Get Mystery Box with random crypto!

በዚህ ታላቅ ወር የተከሰቱ ታሪካዊ ክስተቶች...! 1ኛ- በሙሐረም ወር መጀመሪያ 1318ሒ. ሱልጧ | ሸምሸ ዳኒ [ ዳና የሀድራ ጀመዐ ] chennel

በዚህ ታላቅ ወር የተከሰቱ ታሪካዊ ክስተቶች...!

1ኛ- በሙሐረም ወር መጀመሪያ 1318ሒ. ሱልጧን አብዱልሐሚድ ثሳኒ ሁጃጆችን ወደ ሒጃዝ የሚወስድ የባቡር መስመር ዝርጋታን እንዲጀመር ወሰነ።
ለዘጠኝ ዓመትም ስራው ቀጠለ ነገር ግን ከዚህ በኋላ ለብልሽነት ተጋለጠ።

2ኛ- በሙሐረም በሶስተኛ ቀን 239ሒ. የቡኻሪና የሙስሊም ሸይኽ የዠሆኑት ታላቁ ሐፊዝ ኡስማን ኢብኑ ሙሐመድ ኢብኑ ኢብኑ ኢብራሂም ኢብኑ አቢ ሸይባ አረፉ..!

3ኛ- በሙሐረም 8ኛው ቀን በ923ሒ. የኡስማንያ ሰርወ መንግስት ወደ ቃሒራ ገባ የማምሉክ ስልጣን በሻምና በግብፅ ወደቀ፥ የማምሉክ ስልጣን ሲወድቅ የአባስይ ኺላፋም አብሮ ወደቀ ኡስማንያዎች ኺላፋውን ተቆጣጠሩ..!

4ኛ- ሙሐረም 10 በ61ሒ. የሰይዳችን ﷺ የልጅ ልጅ የሆኑት ሁሰይን ኢብኑ ዓልይ [ረዲየሏሁ ዓንሁማ] በከርበላእ በበዳዮች ሸሒድ ሆኑ...!

5ኛ- በሙሐረም 10 በ5ሒ. የዛቱሪቃ ዘመቻ ነበር።

6ኛ- በሙሐረም 18 በ414ሒ. ታላቁ ፈቂህ ኡሱልይ አቡ ሙዓሊ አብዱል-መሊክ ኢብኑ አብዱሏሕ ኢብኑ ዩሱፍ አልጁወይንይ ኢማሙል ሐረመይን በመባል የሚታወቁት ተወለዱ..!

7ኛ- ሙሐረም 21 በ430ሒ. ታላቁ ዓሊም የታሪኩ ሙሁር አቡ ኑዓይም የ‛የሒልየቱል-ዓውሊያእ’ ባለቤት አረፉ...! ረዲየሏሁ ዓንሁ

8ኛ- በሙሐረም 27 በ549ሒ የኢርቢል ሐገር መሪ ሙዞፈሩዲን ከውከብርይ አንድኛው የሙጃሒዱ ሶላሁዲን አልዓዩብይ ፈረንጆችን በመዋጋት ጊዜ የጦር መሪ የነበሩት፥ ለመጀመሪያ ጊዜ መውሊድን በማህበር እንዲከበር የጀመሩት ተወለዱ..!

9ኛ- በሙሐረም 30 በ7ሒ የኸይበርን ዘመቻ አደረጉ፥ ድልንም ተጎናፀፉ...!


ሙሐረም 11-1444ሒ.

JOIN AND SHARE

https://t.me/+XBeaC-I2mctmNjE8