Get Mystery Box with random crypto!

።።።።።።።።ሳይበረታ ድረስ።።።።።።። አየኸው ዝናቡን አንተን ሲያስታውሰኝ ካለፈው ትዝታህ ወስዶ | የፍቅር ጥቅሶች❤️

።።።።።።።።ሳይበረታ ድረስ።።።።።።።

አየኸው ዝናቡን አንተን ሲያስታውሰኝ
ካለፈው ትዝታህ ወስዶ ሲመልሰኝ
ተመለከትክልኝ የብርዱንስ ብርታት
አንተን እያስመኘ ሲናፍቅ ቀን ከሌት
አስተውለኸዋል የበረዶውን ዶፍ
ወደነዛ ቀናት የዃሊት ሲያከንፍ
አየህልኝ ውዴ ክረምቱ በረታ
ልቤም አንተን አለኝ ፍቅርህ ልቤን ረታ
     ታድያልህ አለሜ............
ናፍቆትህ በርትቶ ካልጋ እንዳላድር
በትዝታህ ባህር ሰምጬብህ ሳልቀር
ዝናቡ ሳይጠና ብርዱም ሳይጠነክር
ሳይበረታ ድረስ ህመሜም እንዲሽር።
ማኪ
─━━━━ ⊱✿⊰ ━━━━━─

@yefikir_tiksoch 
@yefikir_tiksoch 

ሼር