Get Mystery Box with random crypto!

የሆነች የተመቸችህ ሴት ከተዋወካትና አንድ ሁለት ካወራችሁ በኋላ ስልኳን ጠይቀሃት ሰጠችህ እንበል፡ | ያበደች የአራዳ ልጅ

የሆነች የተመቸችህ ሴት ከተዋወካትና አንድ ሁለት ካወራችሁ በኋላ ስልኳን ጠይቀሃት ሰጠችህ እንበል፡፡ ግን ስልክ ቁጥሩ የራሷ መሆኑንና አለመሆኑን በምን ታረጋግጣለህ?

ልክ ስልክሽን ፃፊዉ ብለሃት የራስህን ስልክ ስትሰጣት ስልክ ቁጥሯን ፅፋ ትጨርስ የለ? አንድ ነገር ታደርጋለህ

“እንዳልሳሳት የኔ ቆንጆ ሰልክሽ 0913524 ...ነዉ አይደል?” ብለህ አንድ ሁለት ቁጥር አሳስተህ ትጠይቃታለህ...ቶሎ ብላ አዎ ካለችህ ስልኳን አልሰጠችህም ማለት ነዉ፡፡ በአጭሩ ሙድ እየያዘችብህ ነዉ! በተግባር ላሳይህ፡፡

እኔ፡ እናቱ ስልክሽን ትሰጪኝ? አለ አይደል የሃረሯ ቆንጆ የሚል ግጥም ስለገጠምኩልሽ እንድታዳምጪኝ ስለምፈልግ ነዉ እንጂ ሀገርኛ ጠበሳ ለማካሄድ አይደለም

እሷ፡ ኪኪኪ...እሺ 0912****00

እኔ፡ ኦኬ...አመሰግናለሁ ቆንጆ!

እኔ፡ ወይኔ! ሴቭ ሳላደርገዉ ጠፋብኝ፡፡ አዎ 0912****10 ነዉ አይደል?

እሷ፡ አዎ!

እኔ፡ (ወይኔ! አይ ሴት!!!)