Get Mystery Box with random crypto!

ያበደው ፍቅሬ ክፍል ከቤት ስወጣ ማንም ያየኝ የለም ለነገሩ ማን ሊያየኝ ይችላል... እንደ | Onli Love ♥️ Story

ያበደው ፍቅሬ

ክፍል

ከቤት ስወጣ ማንም ያየኝ የለም ለነገሩ ማን ሊያየኝ ይችላል... እንደሚሰበር እንቁላል የሚንከባከቡኝን ሁሉ አጥቻለው..... እየሄድኩ ነው....መነሻዬን አስታውሳለሁ መድረሻዬን ግን እንጃ.....

ማሰብና ማስታወስ ቢደክመኝም አይምሮዬ ወደማልፈልገው ጊዜ ሽምጥ ጋለበ.... ወደዛ የሁሉም ነገር ጅማሬ የመከራዬ ሀ ወደሆነው ጊዜ....
........
........
በአንድ አነስተኛ የገጠር ከተማ ውስጥ ከእናቴ ጋር ነበር የምኖረው። አባቴን ገና በልጅነቴ ነው በካንሰር በሽታ ያጣሁት። የልጅነት ጊዜዬን እንደማንኛውም ልጅ በጨዋታ እና በሳቅ ነው ያሳለፍኩት። ምንም እንኳን በቤታችን ብዙ የጎደሉ ነገሮች ቢኖሩም እናቴ ለኔ ደስታ አብዝታ ትደክማለች።

ፓስቲ እና ጠላ በመሸጥ ለኔም ሆነ ለሷ የሚያስፈልጉንን ነገሮች ታሟላለች። ሁል ጊዜም ባይሆንም ችግር እና ረሀብ አልፎ አልፎ ቤታችንን ያንኳኳል፤
እናቴን ሲያማት.....
.....
......

በዛን ሰዓት ምን እንደሆነ ባይገባኝም እናቴን አልፎ አልፎ ከበድ ባለ ሁኔታ ያማት ነበር። አንዴ አሟት ከተኛች ሳምንት እና ከዛ በላይ ያስተኛታል። ሀኪም ቤት እንድትሄድ ደጋግሜ ብጨቀጭቃትም የሁል ጊዜም መልሷ አይሆንም ነው፤ ብያት ብያት እምቢ ስትለኝ በሚያማት ሰዓት ከአጠገቧ ሳልለይ እንከባከባት ነበር።
....
......

ከእለታት በአንዱ ቀን ከትምህርት ቤት ስመለስ በራችንን ተዘግቶ አገኘሁት.... እናቴ በዚህ ሰዓት የጠላ ጣሳዎቿን ደርድራ ፓስቲዋን በርንዳ ላይ እየጠበሰች መገኘት ነበረባት....
.....
በሩን ከፍቼ ወደ ውስጥ ስገባ የሽቦ አልጋዋ ላይ እጥፍጥፍ ብላ ተኝታ አገኘኋት

"እማ ምን ሆነሽ ነው አመመሽ እንዴ?' እጄን ግንባሯ ላይ አድርጌ ትኩሳቷን አየሁ.... በጣም ግላለች

'እማዬ አተኩሶሻል እኮ እባክሽ ዛሬ እምቢ አትበይኝ ሆስፒታል እንሂድ' ከወገቧ ቀና ለማለት ስትሞክር አገዝኳትና ትራሱን ከጀርባዋ አስደገፍኳት....
.....
"አይሆንም ልጄ.... ደግሞ ልሂድ ብልስ በምን ገንዘብ .... ይልቅ መድሀኒት አልቆብኛል ሂጂና ግዢልኝ፤ ይህን ወረቀት ስታሳያቸው ይሰጡሻል...." የሆነች ትንሽዬ ወረቀት ከእጅ ቦርሳዋ ውስጥ አውጥታ ከብር ጋር ሰጠችኝ....
......
..
" በይ ታዲያ መጀመሪያ መክሰስሽን ብይና ነው የምትሄጂው" እሺ ብያት ዩኒፎርሜን ቀይሬ ምግብ አቀረብኩና እምቢ ብትለኝም በግድ እያጎረስኳት ትንሽ አብራኝ በላች።
....
....
ከተማችን ያለው አንድ የመንግስት ፋርማሲ ብቻ ነው። እሱም ለሰፈራችን ራቅ ስለሚል በሩጫ መሄድ ይጠበቅብኛል። የእናቴን ጉንጭ ስሜና ቶሎ እንደምመለስ ነግሪያት እየሮጥኩ ከቤት ወጣሁ
....
....
ነፋሻማው አየር ቀሚሴን ወደላይ እያነሳው እኔም እንዳይገልጠኝ ለመከላከል እየሞከርኩ እየሮጥኩ እያለ አንድ ሰው ስሜን የጠራኝ መሰለኝ። ድጋሚ
" ሚጣ" አለኝ ማነው የጠራኝ ብዬ ዞር ስል ሸክም ከአጠገቡ ያስቀመጠ ጎረምሳ ልጅ እጁን አውለበለበልኝ። አቅጣጫዬን ቀይሬ በፍጥነት አጠገቡ ደረስኩና
' አቤት የሚያሸክምህ አጥተህ ነው አልኩት' ከሁኔታው ሳየው ምኑም የኛን ከተማ ሰው አይመስልም ምናልባት ከሌላ ቦታ ለስራ መጥቶ ይሆናል ብዬ መላ ምቴን አስቀመጥኩ።
...
...
ያልገባኝን ፈገግታ ከለገሰኝ በኋላ "አዎ ሚጣዬ እስኪ አሸክሚኝ" አለኝ።
'የምችለው አይመስለኝም ግን እሺ ልሞክር' አልኩትና ጎነበስ ብዬ ሸክሙን ያዝ አደርኩና ቀና ብዬ አየሁት የማይገባኝን አስተያዬት እያየኝ ነው።
'ምነው መሸከም አትፈልግም እኔ እቸኩላለሁ ለእናቴ መድኃኒቱን መግዛት አለብኝ' አልኩት ቆጣ ብዬ

"አይ እንደዛ አይደለም ይሄን አንቺም ለማሸከም ይከብድሻል እኔም እንጃ የምችለው አይመስለኝም... ውስጥ አነስ ያለ ሌላ ሸክም አለ እንደውም እሱን አሸክሚኝ አይዞሽ አትቆይም" ምላሼን ሳይጠብቅ ፊቱን አዙሮ በጭቃ እየተሰራ ወዳለ ጅምር ቤት ገባ። ዘግዬት ብዬ ተከተልኩትና ወደ ውስጥ ስገባ ዘሎ በጥፊ ደረገመብኝ። ተንደርድሬ መሬቱ ላይ ተደፋሁ.... ለመጮህ አፌን እንደከፈትኩ ፀጉሬን ይዞ አፌ ውስጥ ጨርቅ ጠቀጠቀብኝ።
.....
.....
በመንፈራገጥ እና በድብደባ በዛለ ሰውነቴ ላይ ከላዬ ሆኖ በስሜት ይጨፍራል....
......
ከባድ የሆነ የህመም ስሜት ይሰማኛል........
ቀስ በቀስ በእንባ የራሰው አይኔ መከደን ጀመረ......
ከላዬ ላይ ያለው ሰው ምስል ወደ ብዙ ሰውነት ተቀየረ.......
ከዛ ደግሞ ድብዝዝ እያለ መጣ...... በስተመጨረሻም ድርግም ብሎ ጠፋ..........
........
ጨለማ

ይቀጥላል....
ክፍል 3 እንዲቀጥል አንብባችሁ ስትጨርሱ LIKE ማድረግ አይርሱ እንዲሁም ሼር

@amharicquets
@amharicquets