Get Mystery Box with random crypto!

#ኮኖሱኬ ማትሱሺታ+++ ጃፓናዊ ነው! (#Panasonic) እኤአ 1894-1989 የኖረ++ከምንም | የእውቀት ማዕድ ™

#ኮኖሱኬ ማትሱሺታ+++ ጃፓናዊ ነው! (#Panasonic)

እኤአ 1894-1989 የኖረ++ከምንም ተነስቶ ግን ከኤሌክትሪክ መሰኪያ አሳብ እና በዓለም ዙሪያ የሚታወቅ ትልቅ የቢዝነስ ድርጅት በማቋቋም ችሏል።

በጃፓን ውስጥ በምትገኝ ትንሽ የገጠር መንደር ውስጥ ከደሃ ቤተሰብ ነው የተወለደው። ቤተቦቹ እሱን የማስተማር አቅም ስላልነበራቸው ገና በ9 አመቱ ትምህርቱን አቋርጦ ቤተሰቡን ለመደገፍ በአንድ ትንሽ ሱቅ ውስጥ በፅዳት ሰራተኝነት ተቀጠሮ መስራት ጀመረ።

ከትንሽ  ጊዜ በኃላም በ አንድ የኤሌክትሪክ እቃዎችን በሚያመርት ድርጅት ውስጥ በቋሚነት ተቀጠረ። የአንፓልና ሶኬት ስራ ትኩረቱን ይስቡት ነበርና በየቀኑ ራሱን ያስተማርና ይመራመር ነበር። ሶኬትን ከቀድሞው አሻሽሎ መስራት ቢችልም በአሰሪው ድርጅት ተቀባይነት አላግኘም። "የማይረባ ስራ ነው።" ሲሉም አጣጣሉት። እሱ ግን በስራው እርግጠኛ ነበርና  የራሴን ድርጅት መመስረት አለብኝ ሲል አሰበ።

ሃሳቡን ለጓደኞቹ አጫወታቸው "አንተ ትምህርት አልተማርክም፣ልምዱም የለህም፣ ገንዘብም የለህም። ውጤታማ ለማትሆንበት ስራ ብለህ ቋሚ የሆነውን ስራህን ባትተው ነው የሚሻልህ ይህን የእብድ ሃሳብህን ተው።" ሲሉ ተሳለቁበት።

የተማረ ባይሆንም፣ ገንዘብ ባይኖረውም በራሱ ይተማመን ነበርና በ22 አመቱ የህይዎቱ ትልቁን ውሳኔ ወሰነ። በቋሚነት ከሚሰራበት ድርጅት ለቆ በትንሿ ቤቱ ውስጥ የእራሱን ድርጅት መሰረተ። ከሚስቱ ጋር በመሆንም አሻሽሎ የሰራውን ሶኬት በማምረት ቤት ለቤት እየዞሩ ለመሸጥ ሞከሩ ነገር ግን ቀላል አልሆነለትም። አንድም የሚግዛውም አላግኘም። ወራቶች አለፉ ትዕዛዝ የሚሰጠውም ሆነ የሚገዛው ሊገኝ አልቻለም። የእለት ምግብ እጥተው የቤት እቃዎቻቸውን ሁሉ እስከመሸጥ ደረሰ። ህልሙን ፅልመት ሊውርሳት በተቃረበበት ወቅት አንድ ድርጅት 1000 ሶኬቶችን እንዲሰራ ትዕዛዝ ሰጡት።

ከዛሬ 100 አመት በፊት በ1000 ትዕዛዞች የተጀመረው ድርጅት ዛሬ ላይ ከ250,000 በላይ የሚሆኑ ሰራተኞች ያሉት ትልቅ ድርጅት ለመሆን በቅቷል።  በ አመት 65 ቢሊዮን ዶላር ከሽያጩ ገቢ የሚያገኝ ድርጅትም ሁኗል።

ይህን ስኬት ያለምንም ትምህርትና ገንዘብ ማሳካት የቻለው ታላቅ ሰው #konosuke Matsushita ይባላል። በትንሽ ቤት ውስጥ የተመሰረተው አሁን በመላው አለም ታዋቂና ብዙ ቅርንጫፎች ያሉት የ #panasonic company ባለቤት ነው።
ምንጭ:
#electro-space academy