Get Mystery Box with random crypto!

አርጀንቲና በሳውዲ 2ለ1 ስትሸነፍ ከትልልቆቹ እስከ ትንንሾችሁ ድረስ አርጀንቲና ተችቶ ሳውዲ አረቢ | የእውቀት ማዕድ ™

አርጀንቲና በሳውዲ 2ለ1 ስትሸነፍ ከትልልቆቹ እስከ ትንንሾችሁ ድረስ አርጀንቲና ተችቶ ሳውዲ አረቢያን ሲሞግስ ነበር።

አብዛኛውን ሰው #ዳቦ ሊጥ ሆነ! በሚል ስሜት የአርጀንቲና ቡድንን ጥቅም አልባነት ተናግሯል። በተቃራኒው የሳውዲ ቡድን ኃያልነት በሰፊው ተዘግቧል። የሳውዲ ደጋፊዎች #መሲ የታለ?! ብለው አላግጠዋል።

የሳውዲ ንጉሳዊ ቤተሰብ የብሔራዊ ቡድናቸውን አጀማመር በጣም ተደስተው ለእያንዳንዳቸው አዲስ ሞዴል ማርቼዲስ መኪና ሰጧቸው።

የሳውዲ አረቢያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሄርቭ ሬናርድ ግን እንዲህ ብሎ ነበር! "አርጀንቲና( ) የኳታር የአለም ዋንጫ ፍፃሜውን በዚህ ጊዜ ትጫወታለች" ብዙ ሰዎች ይህን ሰምተው ሳቁበት!!

ሊዮኔል ሜሲም ከሳውዲ አረቢያ( ) ሽንፈት በኋላ ለሀገሩ ህዝቦች እና ለደጋፊዎቹ "ለደጋፊዎቼ የማስተላልፈው መልእክት እምነት እንዲኖራቸው ነው!!" ("We won't leave them stranded!") እንዳለውም እምነቱን ምን ጠንካራ መሆኑን በተግባር በማሳየት በቀጣይ ጨዋታዎች ዓለም ሁሉ የሰው ደጋፊ ሆኗል።

በህይወታችን ችግር ሲያጋጥመን ትተን ፊታችንን መመለስ ሳይሆን እምነታችንን በማጠንከር ወደፊት መጓዝ ነው።
ማሸነፍ የምንፈልግ ከሆነ በጥንካሬ እስከመጨረሻው መጓዝ አለብን

ሰዎች አበቃላቸው ቢሉም____የፈለጉትን ቢያወሩም እኛ ግን በራሳችንን ካመንና ተስፋ ካልቆረጥን ከምርም ያሰብንበት እንደርሳለን።

ዛሬ የአርጀንቲና ዋንጫ መብላት ተስፋ ያልቆረጠው የመሲ እና የብሔራዊ ቡድኑ ውጤት ነው። ዛሬ የአርጀንቲና ዋንጫ መብላት ተስፋ ያልቆረጠው የመሲ እና የብሔራዊ ቡድኑ ውጤት ነው።

ምትሀተኛ እያለ ዓለም ስሙን የሚያነሳው መሲ በዓለም ላይ ሁሉንም የዋንጫ ዝርያ በማንሳት ተዓምር የሰራበት የዓለም ዋንጫም ነበር።