Get Mystery Box with random crypto!

• ኮንፊደንስ እንደሌለህ ቢሰማህ እንኳን እንዳለህ ሆነህ ተንቀሳቀስ፡፡ መስታወት ፊት ቆመህ በራስህ | ያበደች የአራዳ ልጅ

• ኮንፊደንስ እንደሌለህ ቢሰማህ እንኳን እንዳለህ ሆነህ ተንቀሳቀስ፡፡ መስታወት ፊት ቆመህ በራስህ ኮንፊደንስ እንዳለህ እየተናገርክ እራስህን አዘጋጅ

• የምትፈልገዉን ነገር ብቻ መጠየቅን ተለማመድ፡፡ የምትፈልገዉን ነገር ግልፅና ቀጥተኛ በሆነ መንገድ ጠይቃቸዉ፡፡

መጀመሪያ ይህን ነገር ስትናገር ሰዎችን ግር ልታሰኝ ትችላለህ ግን በዚህ ተደናግጠህ አታቁም፡፡ ይህን ማድረግህ በራስህ የመተማመን ስሜትህን በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራል፡፡

ይህ ልምድ በጣም ቀላል ሊመስልህ ይችላል ነገር ግን ብዙ ሰዉ ያልታደለዉ ወሳኝ ባህሪ ነዉ፡፡ ገና ለገና ይሄ ሰዉ ያዝንብኛል በሚል ይሉኝታ ዉስጥህ ያለዉን ነገር መተንፈስ ባለብህ ሰአት ሳትናገረዉ ቢያልፍህ በራስ መተማመንህን ይሸረሽረዋል፡፡

• መጥፎ ልማድህን ቀንስ፡፡ መጥፎ የምትለዉን ባህሪ ለይተህ ተዋጋዉ! ከሱ ተቃራኒ የሆነዉን መልካም ባህሪ በመሙላት የሚገርም ማንነት ያለዉ ሰዉ መሆን ትችላለህ

• ትርፍ ናቸዉ በምትላቸዉ ሰአቶችህ እራስህን በምትወደዉ ነገር ሙላዉ፡፡ ለምሳሌ ረጅም ጉዞ የምታደርግ ከሆነ መፃህፍትን ብታነብ ወይንም ጠቃሚ የሆኑ ነገሮችን ከሞባይልህ ላይ ብታነብ አሪፍ ነዉ፡፡

• ስራህን ዉደድ፡፡ ስለስራ ሲነሳ ብዙ ሰዉ ይደብረዋል! ደሞዙ ትንሽ ነዉ፣ አለቃዬ በጣም ያናድደኛል ወዘተ...የሚሉ ምክንያቶችን ልትዘረዝር ትችላለህ፤ነገር ግን በመስራትህ ነዉ ብዙዎቹን ወጪዎችህን የምትሸፍነዉ፣የቤት ኪራይህን የምትከፍለዉ...

የምትጠላዉ ስራ እንኳን ቢሆን የምትወደዉን እስክትሰራ ድረስ ጥርስህን ነክሰህ እየሰራህ ያለዉን ስራ ዉደደዉ