Get Mystery Box with random crypto!

Living Dream

የቴሌግራም ቻናል አርማ ww1dreamers — Living Dream L
የቴሌግራም ቻናል አርማ ww1dreamers — Living Dream
የሰርጥ አድራሻ: @ww1dreamers
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 806
የሰርጥ መግለጫ

✌️Welcome to our Telegram chanel❣️
🙏የዝህ chanel ዋነኛ አላማ፦
❤ መካርና አስተማሪ የሕይወት እውነታወችን
🧠የሥነ ልቦና ምክሮችን
🧠አነቃቂ ፅሑፎችን
🧠ጥቅሶችንና አባባሎችን
🧠 ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎችን..
ለበለጠ መረጃ ይቀላቀሉን 👇
More👉 @WW1DREAMERS

ለ አስተያየት ጥቆማ @Dova57

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-12 21:23:23
@ww1dreamers
307 views18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 08:59:16 ስኬታማ_የሆኑ_ሰዎች_7_ልምዶች

ከአስራ አምስት ሚሊዮን ቅጂ በላይ ተሽጧል፤ በሰላሳ ቋንቋዎች ተተርጉሞም ለንባብ በቅቷል፤ በእኛው አማሪኛ ቋንቋም ተተርጉሞ መታተሙንም አውቃለሁ፡፡ ይህ መጽሐፍ “The 7 Habits of Highly Effective people” ይባላል:: “እጅግ በጣም ስኬታማ የሆኑ ሰዎች 7 ልምዶች” ብለን ቃል በቃል እንተርጉመው፡፡ የመጽሐፉ ደራሲ ስቴቨን ኮቬይ ይባላል፡፡ ይህ መጽሐፍ በግለሰብ ደረጃ እድገትን (Personal development) ለመፍጠር እንዲረዱ ታስበው እስከ ዛሬ ድረስ ከተጻፉ መጽሐፍት መካከል ወደር የማይገኝለት ነው፡፡ ካላነበባችሁት እንድታነቡት እመክራለሁ፡፡ ያነበብነውም ደግመን ልናነበው ይገባል የሚል እምነት አለኝ፡፡

የዚህ ድንቅ መጽሐፍ ደራሲ ስቴቨን ኮቬይ “ውስጣዊ ድል ከውጫዊ ድል ይበልጣል” ይላል፡፡ እዚህ ምድር ላይ ማግኘት የምንፈልጋቸውን ነገሮች በሙሉ ለማግኘት አስቀድመን ራሳችንን ማሸነፍ፤ የህይወታችን ሾፌር መሆን፤ ውስጣዊ ማንነታችንን መቆጣጠር ወዘተ አለብን ማለት ነው፡፡ “ከተማን ከሚመራ ሰው ይልቅ ራሱን የሚመራ ሰው ይበልጣል” ይላል ጠቢቡ ሰለሞን፡፡ ራስን ማሸነፍ ሌሎች ውጫዊ ነገሮችን የማሸነፊያ ቁልፍ ነው፡፡ በመቀጠል በቅደም ተከተል የምንመለከታቸው 7 ልምዶች ማንኛውም ሰው የግል ህይወቱ መሪ እንዲሆን በእጅጉ የሚያግዙ ናቸው፡፡ አሁን ቦታውን ለእነዚህ ልምዶች ለቀቅ እናድርግ እስኪ፡፡

1. ኃላፊነት ውሰዱ

ጅብ ከሄደ በኋላ የውሻ መጮህ ምንም ውጤት አያመጣም፤ ትርፉ ድካም ነው፡፡ ውጤት የሚያመጣው ጅቡ ከመምጣቱ በፊት አስቀድሞ በማነፍነፍ ድምጽ ማሰማት ነው፡፡ ሁኔታዎችን፣ ሌሎች ሰዎችን፣ ዓለምን ወዘተ የሚወቅሱ ሰዎች በህይወታቸው የረባ ቁም ነገር አያከናውኑም፤ ሁልጊዜም ኃላፊነትን የሚያሸክሙት ከእነሱ ውጪ ላለ ሌላ አካል ነው፡፡ ኃላፊነትን መሸከም ስንችል ነው የህይወታችንን ጉዞ አቅጣጫ መወሰን የምንችለው፡፡ የተሸከርካሪውን መሪ ለሌላ አካል አሳልፈን ሰጥተን የምፈልገው ቦታ አይደለም የደረስኩት፤ በፈለኩት ፍጥነት አይደለም እየተጓዝኩ ያለሁት ወዘተ ልንል አንችልም፤ ብንልም ዋጋ የለውም፡፡ የጉዞውን አቅጣጫ፣ ፍጥነት እና አድራሻ የሚወስነው አሽከርካሪው ነው፡፡ ልምዳችን መውቀስ፣ ጣት መጠቆም፣ ራስን መከላከል ወዘተ ከሆነ እውነቱን ለመናገር የሚወቀስ ነገር ማግኘት አይከብድም፡፡ ዘወትር የእናቴ መቀነት አደናቅፎኝ ነው ማለት ህይወታችን ባለህበት እርገጥ እንዲሆን በር ወለል አድርጎ ይከፍታል፡፡ ስለዚህ ለውጥ ለማምጣት፣ የራሳችን ሰዎች ለመሆን፣ ውስጣችንን ድል ለማድረግ ወዘተ ሁልጊዜም ለገዛ ራሳችን ህይወት ሙሉ ኃላፊነት እንውሰድ፡፡ ቃላችንን የምናከብር፤ በአልንበት ቦታ የምንገኝ፤ በገዛ ራሳችን ጥረት የምንፈልገውን ማንኛውንም ዓይነት ነገር እጃችን ለማስገባት መጓዝ ያለብንን ያህል ርቀት መጓዝ የምንችል ሰዎች እንሁን፡፡ “ስራ እኮ ጠፋ! እኔ ምን ላድርግ?!” ከማለታችን በፊት ስራ ለማግኘት የምንችለውን ድንጋይ በሙሉ መፈንቀላችንን እርግጠኛ እንሁን፤ ቀጣሪዎች የሚፈልጉትን ዕውቀት እና ክህሎት ይዘን ለመገኘት ጥረት እናድርግ፤ የተለመደውንም ያልተለመደውንም አማራጭ እንፈትሽ፡፡ ሳይኮሎጂስቶች “Life is 10 % what happens to us and 90 % how we react to it” ይላሉ፡፡ የህይወታችንን አብዛኛውን (90 %) ክፍል በምንፈልገው መልኩ መስራት እንችላለን ማለት ነው፡፡ የምናጭደው የዘራነውን ነው፡፡

2. የምትፈልጉትን ነገር አስቀድማችሁ እወቁ

ስቴቨን ኮቬይ “ነገሮች ሁለት ጊዜ ይፈጠራሉ” ይላል፡፡ የመጀመሪያው ፈጠራ የሚጠናቀቀው አእምሮአችን ውስጥ ነው፡፡ ከቤት ከመውጣታችን በፊት የምንሄድበትን ማወቅ ይኖርብናል፡፡ ከአንድ እና ሁለት፣ አምስት እና አስር ዓመት ወዘተ በኋላ ምንድን ነው ማግኘት፣ ማድረግ፣ መሆን ወዘተ የምንፈልገው? ለእነዚህ ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ መስጠት ነገሮቹ በተጨባጭም ወደ ህይወታችን የሚመጡበትን ዕድል ከፍ ያደርጋል፡፡ “We rise to the level of our expectations” ይባላል፡፡ የምናገኘው የምናስበውን ነው፤ የምንደርሰው እንደርሳለን ብለን የምናስበው ከፍታ ድረስ ነው፡፡ ግባችንን ማወቃችን ትኩረታችንን ለመሰብሰብ ይረዳናል፤ ከነፈሰው ጋር አንነፍስም፤ በፈተና መካከል ጸንተን እንቆማለን፡፡ ሳይኮሎጂስቶች የህይወታችንን ግብ በቅጡ ለመለየት የሚረዳን አንዱ ሁነኛ መንገድ “የቀብራችን ዕለት እንዲነበብ የምንፈልገውን የህይወት ታሪካችንን መወሰን ነው” ይላሉ፡፡ ቁጭ ብለን ልናስብበት ይገባል፡፡

3. ቅድሚያ ለሚገባቸው ነገሮች ቅድሚያ ስጡ

“ሁሉ አማረሽን ገበያ አታውጧት” ይባላል፡፡ ቅድሚያ መስጠት ላለብን ነገሮች ቅድሚያ መስጠት አለብን፡፡ ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ ላይ አይወጣም፡፡ ኮቬይ እንዲህ ይላል፡- “ራሳችሁን ከእነዚህ ሶስት አጉል ልምዶች በአንዱ መውቀስ ቢኖርባችሁ በየትኛው ነው የምትወቅሱት? (1) መስራት ያለብኝን ነገር በቅደም ተከተል መለየት አልችልም፤ (2) በአስቀመጥኩት ቅደም ተከተል መሰረት መስራት አልችልም፤ (3) በወሰንኩት ቅደም ተከተል መሰረት ለመስራት አስፈላጊው ቁርጠኝነት የለኝም፡፡ ብዙ ሰዎች ቁርጠኝነቱ የለኝም ነው የሚሉት፡፡ ጠለቅ ብለን ከመረመርነው ግን እውነቱ ሌላ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ እውነቱ ቅደም ተከተሉ ውስጣችን በጥልቀት አለመስረጹ ነው፡፡ ልምድ 2ን ማለትም የህይወት ግባችንን አስቀድመን በሚገባ ለይተን በሚገባ ውስጣችንን መቅረጽ አለመቻላችን ነው”::

4. በጋራ እኩል ተጠቃሚነት መርህ ተመሩ

ከተቃራኒ ፆታ ጀምሮ እስከ የንግድ ስራ ግንኙነት ድረስ በጋራ እኩል ተጠቃሚነት መርህ መመራት ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ “አዎ! በሚገባ አምንበታለሁ፡፡ በእኩል ተጠቃሚነት መርህ ነው ህይወቴን የምመራው፡፡” ትሉ ይሆናል፡፡ እንደምትሉት እንደምትኖሩ ግን እርግጠኛ ሁኑ፡፡ ለማሸነፍ ከመጣር ይልቅ እንዴት በጋራ እኩል ተጠቃሚ ለመሆን ጥረት አድርጉ፡፡ የበለጠ ተጠቃሚ ለመሆን፣ ከሌላው ከፍ ብሎ ለመታየት፣ ልክ ሆኖ ለመገኘት ወዘተ ከመጨነቅ ይልቅ በጋራ እኩል እንዴት ተጠቃሚ መሆን እንደሚቻል ማሰብ እና ይህንን መርህ በየትኛውም የግንኙነታችን መረብ ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ ይበልጥ ውጤታማ ያደርገናል፡፡

ይቀጥላል

Source: from psychologist

@ww1dreamers
@ww1dreamers
323 views05:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 13:33:54
greatings be safe and keep going on wish you gratefulness @ww1dreamers
322 views10:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 13:26:05
Creating the dream is living the dream, and constantly being able to take one more step, even when that step looks too difficult to take, even when we think we may fall too far, or too hard, even when we know it'll mean going against the convention of what the people around us are doing, taking one more step keeps us ...
298 views10:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 23:38:00
Living the dream means that someone is living his best life; that he is achieving the goals he wants to achieve; that he has all the material comforts and/or relationships that he wants to have. The expression living the dream came into us when we began taking action that facilitates our dreams at least one step forward and making that our disciplines , which is the belief that prosperity, freedom, and success is available to all who work to live dreams practically

@ww1dreamers
296 views20:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 23:21:25 ሰላም ሰላም ዉድ የቻናላችን ተከታታዮችና ቤተሰቦች በሙሉ
የቻናሉን ስም( Title) አንዳንዳችሁ እንደ commentም በሰጣችሁኝ መሠረት Dream ብቻውን በቂ አይደለም ማለትም በእውን (በተግባር) ህልማችንን መኖር መቻል አለብን፤ ላልታለመ ህልም ፍቺ እንደማይፈለገው ሁሉ መጀመርያ ህልም (ራዕይ) ልኖረን ይገባል ያንኑ ህልማችንን ወደ ፍፃሜ የምያፈጥኑልንንና ህልማችንን ወደ ተግባር ለመቀየር የምያስችሉንን ልምምዶችን Discipline ማድርግ አለብን፤ ያኔ Really ህልማችንን መኖር እንጀምራለን ህልማችንን በተግባር ስንኖራቸው በህይዎታችን ደስተኛ እንሆናለን ህይወትን ሳንሰለቻት እናጣጥማታለን ካልሆነ ቅጀት ብቻ ሆኖ ህይዎት ባዶ ትሆለች መኖር አሰልቺ ሆኖ ተስፋ እንቆረጣለን።ስለዝህ ህልማችንን መኖር እንጀምር

ህልምን መኖር
@ww1dreamers
293 views20:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 22:52:22 #ውስጣዊው #ሰው

ባንተ ውስጥ ያንቀላፋ ምንም ነገር ማድረግ የሚችል ጀግና ሰው አለ፡ይህ ጀግና ገራሚ ሐይል ነው፡ይህንን ሐይል ማድመጥ ጀምር፡የስንፈናን አቅምና ሐይል ከውስጥህ ነቅሎ ይጥለዋል፡፡

ሰነፉ ማንነትህ ፈሪ ነው፡ ጀግናው ማንነት #አማኝ ነው፡፡
ሰነፉ ማንነትህ ሰነፍ ነው፡ ጀግናው ማንነትህ #ለፊ ነው፡፡
ሰነፉ ማንነትህ "ሰው ምን ይለኛል?" ይላል፡ ስህተት ይፈራል፡ ፍጹም መስሎ ለመታየት ይሞክራል፡፡

ጀግናው ማንንትት ግን "እኔ ራሴን ምን እላለሁ? ፈጣሪስ ምን ይለኛል?" ይላል ፡ፍጹም መስሎ የመታየት ምኞት የለውም፡፡እሱ የህይወት ዘመን ተማሪ ነው፡ ሰነፉ ማንነትህ ጊዛዊ ደስታን ብቻ ይፈልጋል፡ ጀግናው ማንነትህ ግን ረጅሙን የውስጥ ሰላም፣ ፍቅር፣ ወሳጣዊ ደስታና ስኬት ይሻል።#ይህ ጀግናው ማንነት = ውስጣዊ ማንነትህ ነው

ሰነፉ ማንነት =ውጫዊው ማንነትህን ይወክላል፥ ማየት ፤መታየት፤ ፍረሀት፤ማስመሰል፤የማይፀናና የሚናወጥ መንነትህ ነው ይህ ፈርው መንነትተህን አትስማው
#ውስጥህ ያለውን ሰው አድምጠው ጀግናው ማንነትህን መኖር ጀምር ፤ መሆን የምትፈልገውና የሆንከው የተለያዩት፣ መኖር የምትፈልገውና አሁን የምትኖረው ህይወት ያልተገናኙት፣መሄድ የምትፈልገው ጎዳናና አሁን የቆምክበት ቦታ የተራራቁት፣ እርግጠኛ ሁኜ የምነግርክ በውስጥህ ያለውን ጀግና ማንቃት አልቻልክም።ውስጥህን አድምጠው በገደል ጫፍ ላይ ቆማ በየግዜው ንፋስ ወደገፋት አቅጣጫ እንደምታጎነብስ ዛፍ አትሁን ሰው ስላደረገው ወይንም ባጋጣሚ ጎረቤት ጓደኛ ሰለመከረህ ብቻ፣ ወደዛ አታዘምብል ምክንያቱም ይሄንን አጋጣሚ ጉዞ ሌላ አጋጣሚ ልገታብህ ይችላል።

ውስጥህ ያለው ሌላ የምትኖረው ሌላ፤ ራዕይክ ዓላማክ ሌላ አንተ የምትሆነው ሌላ አሁን ራስህን መጠየቅ ጀምር???
???ለምን?? ??

ድንቅ ምሽት ተመኜሁ
በቅንነት #ሼር ያድርጉ


@ww1dreamers
@ww1dreamers
449 views19:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 22:52:02
@ww1dreamers
301 viewsedited  19:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 13:26:09 ..............................................................continuation of the earliers
........3
. Make Every Step Fun

So many of us have been taught that with enough hard work anything is possible. But this idea leaves out something very important: the people who truly reach their dreams, especially in the biggest ways, have fun along the way. If you do what feels good then you will feel happier. When you feel happier, you are more inspired. Find what makes you feel good and focus on it, because feeling happy and inspired every step of the way is key. As you let go of the old belief that success has to be hard, you see life becomes happier and easier. You won’t need will power because you are driven with happy inspiration and you will be excited to get the next step of your work done! As you make fun and happiness a priority, you will notice wonderful shifts, and creating your dreams in very big ways will become easier than you were ever led to believe.

Funny move

@ww1dreamers


Continue reading active..............
350 views10:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 23:41:18 ከዕለታት አንድ ቀን ህጻን ቶማስ ኤዲሴን ከትምህርት ቤት ወደ ቤቱ ተመለሰ። ለእናቱ «እማየ ፣ ይህን መልዕክት ላንቺ እንዳደርስ ከመምህራችን የተሰጠኝ ነው» በማለት በእጁ የያዘውን ወረቀት ሰጣት። ወረቀቱ ላይ የሰፈረውን ፅሁፍ ስታነብ አይኖቿ እንባ አቀረሩ። ለህጻኑ ቶማስ ኤዲሰንም መልዕክቱ «ልጅሽ የምጡቅ አይምሮ ባለቤት ነው፤ ስለሆነም የኛ ትምህርት ቤት ከርሱ አቅምና ብቃት አንጻር የሚመጥነው ባለመሆኑ በቤት ውስጥ አስተምሪው» ይላል በማለት አነበበችለት። እናት ልጇን በራሷ ስልት በቤት ውስጥ ማስተማር ጀመረች። ራሱም በራሱ እንዲማር አተጋችው፡፡ ጊዜዋን ሰውታ ከርሱ ጋር ሌት ከቀን በማሳለፍ አበረታችው፡፡

ዓመታት አለፉ። የቶማስ ኤዲሰን እናት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች። ህጻኑ ቶማስ ኤዲሴን የህይወት ፈተናዎችን ተጋፍጦ የወጣነት የዕድሜ እርከን ላይ ደረሰ። ለአገሩ አሜሪካና ብሎም ለዓለም ብዙ የፈጠራ ትሩፋቶችን አበረከተ። በሰው ልጅ ታሪክ የመጀመሪያውን የኤሌክትሪክ አምፑል «ፈጣሪ» ሆነ። ዓለምን ከ«ጨለማ» ወደ «ብርሃን» አሸጋገረ። የሰው ልጅ ከኩራዝ ብርሃን ወደ ኤሌክትሪክ ብርሃን እንዲተዋወቅ መሸጋገሪያ ድልድይ ፈጠረ።

አንድ ቀን ቶማስ ኤዲሰን የእናቱን ሳጥን እየፈተሸ ሳለ አይኖቹ ከአንዲት ወረቀት ላይ ተተክለው ቀሩ። ወረቀቱን አንስቶ በውስጡ የያዘውን መልዕክት ሲያነብ ክው አለ። ወረቀቱ ላይ የሰፈረው ጽሁፍ «ልጅሽ ቂልና የማይገባው ዘገምተኛ ነው፤ ከነገ ጠዋት ጀምሮ ወደ ትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ፈጽሞ አናስገባውም» የሚል ነበር። ቶማስ ኤዲሰን ለብዙ ሰዓታት በእንባ ጎርፍ ታጠበ። ይህች ወረቀት ቶማስ ኤዲሰን ህጻን እያለ ከመምህሩ ለእናቱ እንዲያደርስ የተሰጠው ወረቀት ናት። እናት የልጇን ስሜት ላለመስበር ጽሁፉን ያነበበችው በተቃራኒው ነበር ።.

ቶማስ ኤዲሰን ወረቀቷን ካነበበ በኋላ በማስታወሻው ላይ «ኤዲሰን ሞኝ እና የማይረባ ህጻን ነበር ፤ ግና ውድ በሆነች እናቱ እገዛ የምጡቅ አይምሮ ባለቤት ሊሆን ቻለ» በማለት አሰፈረ ።

በቅንነት ሼር አድርጉ
496 views20:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ