Get Mystery Box with random crypto!

ሰኔ 16፣ 2014 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽን በምዕራብ ወለጋ | አለምአቀፍ እውነታዎች ™

ሰኔ 16፣ 2014

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽን በምዕራብ ወለጋ ቶሌ ቀበሌ የተገደሉ ንጹሃንን በተመለከተ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ ጠየቀ፡፡

የዩ.ኤ.ን የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽን ቢሮ ዛሬ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ስለተገደሉበት ጥቃት በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ ጠይቋል፡፡

ቢሮው የዓይን እማኞችን ማነጋገሩን በመግለጫው ጠቅሷል፡፡

በዚህም መሰረት የታጠቁ ቡድኖች ባለፈው ቅዳሜ ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ የአማራ ተወላጆች በሚኖሩበት ቶሌ ቀበሌ በመገኘት ፤ እንዳገኙ በመደዳ በመተኮስ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃንን እንደገደሉ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

ከሟቾች መካከል አብዛኞቹ ሴቶችና ህፃናት ናቸው የተባለ ሲሆን ሌሎች 2 ሺህ ያህሉ ደግሞ ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸውን ቢሮው ጠቅሟል፡፡

የተፈፀመው ትርጉም አልባ ግድያ በጣም አሰቃቂ ነው ያለው ቢሮው ነዋዎች ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸው ተገቢ አይደለም ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በገለልተኛ አካል ጉዳዩ እንዲጠና እንዲያደርጉና ተጠቂዎችም ስለ ቤተሰቦቻቸው ተገቢውን እውነት እንዲያውቁ እንዲሁም ፍትህ እንዲያገኙ እንዲደረግ ጠይቋል፡፡

በቁጥር ምን ያህል እንደሆኑ ያልታወቁ ሰዎች አድራሻቸው መጥፋቱን የጠቀሰው ቢሮው እስካሁን የት እንዳሉ እንደማይታወቅ ተናግሯል፡፡

ይሄን በተመለከተም በህጋዊ መንገድ ተጣርቶ የተሰወሩ ሰዎች የት እንዳሉ እንዲረጋገጥ እና ነፃነታቸውም እንዲመለስላቸው ሲል የተባበሩት መንግስታት የከፍተኛ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ ጠይቋል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

#Ethiopia #ShegerWerewoch #United_Nations
#ቶሌ_ቀበሌ