Get Mystery Box with random crypto!

​​​​ መልካሙ ዶክተር ክፍል አምስት አዘጋጅ ሰሊና(የብዕር ስም) ዛሬ ከ | የ ፍቅር ቃል ♡ⓛⓞⓥⓔ♡

​​​​ መልካሙ ዶክተር

ክፍል አምስት

አዘጋጅ ሰሊና(የብዕር ስም)

ዛሬ ከዶክተሩ ጋር ቀጠሮ አለን፣ የእዩኤልን የምርመራ ውጤት ለመንገር ሃኪም ቤት ቀጥሮኛል ምን ይፈጠር ይሆን?
ክፍል ገብቼ ሰላም ብዬ ቁጭ አልኩኝ ዶክተር እንዴት ነህ አልኩት እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ አለኝ ታድያ እንዴት ነው የእዩኤል የምርመራ ውጤት ብዬ አይን አይኑን ማየት ጀመርኩኝ ፊቱ ላይ ጥሩ ስሜት አይታይም የሆነ ለመንገር የፈለገው ነገር ያለ ይመስላል ግን መናገር አልቻለም ዶክተር ምነው ሰላም አይደለህም? አይይይ ደህና ነኝ ታድያ ምነው? ጥያቄውን እኮ አልመለስክም አልኩት ሀረግ ትንሽ ጭንቅ ብሎኛል ሌላ ጊዜ ማውራት እንችላለን ወይ ብሎ ጠየቀኝ ምነው ዶክተር የእዩኤል ነገር ነው አይደል እባክህን እውነቱን ንገረኝ እውነቱን ማወቅ እፈልጋለሁ አልኩት አንቺ ደግሞ ሁሉንም ነገር በቃ ከእዩኤል ጋር ማገናኘት ትወጃለሽ ባይሆን ሻይ ቡና ማለት እንችላለን? ብሎ ጠየቀኝ እሺ ግን በእናትህ እዩኤልን ማጣት አልፈልግም ብቻ የሆነ ነገር አድርግልኝ አልኩት በሰው ህይወት ላይ ሁሉንም የማድረግ አቅም ያለው ፈጣሪ ብቻ ነው እንጂ ሰው ምንም ማድረግ አይችልም፣ አይዞሽ ሊሆን ያለው ነገር ሁሉ ይሆናል ብሎ ወደ አንድ ካፌ ይዞኝ ሄደ የኔ ትግል ሁሉ ስለ እዩኤል የምርመራ ውጤት ማወቅ ቢሆንም ዶክተሩ ግን ጨዋታ እየቀየረ የምርመራውን ውጤት ለመንገር ፍቃደኛ አለመሆኑን በግልጽ እያሳየ ነው። እንቆቅልሽ የሆነብኝ ነገር ቢኖር የዶክተሩ አዲሱ ፀባይ ነው በልቤ ውስጥ ብዙ ጥያቄዎች ቢኖሩም ዶክተሩን ግን ከዚህ በላይ ማስገደድ አልቻልኩም ግን ልቤ አሁንም ፍርሃት ፍርሃት ይለኛል የሆነ ችግር እንዳለ ይገባኛል ግን ምንም የማድረግ አቅም የለኝም። ቤት መጥቼ ቤት ውስጥ ብቻዬን ማልቀስ ጀመርኩኝ
እዩኤል ጋር አጠገቡ ቁጭ ብዬ የእሱን ስቃይ ከማየት ሌላ ቦታ ለብቻ መኖር ሁሉ ሳይሻል አይቀርም በሩን ዘግቼ መኝታ ክፍል ውስጥ ብቻዬን ቁጭ ብዬ ሳለቅስ ህይወቴን ከጎዳና ላይ አንስታ አዲስ የህይወት ምዕራፍ እንድጀምር የረዳችኝ እናት በሩን ማንኳኳት ጀመረች እማማ ለጥቂት ጊዜ ብቻዬን መሆን እፈልጋለሁ አልኳቸው ተይ እንጂ ልጄ እንደዚህ አትሁኚ የሆንሽውን ነገር ንገሪኝ አሉኝ እማማ ምንም አልሆንኩም በቃ ብቻዬን መሆን እፈልጋለሁ አልኳቸው ልጄ መቼም በስጋ እናትሽ ባልሆንም እኔ ግን በዚህች በጥቂት ወራት ውስጥ በክፉ አጋጣሚ ያጣውትን ልጄን መልሼ ያገኘው ነበረ የመሰለኝ አንቺ ግን የሌላ ሰው ልጅ መሆንሽን ነው የነገርሽኝ ብለው ሊሄዱ ሲሉ... በፍጥነት በሩን ከፍቼ ወጥቼ እምባ ማፍሰስ ጀመርኩኝ... እማማ እኔ እኮ የእናቴን ማንነት አላውቅም ለእኔ ከእርሶ ሌላ እናት የለኝም እናት ማለት ለኔ መውለድ ማለት ብቻ አይደለም ትክክለኛ እናት ከሆዷ ለወጣ ልጅ ብቻ ሳይሆን ለየትኛውም ልጅ የሚያዝን ልብ ያላት እናት ናት ስለዚህ እኔ እናት የለኝም አልልም እናቴ እርሶ ኖት አልኳቸው ታድያ ለምን የሆንሽውን አትነግሪኝም ከእናት የሚደበቅ ነገር እኮ የለም አሉኝ በቃ እማማ ጓደኛዬ ሊሞት ነው አልኳቸው በጣም ድብቅ ነሽ ማለት ነው በቃ አሁን አንቺ አታልቅሽ የትም የትም ብለን ይድናል አሉኝ እማማ አመሰግናለሁ ብዬ ቶሎ ብዬ ወደ ዶክተሩ ሄድኩኝ ከዛም የሆነውን ነገር ሁሉ ነገርኩት እሱ ግን ምንም ደስ አላለውም ምነው ዶክተር ደስ አላለህም? እዩኤል እኮ ሊድንልኝ ነው አልኩት እግዚአብሔር ቢያደርግልሽ ደስ ይለኛል አለኝ ማለት? አልገባኝም ሀረግ ያልናገርኩሽ ነገር አለ አለኝ እኮ ምንድነው ዶክተር? ንገረኛ አልኩት ምን መሰለሽ ሀረግ...


ሀረግ የሆነ ያልናገርኩሽ ነገር አለ አለኝ እኮ ምንድነው ዶክተር ንገረኛ አልኩት ምን መሰለሽ ሀረግ አንቺ በጣም ጠንካራ እና ብልህ ልጅ ነሽ ስለዚህ የትኛውም ነገር ብመጣ ጽኑ መሆን አለብሽ ደግሞ ሁሉም ነገር በእግዚአብሔር ፍቃድ እንደሚሆን ታውቃለሽ አይደል ስለዚህ ጠንካራ መሆን አለብሽ አለኝ ዶክተር ስለ ምክሩ አመሰግናለሁ ያልናገርከኝ ነገር ግን ምንድነው ምንም ይሁን ምን ማወቅ እፈልጋለሁ ንገረኝ ብዬ መስጨናቅ ጀመርኩት ሀረግ ይሄን የምናግርሽ ብልህ ልጅ ነሽ ብዬ ስለሚያምን ነው እዩኤል የምርመራ ውጤት እንደሚያሳይ ከሆነ በህይወት መቆየት የምችለው ሁለት ወረቶችን ብቻ ነው ይህን የምናግርሽ ግን ቅድም እንደልኩሽ ብልህ እና ጠንካራ ሴት ስለሆንሽ ነው እነዚህን ጥቂት ቀናቶችን በሀዘን ሳይሆን በደስታ ለማሳለፍ ሞክሪ በርግጥ አውቃለሁ በጣም ከባድ ነው ቢሆንም ግን እዩኤል ሁለት ወር ራሱ መቆየት የምችለው ደስተኛ ከሆነ ብቻ ነው ይህ ከሊሆነ ሁለት ወር ራሱ መቆየት አይችልም እዩኤል እነዚህን ሁለት ወረቶችን እንዲቆይ የምትፈልጊ ከሆነ በሱ ፊት ደስተኛ መሆን መቻል አለብሽ ፍቅረኛሽን መትረፍ በለመቻሌ አዝናለሁ አንቺ ግን እራስሽን ጠብቂ አለኝ ዶክተር ምን እያልክ እንደሆነ ተውቆሃል? እዩኤል ይሞታል እያልከኝ እኮ ነው ቆይ ግን ምን አይነት ሞርተኛ ነህ? ዶክተር ብሩ እኮ ተገኝተዋል ዶክተር እዩኤል አይሞትም አልኩት ሀረግ ይሄ የብር ጉዳይ አይደለም ሰአቱ አልፏል It's too late ከእንግዲህ ወዲህ ተአምር ከልተፈጠረ በስተቀር እዩኤል የማዳን እድል የለውም አለኝ ዶክተር እዩኤል እይሞትም እያልኩ መንገድ ላይ ብቻዬን እዩኤል አይሞትም እያልኩ ወደ ቤት ተመለስኩኝ ቤት ውስጥ መጥቼ ከእግዚአብሔር ጋር ክርክር ጀመርኩኝ ቆይ ለምን ነብሴን እሾህ መሃል ፈጠርከት? አንዱን ሰጥታኝ አመስግኜ ሰልጨርስ ለምን ሌላውን ትወስድብኛለህ? ቆይ እኔ ደስተኛ እንዲኖር በ40ኛው ቀን ላይ አልተጻፈም? እያልኩ ያለውን የሌላውን ሁሉንም መጠየቅ ጀመርኩኝ አሁንም ግን መልስ የሚሰጠኝ አካል የለም ሰማይ ዝም አለ መንፈሴ ሰላም አጠች ነብሴ ተጨናቃች በዚህ ሰአት ከእኔ ከጤነኛ ሀረግ ህመምተኛው እሱ ይሻላል ለመሞት ከተዘጋጀው ከእሱ ይልቅ እኔ ተስፋ ቆረጥኩኝ ተመልሼ እና እዩኤል ቤት ሄድኩኝ በጣም ጤነኛ ሰው ይመስላል፣ ፍቅር መጣሽ አሁን እኮ በጣም ደህና ነኝ ደብሮኝ ነበረ እንኳን መጠሽ ብሎ መጫወት ጀመረ ዋውውውው በጣም ደስ አለኝ በልቤ ዶክተሩ ውሸታም ነው አልኩት ትንሽ አብረን ከተጫዋተን በኋላ እዩኤል ከአፉ ደም መትፈት ጀመረ

꧁༺༒༻꧂
ይቀጥላል
​​​​​​​​╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝

ሀሳብ በግል ለመስጠት @dkeya
• ₊° ✧︡ ˗ ˏ ˋ ♡ ˎˊ ˗ »»— ★ ——

ለአስተያየት ለውይይት @coldcommnt
★━━━━━━━━━━━━★
:¨· .·¨ :
`· .የ ፍቅር ቃል★° *゚ ተቀላቀል ክፈት

╔═ .✵. ══════════╗
@YEFKI @YEFKI @YEFKI
╚══════════ .✵. ═╝