2022-06-10 13:26:48
አስተዋዩ ሰው
አንድ ዓይነ ስውር ልጅ በህንጻ ደረጃ ላይ
በእግሩ ስር መለመኛ ኮፍያ አድርጎ ተቀምጧል።
“አይነ ስውር ነኝ እባካቹ እርዱኝ” ተብሎ የተፃፈበት
ምልክትም ይዟል። በዚህን ጊዜ በባርኔጣው ውስጥ
ጥቂት ሳንቲሞች ብቻ ነበሩ።
አንድ ሰው በአጠገቡ ሲያልፍ ከኪሱ ጥቂት ሳንቲሞች
አወጣና ኮፍያው ውስጥ አስቀመጠ።
ከዚያም ምልክቱን አንስቶ አንዳንድ ቃላትን ፃፈና
በአጠገቡ የሚሄዱ ሰዎች ምልክቱን
በሚያዩበት ቦታ አስቀምጦ ይሄዳል።
ሰውየው ከመሄዱ ብዙም ሳይቆይ ባርኔጣው
በሳንቲሞች መሙላት ጀመረ።
ብዙ ሰዎች ለዓይነ ስውሩ ልጅ ገንዘብ
እየሰጡት ያልፋሉ። የዚያን ቀን ከሰአት ላይ ምልክቱን የለወጠው
ሰው ሁኔታውን ለማየት ይመጣል። ልጁ የሰውዮውን
እግር አውቆ "ዛሬ ጠዋት ምልክቴን የቀየርከው አንተ ነህ አይደል?
ምን ነበር የፃፍከው?" ሲል ይጠይቀዋል።
ሰውየውም ''እውነቱን ብቻ ነው የፃፍኩት። ነገር ግን
የፃፍከውን ነገር እኔ በሌላ መንገድ ነው የፃፍኩት።"
ብሎ ይመልስለታል።
የጻፈውም "ዛሬ በጣም ደስ የሚል ቀን ነው።
እኔ ግን ላየው አልቻልኩም" የሚል ነበር።
የመጀመሪያው እና ሁለተኛው ምልክት ተመሳሳይ
ነገር የሚናገሩ ይመስላችኋል?
@yefekrneger
125 views Hånĭ, 10:26