Get Mystery Box with random crypto!

* እኔኮ ስወድሽ * ፡ እኔኮ ስወድሽ ቃላት ይደክማሉ፣ ፊደላት ሰልለው ድጋፍን ይሻሉ፣ ፡ ምን | የፍቅር ጥቅሶች

* እኔኮ ስወድሽ *


እኔኮ ስወድሽ ቃላት ይደክማሉ፣
ፊደላት ሰልለው ድጋፍን ይሻሉ፣

ምን ቃል አለኝና ፍቅሬን ነግርሻለሁ፣
በልቤ ወድጄሽ ለፍቅርሽ ሞቻለሁ፣

አንቺን መተው ለኔ ይገርምሻል ውዴ፣
ከሞት ከቶ አያንስም እወቂው እንግዴ፣

አረ እንደውም መሞት ሳይሻል አይቀርም፣
የማፍቀር ሰቀቀን ጠባሳው አይሽርም፣
የናፍቆትን እከክ ጥፍር አያከውም፣
የመውደድን መሞት አይኖች አያዩትም፣

እናምልሽ ውዴ እራቀኝ ስትዪኝ፣
በቁም ሳለሁ በድን እንደሆንኩ እወቂኝ፣

በፍቅርሽ ሰንሰለት እግረ ሙቅ ታስሬ፣
አቅም የተቀማሁ የማልቆም ዳክሬ፣
የመከነ ልፋት ሰርክ ምድርን ዞሬ፣
የድጋይ ላይ ተክል የማይበዛ ዘሬ፣
እንዲ ነኝ አለሜ ካጣሁሽ አፍቅሬ፣

ዓሳ ከውሃ ወጥቶ ይኖር ዘንድ እንዳይችል፣
ንስር ምድር ወርዶ እንደማይሄድ ቁልቁል፣
እየተገረፈ እንደማይድን ቁስል፣
ለመርዶ ነጋሪ እንዳይባል እልል፣
እኔም አንቺን ካጣሁ ፍቅሬ ይከብደኛል፣

እኔኮ ስወድሽ ከገደቡ አልፌ፣
ጧት ማታ ሳልምሽ መውደድሽን ታቅፌ፣
ሌላ ምንስ አለኝ ፍቅርሽ ነዋ ትርፌ፣
ልተውሽ አልችልም ልቤ ላይ ሸክፌ፣

ውሰጂው ያለኝን ልሁን ነጭ ደሃ፣
ወይኑንም ተጎንጪ ለኔ ደሞ ውሃ፣

ከጮማው ቁረጪ አማርጪ ያሻሽን፣
እኔ ውዬ ልደር እየራበኝ ጦሜን፣

ላንቺ ነው

Join & Share

@yabutiiiiiiiiiiiii
@yabutiiiiiiiiiiiii