Get Mystery Box with random crypto!

እናቴ አሪፍና የልብ ጏደኛዬም ናት! (ነበረች አልልም ዛሬም ደምቃ በልቤ ውስጥ ስለምትኖር ) ከ | Yamlumolla

እናቴ አሪፍና የልብ ጏደኛዬም ናት! (ነበረች አልልም ዛሬም ደምቃ በልቤ ውስጥ ስለምትኖር )

ከሚገርመኝ አንዱ:- ፊቴን አይታ ያለሁበትንና የማስበውን ትረዳና እኔን ካረገዘችበት ቀን ጀምሮ ያለውን ታሪክ ፊቷ ደምቆና ፈገግ ብላ ሳትሰለች ትጀምራለች ለመቶኛ ጊዜ መሆኑ ነው [ በጣም የሚገርመው አንድን ታሪክ ስታወራ በጣም አስውባና አሳምራ ነው ምታወራው በዚህ ደግሞ ጏደኞቿና የሚያውቋት ኹሉ ምስክር ናቸው] ብቻ በታሪኩ መጨረሻ ከሚሰማኝ ድብርት ውስጥ ወጥቼ ፣ ተስፋ ተሞልቼ ነበር የማሳልፈው። አይ ማም!

ለምንኛውም እናቴ (ማማ) አሁን በልጄ ገብቶኛል በደንብ የከፈልሽውን ዋጋና ፍቅር! ያንቺንና የሞላዬን እሩቡን ያህል ጥሩ ወላጅ ከሆንኩኝ በእውነት ደስታዬ ወደር አይኖረውም!

እወድሻለሁ! በፍ....ጹም አንረሳሽም! በቅርቡ እስክንገናኝ ይህን ሙዚቃ ፃፍኩልሽ!

Hule Hule is out on all online platforms!! ( Spotify, Apple Music.. )

Watch the full video on YouTube ( link )




#hulehule #mama #zerubabbelmolla #yamlumolla #mothersday