Get Mystery Box with random crypto!

- አብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ሕልው እንደሆነ ፣ ወልድም በአብ በመንፈስ ቅዱስ ሕልው እንደሆነ መ | ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን

- አብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ሕልው እንደሆነ ፣ ወልድም በአብ በመንፈስ ቅዱስ ሕልው እንደሆነ መንፈስ ቅዱስም በአብ በወልድ ሕልው እንደሆነ እናምናለን ይህች ሦስትነት ያለመለየት ያለመለወጥ በሦስት አካላት በአንድ መለኮት የተካከለች ናት ፡፡ 
- አንዲት አገዛዝ አንዲት ፈቃድ አንዲት ሃይል አንዲት መንግሥት አንዲት ስግደት አንዲት ምሥጋና አንዲት ክብር አንድ ጽንዕ ለሥላሴ ይገባል ፡፡ አንዲት ምክር አንዲት ሥልጣን አንድ ክብር አንዲት ጽንዕ አንድ አኗኗር አንድ ፈቃድ ለሥሉስ ቅዱስ ነው ፡፡
  - አብም አብ ነው እንጂ ወልድን መንፈስ ቅዱስን አይደለም ፡፡ ወልድም ወልድ ነው እንጂ አብን መንፈስ ቅዱስን አይደለም ፡፡ መንፈስ ቅዱስም መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ አብን ወልድን አይደለም ፡፡ አብ ወልድን መንፈስ ቅዱስን ወደመሆን አይለወጥም ፡፡ ወልድም አብን መንፈስ ቅዱስን ወደመሆን አይለወጥም መንፈስ ቅዱስም አብን ወልድን ወደመሆን አይለወጥም ፡፡ እሊህ ሦስቱ አካላት በጌትነት በክብር ፍጹማን ናቸው ፡፡ በአንድ መለኮት አንድነትም አንድ ናቸው ፡፡
  - ይኸውም ሦስትነት ከእርሱ የሚገኝ አንድ ብርሃን ነው ፡፡ በዓለሙ ሁሉ መሉዕ ነው ፡፡ ከምድር በታች ላሉትም ያበራል ፡፡ በሰማይ በምድር ምሉ ነኝ እኮ ! በሲኦልም ያሉ ጌትነቱን አዩ ተብሎ እንደተፃፈ ፡፡


ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት 9 ገፅ 23