Get Mystery Box with random crypto!

የህክምና መረጃ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ye_doctor_doctor — የህክምና መረጃ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ye_doctor_doctor — የህክምና መረጃ
የሰርጥ አድራሻ: @ye_doctor_doctor
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.29K

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-01-12 17:57:14 ስቅታ የሆድ እቃንና ደረትን የሚለየው ዳያፍራም የሚባል ጡንቻ በሚኮማተርበት ጊዜ የሚከሰት ችግር ነው
692 viewsHi, 14:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-12 17:56:59 ልጆች እያደጉ ሲሄዱ መቀመጥ መዳህ፤መሮጥ፤ደረጃ መውጣት ክህሎቶችን ያዳብራሉ
663 viewsHi, 14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-09 10:27:57
1.0K viewsHi, 07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-09 10:26:06 ፓፓዬ የዓለማችን ተመራጭ በሽታ ተከላካይ ምግብ
*****************************
ፓፓዬ በቫይታሚን ሲ እጅግ የበለፀገ የዓለማችን የፍራፍሬ
አይነት ነው።

ፓፓዬ ካሉት በርካታ የጤና በረከቶች በጣም የተወሰኑትን
ልናካፍልዎ ወደድን

1.በሰውነታችን የኮሌስትሮል መጠን እንዲቀንስ የጎላ አስተዋኦ ያበረክታል!
ፓፓዬ በፋይበር፣ ቫይታሚን ሲ እና የተለያዩ አንቲኦክሲዳንቶች
የበለፀገ በመሆኑ እነዚህ ነገሮች በደምስሮቻችን ውስጥ
የኮሌስትሮል ክምችት እንዳይኖር ያደርጋሉ።
በዚህም የስትሮክ ህመም እና ሀይፐርቴንሽን ችግር
እናዳይገጥመን የጎላ ሚና አላቸው።

2.ክብደት ለመቀነስ ተመራጭ ነው!
ክብደታቸው እንዲቀንስ የሚፈልጉ ሰዎች ፓፓያን ከምግብ
ገበታቸው ማራቅ የለባቸውም፣
ፓፓዬ አንስተኛ ካሎሪ እና ጥሩ የሚባል ፋይበር ያለው በመሆኑ
ክብደታችን ባልተፈለገ ሁኔታ እንዳይጨምር ይከላከላል።

3.በሽታ የመከላከል አቅምን በከፍተኛ ደረጃ ያሳድጋል!
አንድ የፓፓዬ ፍሬ በቀን ከሚያስፈልገን ቫይታሚን ሲ200
በመቶ ያህሉን በውስጡ ይዟል።
ይህም ኢንፌክሽንን ጨምሮ ሰውነታችን ሊደስበት የሚችለውን
ህመም ለመመከት ፓፓዬ እጅግ ተመራጭ የምግብ ዓይነት
ያደርገዋል።

4. ፓፓዬ ለስኳር ህመም እንዳንጋለጥ ያግዛል!
ፓፓዬ ምንም እንኳን ጣፋጭ ቢሆንም አንስተኛ የስኳር መጠን
በመያዙ የስኳር ህመመተኞች ጨምሮ ለማንኛው ሰው
የሚመከር የፍራፍሬ አይነት ነው።

5. ፓፓዬ ለአይን ጤንነት የሚበጅ ነው!
ፓፓዬ በቫይታሚን ኤ የበለፀገ በመሆኑ የተሻለ ዕይታ እንዲኖረን
ከማድረጉም ባለፈ ከአይን ጋር ተያያዥ በሆኑ ህመሞች
እንዳንጠቃ ይረዳናል።

6.ፓፓዬ በተለይ ከወር አበባ ጋር ተያይዞ ለሚከሰት ህመም
ፍቱን ነው!
በፓፓዬ ውስጥ የምናገኘው ፓፔን የተባለው ኢንዛይም የወር
አበባ ፍሰትን ከማስተካከል ባለፈ ተያይዞ የሚከሰትን ህመም
በመግታት እፎይታን ያጎናፅፋል።
በመሆኑም በወር አበባ ወቅት ሴቶች ፓፓዬን እንዲያዘወትሩ
ይመከራል።

7.ፓፓዬ ካንሰርን ይከላከላል!
ፓፓዬ ፓይቶ ኒውትረንትስ እና ፍላቮኖይድስ በተሰኙ
አንቲኦክሲዳነትስ እንደመበልፀጉ መጠን የሰውነታችን ሴሎች
እንዳያረጁ፣ እንዳየሞቱ እና ለተለያዩ የካንሰር ህመሞች
እንዳየጋለጡ ያደርጋል።

አንዳንድ ጥናቶች በተለይም የፕሮስቴት ካነሰርን በመከላከል
ፓፓዬ ወደር እንደሌለው ነው የሚናገሩት።

ለበለጠ ጤና ነክ መረጃ ለማግኘት ፔጃችንን ይወዳጁ. 7564 OK ብለው ይላኩ
1.1K viewsHi, 07:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-15 16:32:58 ሰዉነታችን ከምግብ የምናገኘዉን ስኳር ወደ ሴሎቻችን ገብቶ ሀይል እንድናገኝ የሚያደርገዉ ከቆሺት የሚመነጨዉ ኢንሱሊን የተባለዉ ሆርሞን ነዉ
አንዳንዴ ሰዉነታችን ኢንሱሊን የተባለዉን ሆርሞን በበቂ መጠን ወይም ሙሉ በሙሉ ላያመርት ይችላል
987 viewsHi, 13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-15 16:31:13 የስኳር ህመም ምንድን ነዉ

በደም ዉስጥ ያለዉ የግሉኮስ መጠን ከመደበኛዉ ልኬት በላይ ሲሆን የሚከሰት ነዉ።
956 viewsHi, 13:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-12 12:32:53 ጥሩ እንቅልፍ ለመተኛት በራሳችን ልናደርግ የምንችላቸዉ፡፡

ማድረግ የሚገባ
--------------------
#ቋሚ የመተኛ ሰዓት መመደብ
#ቋሚ የመነሻ ሰዓት መመደብ (አእምሮአችን መደበኛ የሆነ የእንቅልፍ ፕሮግራም እንዲይዝ ያደርጋሉ ፡፡)
#የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ (ጠዋት ጠዋት ቢሆን ይመረጣል )
#እራት በጊዜ መመገብ ( ከመተኛት ሶስት-አራት ሰዓት ቀደም ብሎ )
#መኝታ ክፍልን ብርሀን ያልበዛበት፣ ጸጥተኛና ቀዝቀዝ ያለ ማድረግ

ማድረግ የሌለብን

#አልጋ ላይ ሆኖ ስልክ ማወራት፤ ቻት ማደረግ
#አልጋ ላይ ሆኖ ቲቪ ማየት፣ ሬዲዮ ማዳመጥ
#አነቃቂ ነገሮች አመሻሽ ላይ መጠቀም
#አልኮል መዉሰድ (ለአጭር ጊዜ የሚረዳ ቢመስልም ከጊዜ በኃላ የተቆራረጠ እንቅልፍ ያስከትላል ፡፡)

ከላይ የተዘረዘሩት ቀላል ዘዴዎች ስለሆኑ የማይሰሩ ሊመስሉ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ብዙ የእንቅልፍ ችግር ያለባቸዉን ሰዎች ያለ መድኃኒት ጥሩ እንቅልፍ እንድተኙ ረድተዋል፡፡

ከእንቅልፍ ጋር ተያይዞ ህክምና የሚያስፈልጋቸዉ

-ከላይ የተጠቀሱትን አድርገን አሁንም በቂ እንቅልፍ የማናገኝ ከሆነ
- ተያያዞ የድብርት ስሜት የሚሰማ ከሆነ
-ተያይዞ ጭንቀት ካለ
-በአጠቃላይ የእንቅልፍ ችግሩ በሥራችን ወይም በማህበራዊ ህይወታችንን ላይ ተፅኖ ካሳደረ።
አንድ ሶስተኛ ስንንከባከብ ሁለት ሶስተኛው ላይ የበለጠ ውጤታማ መሆን እንችላለ

ለምን የሙከራ ስራውን ዛሬ አንጀምርም።መልካም አዳር

7564 OK ብለው ይላኩ
1.1K viewsHi, 09:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-12 12:23:46 7564. OK
ብለው በመላክ የጤና መረጃዋዎችን ያግኙ
አገልግሎቱን ሲያገኙ ብቻ 1 ብር የኢትዩፕያ ብቻ ይከፍላሉ ።
763 viewsHi, 09:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-12 12:21:54 የዱባ ፍሬ በሽታ የመከላከል አቅም ይጨምራል
752 viewsHi, 09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-08 16:03:15
788 viewsHi, 13:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ