‹‹አዲስ ዓመት መልካሙን የምንሰራበት ይሁንልን!›› : ☞ዘመናትን የሚያቀያይርና አዲስ ዓመትን የሚሰጠን እርሱ ፈጣሪ ነው። : ይህንን የፈጣሪን ምህረትና ቸርነት የምናስብ ስንቶቻችን ነን? : ሰው ደግሞ ተጨማሪ አዲስ ዓመትና እድሜ ካልተሰጠው ምንም ማድረግ አይችልም፡፡ : ፈጣሪ እንድንኖር ካልፈቀደልን አዲሱን ዓመት ካልሰጠን ምንም ነገር ማድረግ አንችልም፡፡ : # ሌላው ቀርቶ፦ ፡ ➊.ወጥተን→የምንገባው፣ : ➋.ተቀምጠን→የምንነሣው፣ : ➌.ተምረን ለውጤት→የምንበቃው፣ : ➍.ሠርተን→የምናገኘው፣ : ➎.ነግደን→የምናተርፈው፣ : ➏.ወልደን→የምንስመው፣ : ➐.ለመጪው ዓመት ብለን እቅድ→የምናቅደው ፈጣሪ እንደ ቸርነቱ ወደ አዲሱ ዓመት እንድንሸጋገር ሲፈቅድልን ነው፡፡ : √ብዙ ሰዎች ግን የፈጣሪን ቸርነት ረስተዋል፡፡ : √አዲስ ዘመን ሲሰጠን ዋጋ የሚከፈልበት ቢሆን ኖሮ ዋጋውን ማን ይችለው ነበር? : √ግን ፈጣሪ አዲስ ዓመት የሰጠን ያለዋጋ በነፃ ነው። ፡ √ለምንኖርበት ዕድሜ ለሰጠን ተጨማሪ ዓመት የጠየቀን ዋጋ የለም፡፡ : √ታዲያ ጊዜ የሰጠን ፈጣሪ ደግሞ ጊዜ እንድንሰጠው እንድናመሰግነው ይፈልጋል። : ❀︵♡︵♔︵♡︵♔︵♡︵♔︵♡︵❀ : # አዎን ወዳጆቼ፥ ፡ ☞አንዳንድ ሰዎች እንዲኖሩ፣ እንዲወጡና እንዲወርዱ አዲስ ዓመትና ጊዜ ፈጣሪ ሰጥቷቸው ሳለ አዲስ ዓመት ለሰጣቸው ለፈጣሪ ግን ጊዜ መስጠትና ማመስገን ተስኗቸው ይስተዋላሉ፡፡ : ♡ይህቺን ቀን አስበው እዚህች ቀን ላይ፣ ለዚህች ዓዲስ ዓመት ያልደረሱ ብዙ ሰዎች አሉ። ፡ ♡አንተ እኔ ሁላችንም ግን ደርሰናልና እንደ ቸርነቱና ምህረቱ ለዚህ ላደረሰን አምላካችን እንዲህ እያልን እንፀልይ፦ ፡ ➊.አምላካችን ሆይ፥ አዲሱን ዓመት ስለሰጠኸን እናመሰግናሀለን። : ➋.አምላካችን ሆይ፥ ከዚህ በኋላ የሚኖረን ቀሪ እድሜ በፊትህ ያማረ ይሁንልን፡፡ : ➌.አምላካችን ሆይ፥ እድሜና ዘመናችን በቤትህ ይለቅ፡፡ : ማለዳ ማለዳ በአዲስ ምስጋና፣ : በአዲስ ዝማሬ፣ : በአዲስ ሽብሸባ፣ : በአዲስ ቅኔ፣ : በአዲስ እልልታ ይህ በረከት የሆነው እድሜና ዘመናችን በቤትህ ይለቅ፡፡ ፡ ➍.አምላካችን ሆይ፥ ሳናመሰግንህ ላለፉት የምህረት አመታት ሁሉ ዛሬ ይቅር በለን፡፡ : ➎.አምላካችን ሆይ፥ የሚከፋፍለን የሚያለያዬንን የጥል፤ የክርክር፤ የዘረኝነት ግድግዳ አንተ አፍርስልን። : ➏.አምላካችን ሆይ፥ በአዲሱ ዓመት ፍቅርና አንድነትን ስጠን። : ➐.አምላካችን ሆይ፥ ሐገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ባርክ። : ➑.አምላካችን ሆይ፥ በሰጠኸንም እንደ ቸርነትህ በጨመርክልን አዲስ ዓመት መልካሙን እንድንሰራበት አንተ ይርዳን! # ለዘላለሙ አሜን! : ♡እስኪ ተመስገን በሉት። ተመስገንንንንንንንንንንንንንንንን : ❀︵♡︵♔︵♡︵♔︵♡︵♔︵♡︵❀ : # መጪው አዲስ ዓመት፦ ፡ ➊.ሀጥያትን→በጽድቅ፣ ፡ ➋.አለመጸለይን→በመጸለይ፣ ፡ ➌.ስጋዊነትን→በመንፈሳዊነት፣ ፡ ➍.አለማገልገልን→በማገልገል፣ ፡ ➎.ድህነትን→በመስራት፣ : ➏.አለማንበብን→በማንበብ፣ : ➐.አለማወቅን→በመማር፣ : ➑.ጥላቻን→በፍቅር፣ : ➒.ክፉን→በመልካም፣ : ➓.ንፉግነትን→ በመስጠት፣ የምንከርመበትና ፍቅር የበዛበት ብሩህ ዘመን ይሁንልን! : [☞መልካም አዲስ ዓመት☜] : «ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ» : "ሰላማችሁ ይብዛ" : #አድራሻ ፦ #ቤቴል አደባባይ 100 ሜትር ወረድ እንዳሉ ኑሃ ህንፃ ቢሮ ቀጥር 3 ላይ እንገኛለን። ለቀጠሮው +251927707000 ይደውሉ #ሰው_ሁን_ከሰውም_ሰው_ሁን #ቴሌግራም https://t.me/BiniGirmachew https://t.me/BiniGirmachew https://t.me/BiniGirmachew SUPPORT ON YOUTUBE tiktok tiktok.com/@bini_girmachew tiktok.com/@bini_girmachew #ሰው_ሁን_ከሰውም_ሰው_ሁን 2.7K views19:56