Get Mystery Box with random crypto!

ሳልነግርህ . . አፍቅሬ እንዳጣሁህ በነብያቶች አፍ ፍልስፍና ሚመስል፣ ትንቢት ተነገረ ታምር የ | የዱርዬ ፍቅር

ሳልነግርህ
.
.
አፍቅሬ እንዳጣሁህ
በነብያቶች አፍ
ፍልስፍና ሚመስል፣ ትንቢት ተነገረ
ታምር የሚሰራ
ጎትቶ ጎትቶ
በመርፌ ቀዳዳ፣ ግመል አሻገረ
ግመሉ ሲሻገር፣ መርፌው ተሰበረ
በሰባራ መርፌ
ፍቅርህን ከፍቅሬ፣ ባንድነት ልሰፋ
ይኸው እደክማለሁ
ክር ሆነህ እያጠርክ ፣ ኖራለሁ ስለፋ




@yedurye_fkr
@yedurye_fkr