Get Mystery Box with random crypto!

ዲና{DINA} {ተከታታይ ልበወለድ } @yebirihan_lijoch ''''''''''''' | የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

ዲና{DINA}
{ተከታታይ ልበወለድ }
@yebirihan_lijoch

"""""""""""""""ክፍል """""""""""""

.....እስክመለስ ጨንቆኛል ዛሬ አርብ ነው ጥበብ ደውላ በፍጥነት ልታገኘን እንደምትፈልግ ነገረችኝ ምነው ምን ተፈጠረ ስላት ቶሎ ነይ ብላኝ ያለችኝ ቦታ ሄድኩ ገና ቁጭ ሳልል ስሚ መኖር አትፈልጊም አለችኝ ማለት ስላት ስለ እግዚአብሔር ስታወሪ መንፈሳዊ ሰው ትመስዬኝ ነበር አለችኝ ምነው ጥበብ ምን አድርጌሽ ነው ስላት አንድ ፎቶ ሰጠችኝ ፎቶው ላላይ እኔና ሰውዬው ተቀምጠን ነበር ሆቴል ውስጥ ቀኑን ሳስታውስ ሰውዬው የሆነ ቀን ሳምሪን ካላገኘውሽ ብሎአት ስትለምነኝ አብሬአት ሄድኩ አለመታደል ሆኖ ሳምሪ መታጠቢያ ቤት ልሂድ ብላ ሁለታችን ነበርን ኸረ ጥበብ እንዳሰብሽው አይደለም ብዬ ሁሉንም ነገርኳት ።
ስሚ ሰውዬው እኮ የሊዲያ ባል ነው
ምን ትልቅ ሰው እኮ ነው አልኳት አዎን ሊዲያም ለገንዘቡ ብላ ነው የተዋወቁትም እዚህ ሴቶችን ሊያድን በመጣበት ነው እሷ ምንም ዘመድ የላትም በችግር ና ስቃይ ነው ያደገችው ትምህርቷን ተምራ ህልሟን ለማሳካት ነው ሚስቱ ሆና ቸገባችው አሁን ግን እድሜ ለእናንተ አይንሽን ለአፈር ብሎአታል ልጅቷ በምን ትማር ብላ አፈጠጠችብኝ ታዲያ እኔ ምን አደረኩ አልኳት እሷ ምክኒያቱን ለማጣራት ከማን ጋር እንደሚውል ስታጣራ በተደጋጋሚ አብራችሁት የታያችሁት እናንተ ናችሁ ሳምሪ አልሽ እንጂ እሱ አንቺን ሊያገባ እንደሆነ ነግሮ ነው ያባረራት አለችኝ ምን ትልቅ ሰው አይደል እንዴ አይከበርም ምን አይነት ጣጣ ነው እሺ ሊዲያስ አልኳት እሷማ እየሸረበችልሽ ነው ።
@yebirihan_lijoch

እደፋታለሁ ነው ወሬዋ ሁሉ ካገኘችሽ አትለቅሽም ከሳምሪ ጋር በጭራሽ ጭር ወዳለ አከባቢ እንዳትሄዱ ወደ ውጪም አትውጡ ሹፌሮችን ስለምታውቃቸው ሆን ብላ ወጥመድ ልታዘጋጅላቹ ትችላለች ሊዲያ ለማንም አትመለስም እንዳልኩሽ የሰው ፍቅር አታውቅም ምክኒያቷን ሌላ ጊዜ ነግርሻለሁ ራሳቹን ጠብቁ አለችን እሺ ቆይ ግን ዘመድ ከሌላት ማን ጋር ነው ለእረፍት ምትሄደው አልኳት የትም አትሄድም ካወኳት 3 አመት ሰውዬው ጋር ነው ምትሄደው አብራው ትኖራለች በጣም ሀብታም ስለሆነ የቤቱ እመቤት ነበረች ያንን የመሠለ ህይወት እንደቀማቹአት ነው ምታስበው በይ በይ አብረን ካየችን እኔም ያበቃልኛል ብላኝ እየሮጠች ሄደች ወደ ዶርም ተመልሼ ስሄድ ሳምሪ የለችም ፀጋ ሳምሪስ ስላት እንጃ ተደውሎላት መሠለኝ የወጣችው አለችኝ ወይኔ አምላኬ ልጅቷን ምን አገኛት ስልኳ ጥሪ አይቀበልም ምጥ እንደያዛት ሴት መንቆራጠጥ ጀመርኩ በሁላችንም ስልክ ብንሞክር ስልኳ አይሰራም ሁሉም እንደኔ ተጨንቀዋል ለ አብ ፀጋ ደውዬ የተፈጠረውን ነገርኳቸው ከዚህ በፊት ስለ ሊዲያ ስላወራዋቸው በጣም ነው የተጨነቁት ለአብፀጋ ደውዬ ነገርኩት ስልኳ ካልሰራ የት ብለን እንፈልጋታለን እሱም ግራ ገባውየተለያዩ ጥያቄዎችን ጠየቀኝ ምንም ተስፋ አይሰጡም በዛ ላይ ከምሽቱ 3:37 ይላል የስልኬ ሰዓት ለጥበብ ደወልኩላት በሹክሹክታ ድምፅ አንቺ ምን ሆነሻል በዚህ ሰአት አለችኝ ስመለስ ሳምሪ አልነበረችም ሊዲያ .. ኸረ እሷ እዚሁ ናት ተኝታለች የት ልትሆን ትችላለች አለችኝ እኔ አላውቅም ብዬ ሳለቅስባት በቃ ተረጋጊ በጠዋት እንፈልጋታለን ብላኝ ስልኩን ዘጋችው ጭንቀቴ እጥፍ ድርብ ሆነ ሁሉም እያየኋቸው አንድ በአንድ እንቅልፍ ወሰዳቸው እኔ አእምሮዬ ተበጠበጠ ገና በመጀመሪያ አመት ምን አይነት ስቃይ ነው 7ሰአት ሆነ እማ ደወለችልኝ በዚ ሰአት ምን ሆና ይሁን ብዬ አነሳሁት ገና ሳነሳው ይኸው እንደፈራሁት የኔ ልጅ ምን ሆንሽብኝ አለችኝ ምነው እማ ስላት ይኸው እየተረበሽኩ ነው ሰሞኑን ስለ አንቺ የማልመው ሁሉ ጥሩ አይደለም አሁንም እንቅልፍ አጣሁ ልጄ አመመሽ እንዴ አለችኝ እምባዬ መጣ ኸረ እማ ደህና ነኝ ተረጋጊ ስላት እሺ እስከአሁን እንዴት አልተኛሽም አለችኝ አይ እማ ፈተና ደርሶ የለ ለዛ ነው አልኳት ወዲያው አባቢ ሄለው የኔ ልጅ ደህና ነሽ አይደል አለኝ አዎን አባ አረጋጋት አልኩት ይኸው ሰሞኑን ለራሷ ተጨነንቃ እኔንም እየረበሸችኝ ነው በይጨራስሽን ጠብቂ ብሎኝ ስልኩ ተዘጋ በጣም እየተረበሽኩ ነው ወይ እንቅልፍ አይወስደኝ ማስበውን ሁሉ አላውቅም ለእዩ ደወልኩለት ገና አንዴ ጠርቶጰሳይጨርስ አነሳው ደነገጥኩ ምነው ዲኑ እስካሁን አልተኛሽም አለኝጨአንተ ራስህ አልተኛህም አልኩት አይ እኔ እያነበብኩ ነበር በሰላም ነው ድምፅሽ ልክ አይደለም አለኝ እዩ ላብድ ነው በቃ አቃተኝ አልኩት ምነው ምን ሆንሽብኝ ተረጋጊ መጀመሪያ ሲለኝ ሁሉንም ተረኩለት ስለ ሊዲያም ስ ሰውዬውም ሊያረጋጋኝ ከሞከረ በኋላ እናንተ ድሮ ከሽማግሌ ጋር እንዴት ገጠማቹ ደግሞ አንቺስ አትተያትም ስለ መጥፎነቷ እየተነገረሽ ብሎ ብዙ ተቆጣኝ አንተ ደግሞ ስለ ጨነቀኝ እንጂ እንድትወቅሰኝ ነው እንዴ የነገርኩህ አልኩት እሺ ይቅርታ ግን ተረጋግተሽ ለመተኛት ሞክሪ ብሎ አረጋግቶኝ ስልኩ ተዘጋ ሰአቱ 9:43 ይላል እውነትም ልተኛ ብዬ ለመተኛት ጥረት አደርኩ የማይደርስ የለ ነግቶ ወፎች መንጫጫት ጀመሩ .........


.........ይቀጥላል...........

@yebirihan_lijoch
@yebirihan_lijoch