Get Mystery Box with random crypto!

የቡሄ ፀሃይ '''''''''''''' አንቺ የሳሎን ጌጥ ቢቆጡሽ አባትሽ | የፍቅር ጥቅሶች

የቡሄ ፀሃይ
""""""""""""""
አንቺ የሳሎን ጌጥ
ቢቆጡሽ አባትሽ ከቤት የማትወጪ
እኔ በአመት አንዴ
ሆያ ሆዬ እያልኩኝ ከቤታችሁ መጪ
በነሀሴ ዝናብ
ብቅ የምትይ ፀሀይ ብርሃን አመንጪ
ከእናትሽ ጀርባ
ሙልሙል ዳቦ ይዘሽ ነይ ውጪ ነይ ውጪ!መጪ
አይንሽን እያየሁ
"ቡሄ በሉ" እያልኩኝ ስትይ አ.ፈ.ር ቀና
ምቱ ተዛባብኝ
አፌ ተሳሰረ ግጥሙም ጠፋና።
እናትሽ ታዘቡ
አባትሽ ተቆጡ ወንድምሽ ደነፋ
እኔን ውሀበላኝ
የማረገው አጣሁ መላ ቅጤ ጠፋ።

ብቻ እዘማምራለሁ

"ቡሄ በሉ.....ቡሄ በሉ
ይቺን ቆንጆ ለእኔ በሉ
እኔም ላቁም መስለምለሙ
እሷም ትተው መሽኮርመሙ

እዛ ማዶ ጭስ ይጨሳል
እዚ ማዶ ልቤ ጨሷል
የሷን ፍቅር ይፈልጋል
አል'ያ ግን ጨሶ ያልቃል

ድምፅዋን ብሰማ
ብሩህ ነው ቀኔማ"

ብዬ እንኳን ሳልጨርስ መዘማመሬን፤
አባቷ ደቆሱኝ በዱላ ጎኔን።
ከቀልብያ ሆኜ ሳልጀምር እሩጫ፤
ዋልጌ ነህ እያለ
ይነግረኝ ነበረ የእናቷ ግልምጫ።
አቤት የወንድሟ
በእኔ ግጥም ስንኝ በብስጭት ናውዞ፤
ካልገደልኩት ይላል
በአገላጋዮች ተከቦ ተይዞ።

ምን አለ ፈጣሪ
ከቤቷ በረንዳ እሷን እያየሁኝ
ከሙልሙሉም ዳቦ እየገማመጥኩኝ
እሷ ፈገግ ብላ እኔ እየጨፈርኩኝ
አመቱን በሙሉ ሆ እያልኩኝ በኖርኩኝ !!

እንኳን አደረሳችሁ

Join & Share

@yabutiiiiiiiiiiiii
@yabutiiiiiiiiiiiii