Get Mystery Box with random crypto!

​​ መልካሙ ዶክተር ┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉ ክፍል ስድስት ዋውውውው በጣም ደስ አለ | የ ፍቅር ቃል ♡ⓛⓞⓥⓔ♡

​​ መልካሙ ዶክተር
┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉
ክፍል ስድስት


ዋውውውው በጣም ደስ አለኝ በልቤ ዶክተሩ ውሸታም ነው አልኩት ትንሽ አብረን ከተጫወታን በኋላ እዩኤል በአፉ ደም መትፈት ጀመረ... ፍቅር ፍቅር ደም እኮ ነው የተፈው አልኩት ታድያ ምነው አዲስ ሆነብሽ አለኝ ማለት እንዴት አይሆንብኝም አልኩት አይይይይ የተመመ ሰው ብዙም ጊዜ ደም ይታፍል አለኝ እዩኤል ከዚህ በፊትም ደም እየታፍ መሆኑን ነገር ግን ከእኔ ደብቆ እንደነበረ አሁን ገና ገባኝ የኔ ፍቅር ሃኪም ቤት እንሂድ አልኩት አይይይ አሁን እኮ ደህና ነኝ ደግሞ ምንም ለውጥ እንደሆነ የለም መሄዱስ ምን ያደርጋል ብለሽ ነው ባይሆን አንቺ ሁለም ደስተኛ ሁኝልኝ ደስ ስልሽ ደስ ይለኛል ብሎ እምባ ማፍሰስ ጀመረ ፍቅር እያለቀስክ እኮ ነው አልኩት የደስታ እምባ እኮ ነው አለኝ ስለ የትኛው ደስታ ነው የምታወራው አልኩት ፍቅር አንቺን አፍቅሮ ይሄን ሁሉ ወረቶችን በፍቅር አሰልፈን መሞት በራሱ ለኔ ትልቅ ደስታ ነው ብዙዎች እኮ ናቸው ይሄን እድል ማግኘት ያልቻሉት ብዙ ዘመናትን ኖረው ግን ፍቅር የሚባል ነገር በጭራሽ አያውቁም እኔ እድለኛ ነኝ፣ ፍቅር ግን ምንም ነገር ብመጣ ሀዘንተኛ እንድትሆኝ አልፈልግም ሁለም ደስተኛ ሁኝልኝ እሽ አለኝ ውዴ ስለ ምን ሞት ነው የምታወራው በእናትህ ሁለተኛ ስለ ሞት አታውራ አሁን እኮ ደህና ነህ ከዚህ በኋላ ሁሉም ነገር መልካም ይሆናል አልኩት እኔ ግን አይመስለኝም ልቤን ፍርሃት ፍርሃት ይለኛል ከዚህ በፊት እንደዚህ አይነት ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም ነበረ አሁን ግን መጨረሻው ምዕራፍ ላይ ያለውት ይመስለኛል፣ ግን ፍቅር ዶክተሩ በጣም መልካም ሰው ነው አለኝ ይሞታል የሚለውን ነገር ነግሮኝ ስለነበረ ባክህ እሱ አስጣልታ ነገር ነው እሱን ተው አልኩት ምነው ፍቅር በዚህ ዘመን እንደሱ ጊዜውን ገንዘቡን ሁሉንም ነገር አይቶ እንኩዋን ለማያውቅ ሰው አሰልፎ የሚሰጥ ሰው ማን ነው? እነዚህን ሁሉ ወረቶች የቆየውት ከፈጣሪ በታች በእሱ እርዳታ አይደል? እሱ ባይኖር ሌላ ቀርቶ ምግብ ራሱ አልነበርም እኮ አለኝ ለናገሩ እዩኤል ትክክል ነው ግን እኛ ሰዎች መቼም እውነት ተናግሮ ከሚጎዳ ሰው ይልቅ በውሸት የሚያጽናና ሰውን አብዝታን እንወዳለን የኔም ጥላቻ ከዚው የመጣ ነው። እሱማ ትክክል ነህ ግን ውሸታም ነው አልኩት ማን ዶክተር? ፍቅር እሱ በፍጹም ውሸታም አይደለም ባይሆን ይሄን ደብዳቤ ወስደሽ ቤትሽ አስቀምጪ አለኝ የምን ደብዳቤ ነው? ማነው የላከው? አልኩት ሁሉንም ነገር ደብዳቤ ላይ ታገኛለሽ ነገር ግን ደብዳቤውን አሁን መክፈት የለብሽም አለኝ እኔስ ድሮ በአንተ ፊት ምን ብዬ እከፍታለሁ ብለህ ነው አልኩት እንደዛ ማለቴ አይደለም.... ፍቅር ቤት ሄደሽም መክፈት የለብሽም አለኝ እኮ ለምን አልኩት መክፈት ያለብሽ ቀን ይመጣል አሁኑ ቀኑ አልደረሳም አለኝ እኮ ቀኑ መቼ ነው አልኩት ቀኑ

አሁን ቀኑ አልደረሰም አለኝ እኮ ቀኑ መቼ ነው አልኩት ቀኑ....በአንድ አጋጣሚ በጣም ከፍቶሽ መፍትሄ ስታጪ ደብዳቤውን ከማንበብሽ በፊት የትኛውም ውሳኔ ላይ አትድረሽ ቀድመሽ ደብዳቤውን ማንበብ አለብሽ አለኝ እሺ ፍቅር አንተው እንዳልከው አደርጋለሁ ብዬ ደብዳቤውን ተቀብዬ ቤት ሄድኩኝ.. .. ደብዳቤው ውስጥ ያለውን ነገር የማወቅ ጉጉት እረፍት ቢነሳኝም ቃል ግን ቃል ነውና በአንድ ጥሩ ቦታ ላይ አስቀመጥኩት ዶክተር አንድ ቀን ስልክ ደውሎ እዩኤል እንዴት ነው አለኝ ምንም አዲስ ነገር የለም ግን በድጋሚ ሆስፒታል መሄድ አለበት እናቴ ብሩን ለመስጠት ቃል ገብታለች አልኩት የግድ መሄድ አለበት ካልሽ ችግር የለም እኔም በቻልኩ መጠን ለመርዳት እሞክራለሁ እንደውም ነገ ጠዋት መኪና ይዤ እመጣለሁ ከዛም አንቺ የፈለግሽበት ሆስፒታል ሁሉ ይዘን እንሄዳለን አለኝ ዶክተር በጣም አመሰግናለሁ ብዬ ስልኩን ዘጋውት በልቤ ተመስገን አምላኬ ብሩ አሁን ተገኝቶዋል... እዩኤል መቼም አይሞትም ብዬ ተመልሼ ወደ እዩኤል ሄድኩኝ ዛሬ ከእሱ ጋር ብዙም ቁጭ አላልኩም.. ቤት ውስጥ የቆሸሸ እቃ ምናምን ሞልቶ ነበር እቃዎችን አጥቤ ቤቱን አስተካክዬ ወደ ቤት ተመልሼ ልመጣ ስል ፍቅር የሚል ድምፅ ሰማሁ... አቤት ብዬ ስሄድ.. ለምን ጥለሽኝ ትሄጃለሽ አለኝ አይይይ ፍቅር እናቴ ቤት ውስጥ ይጠብቁኛል ብዬ እኮ ነው አልኩት አይዞሽ አሁን ጥቂት ጊዜ ነው የቀረኝ ግን እኮ ፍቅር በጣም ነው የምወድሽ አለኝ የኔ ውድ እኔም በጣም እወድሃለሁ አልኩት እስኪ በተግባር አሳዪ ቢሉሽ ምን ታደርጊልኝ ነበረ ብሎ ጠየቀኝ የመጨረሻ ምንያህል እንደምወድህ ለማሳየት ሞት እንኳን ቢሆን እሞትልህ ነበረ አልኩት በጣም ደንግጦ.... ፍቅር ሁለተኛ እንደዚህ እንዳትዪ አለኝ የምትወጅኝ ከሆነ እኔ በሌለውበት እኔ ለምወደው ነገር ጥንቃቄ ማድረግ ነው ሞትሽ ማለት እኮ እኔን አትወጅኝም ማለት አይደል አለኝ እኮ አንተ ምንድነው የምትወደው አልኩት እናቴን ነዋ! እኔ በሌለውበት እሷን መንከባከብ የሚችል ሰው የእውነት ይወደኛል ማለት ነው ጥሏት የሞተ ሰው ግን እኔንም አይወደኝም ማለት ነው አለኝ ስለ ምን ሞት የምታወራው አሁን ስለ ሌላ ነገር እናውራ አልኩት እናትህማ ለኔም እናቴ ናት ግን አደራ ስለ ሞት አታውራ አልኩት በጣም ደስ አለው ፍቅር ብሎ እጄን ያዘኝ.... እጁ በጣም ቀዝቅዞ ነበረ... ፍቅር ለምንድነው እጅህ እንደዚህ ቀዝቃዛ የሆነው አልኩት መልስ የለም.... ፍቅር ምነው ደከምክ እንዴ አልኩት... መልስ የለም... ፍቅር አውራ እንጂ እኔ እንደዚህ አይነት ቀልድ አልወድም አልኩት.... መልስ የለም... በድንጋጤ ጩኸቴን ለቀቅኩት


ይቀጥላል ....
꧁༺༒༻꧂
ይቀጥላል
​​​​​​​​╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝

ሀሳብ በግል ለመስጠት @dkeya
• ₊° ✧︡ ˗ ˏ ˋ ♡ ˎˊ ˗ »»— ★ ——

ለአስተያየት ለውይይት @coldcommnt
★━━━━━━━━━━━━★
:¨· .·¨ :
`· .የ ፍቅር ቃል★° *゚ ተቀላቀል ክፈት

╔═ .✵. ══════════╗
@YEFKI @YEFKI @YEFKI
╚══════════ .✵. ═╝