ለምንድነው ጥላቻው? ታድያ የምንድነው ጀግንነቱ? ታድያ የትኛው ነው ትልቁ ዘር? ታድያ የትኛው ነው የአንተ ጉልበት? ፍቅር ማሸነፍ የልቻለውን ሞት በዚህች ምድር ላይ ምንም ማሸነፍ አይችልም። ከአንድ ስምንት የሰዎች ጋጋታ በኋላ እኔ እና ሁለቱ እናቶቼ ብቻ ቀረን... ሰው ሁሉ አንድ በአንድ እያለ ከቤቱ ወጥቶ አለቀ። ህይወት አስጣለኝ መኖር ሰለቸኝ ለከ ተስፋ ከሌላት ህይወት መኖርን እንደዚህ ስልችት ትላለች እንደዚህ እያልኩ አንድ ወር ደረስኩኝ... ከአንድ ወር በኋላ ቆይ በምድር ላይ የኔ የሚለውን ነገሮች አጥቼ መኖር ምን የምሉት ነገር ነው የሚል ሃሳብ በተደጋጋሚ መምጣት ጀመረ እራሴን ለመጥፈት እቅድ ስያወጣ በድንገት አእምሮዬ ላይ የእዩኤል አደራው እና የደብዳቤው ነገር ትዝ አለኝ በፍጥነት ደብዳቤው ያስቀመጥኩበት ቦታ ሄድኩኝ
እራሴን ለማጥፋት እቅድ ሳወጣ በአጋጣሚ እዩኤል የሰጠኝ የአደራው ነገር እና የደብዳቤው ነገር ትዝ አለኝ... በፍጥነት ደብዳቤውን ካስቀመጥኩበት ቦታ አውጥቼ ስከፍት ሁለት ወረቀቶች በውስጡ አሉ... ቶሎ ብዬ አንዱን ከፍቼ ማንበብ ጀመርኩኝ ደብዳቤው እንዲህ ይላል፦
ደብዳቤውን ከማንበባችሁ በፊት እስቲ ቻናሉን አጋሩ አቤት እናንተ የሚያስከፍል ይመስል ትትስታላችሁ ለማነኛውም ደብዳቤው እንዲህ ይላል
በጣም የምወድህ ምርጥ ጓደኛዬ እንዴት ነህ? እግዚአብሔር ይመስገን እኔ ደህና ነኝ፣ በእርግጥ ስለ አንተ ማንነት ብዙም አላውቅም ግን በዚህች አብረን በሆንበት ጥቂት ወራቶች ውስጥ ከአንተ ብዙ ነገሮችን ተምሬያለሁ ግን አሁን ማውራት የፈለኩት ስለ መልካምነትህ አይደለም፣ ከአንተ ልርቅ መሆኔን ልነግርክ ነው እንጂ! በርግጥ አንተ ምናልባት አንድም ቀን ከእኔ ይርቃል ብለህ ላታስብ ትችላለህ ግን እኔም ግድ ሆኖብኝ ነው ለመራቅ የወሰንኩት ምክንያቱም በአንተ እና በሀረግ ፍቅር መሃል መግባት አልፈልግም ዝም ብዬ እንዳልቀመጥ ደግሞ አቅም አጣሁ፣ ሀረግን በጣም እወዳታለሁ ለሷ ግን ተመንገር የለብህም አንተም እንድታውቅ የፈለኩት ልርቅህ ስለሆነ ምክንያቱን እንድታውቅ ብዬ ነው ይላል ምን? ዶክተር ከእኔ ፍቅር? ቀልድ መሆን አለበት ብዬ በፍጥነት ሁለተኛውን ወረቀት ስከፍት.. እንዲህ ይላል፦ ሁሌም የምወድሽ በልቤ ዙፋን ላይ ለዘላለም ተቀምጠሽ የምትኖሪ የመጀመርያዬም የመጨረሻዬም የልቤ ንግስት የምወድሽ የማከብርሽ ሀረግ ሰላም ላንቺ ይሁን... አንቺን ለመግለጽ ብዙ ቃላቶች አይበቁም እነዚህ ጥቂት ወራቶች አንቺ ከጎኔ ባትሆኝ እንዴት ሆነው ያልቁ ነበረ ብዬ ሁሌም አስብ ነበረ አንቺ ከጎኔ ስለነበርሽ ግን ይሄው የመጨረሻው ቀን ደረሰ የኔ ፍቅር በውስጤ ይዤ ለመሞት ያሰብኩ አንድ ምስጢር ነበረ አሁን ግን ላንቺ ጠቃሚ ስለሆነ ለመንገር ወሰንኩኝ እኔ የካንሰር በሽተኛ ብቻ አይደለሁም ትዝ ይልሻል? የዚያን ቀን በጣም ስሜት ውስጥ ከገባን በኋላ ምክንያት ፈጥሬ ጥዬሽ የሄድኩትን ቀን? የዚያን ቀን ጥዬሽ የሄድኩት ስሜት ስለሌለኝ ሳይሆን በደሜ ውስጥ ኤች አይ ሺ ኤድስ ስለነበረብኝ ነው። ደሜ ውስጥ እሱን ተሸክሜ እስከዛሬ አብሬሽ በመኖሬ ራስ ወዳድ ነኝ አይደል? የኔ ፍቅር እውነታውን ያወኩት ፍቅር ውስጥ ከገባን በኋላ ነበረ.. ከዛም ምክንያት ፈጥሬ ካንቺ ለመራቅ አሰብኩኝ በዚህ መሃል ግን ዶክተሩ ይሄን ደብዳቤ ሰጠኝ እኔም ዶክተሩ መልካም ሰው ስለሆነ የሱን መልካምነት በእኔ ምክንያት አንቺም እንድታውቂ ብዬ ዝም አልኩኝ እውነታው ይሄ ነው ፈጣሪ ሁሉንም ነገር ቀድሞውኑ ያውቃል እኔ የምሞተው ብኖርም ተስፋ ስለሌለኝ ነው እራስሽን ጠብቂ የእናቴን ነገር ደግሞ አደራ ሁሌም የምወድሽ የሁልጊዜ አፍቃሪሽ እዬኤል ይላል። ከአይኔ እምባ መውረድ ጀመረ... ለካ ሰውን አውቃለሁ ማለት ውሸት ነው የሰውን ልብ የሚያውቀው አንድ ፈጣሪ ብቻ ነው። ግን እሱንም መውቀስ አልችልም ምክንያቱም ለኔ ብሎ ያደረገው ነገር ነው የሚወዱትን አጥቶ መኖር በጣም ከባድ ቢሆንም ህይወት ግን ትቀጥላለች እሱ እንዳለውም ሁሉም ነገር ያለ ምክንያት አይሆንም!! እዩኤል ከሞተ ከሁለት ዓመት በኋላ ከዶክተሩ ጋር በፍቅር ማሳለፍ ጀመረን እኔም ቃሉን ጠብቄ ደስተኛ ሆኜ እናቱንም አቅሜ በቻለው መጠን ሁሉ እየረዳው እየኖርኩኝ ነው እናም የምትወዱትን ሰው በአጋጣሚ ብታጡ እንኩዋን ህልሙን ለመኖር ሞክሩ እንጂ ራሳችሁን ወደ መጥፎ ሱስ ወይንም እብደት አስገብታችሁ ነብሱን እረፍት አትንሱት እያልኩ ታሪኬን እዚሁ ልቋጭ።

ከጅማሬ እስከ ፍጻሜ አብራችሁኝ ለነበራችሁ ምስጋናዬ ከልብ ነው በሌላ ታሪክ እስክንገናኝ መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ !!" ሰሊና(የብዕር ስም )

​​​​​​​​╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝

ሀሳብ በግል ለመስጠት @dkeya
• ₊° ✧︡ ˗ ˏ ˋ ♡ ˎˊ ˗ »»— ★ ——

ለአስተያየት ለውይይት @coldcommnt
★━━━━━━━━━━━━★
:¨· .·¨ :
`· .የ ፍቅር ቃል★° *゚ ተቀላቀል ክፈት

╔═ .✵. ══════════╗
@YEFKI @YEFKI @YEFKI
╚══════════ .✵. ═╝