Get Mystery Box with random crypto!

ግንቦት 07/2014ዓ.ም በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ከወጣቶች ጋር ውይይት ተደረገ !! የኮ/ቀ/ክ | Kolfe Prosperity party 01 Youth League

ግንቦት 07/2014ዓ.ም

በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ከወጣቶች ጋር ውይይት ተደረገ !!

የኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር ወጣቶች ሊግ ‹‹ ጽንፈኝነትን በመታገል ሃገራዊ አንድነትን እናጠናክር›› በሚል መሪ ቃል በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ከወጣቶች ጋር ውይይት አደረገ !!

በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር ስር ከሚገኙ ወጣቶች ጋር በዘሬው ዕለት ሀገራዊ አንደነትን ፤ ሃገረ-መንግስት እና ብሄረ-መንግስት፤ በኢትዮጵያ ሀገራዊ አንድነትን ማጎልበት እና ተግዳሮት፤ ሀግራዊ አንድነት በብልጽግና የወጣቶች ሚና ምን መሆን እዳለበት የወረዳ 01 አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ #አቶ_አየለ_አለባቸው እና የብልጽግና ወጣቶች ሊግ ሰበሳቢ #አቶ_የቻለው_አላምር ወቅታዊ እና ሃገራዊ ሁኔታ የደሰሰ የመወያያ ሰነድ ቀርቧል።

በመነሻ ሃሳቡ ወጣቶች ያነሷቸው ጥያቄ ከስራ እድል ፈጠራ፤ የሰላም እና የጸጥታ ጉዳይ ወጣቶች አልባሌ ቦታ እንዳይውሉ፤ መሰራት እንዳለበት ያመላከቱ ሲሆን፤ መንግስት በርካታ ስራዎች እየሰራ እንዳለ እና አሁን የወጣቶች ሚና ብዝሃነትን በማክበር ራስን ከብሄር እና ከሃይማኖት ፅንፈኝነት ነጻ ማድረግ፤ የወንዳማማችነት እና የእህትማማችነትን አሰተሳሰብ ማጎልበት፤ ምክንያታዊነት የተላበሰ በእውቀት የተመሰረተ የውይይት ባህል ማሳደግ ፤ህግ እና ስርዓትን በማስከበር ሀገራዊ ሰላምን ማስጠበቅ ፤በበጎ አድራጎት ስራዎች ላ ይ ተሳትፎ ማድረግ እዲሁም ወጣቶች የህልውና ዘመቻው ላይ የነበራቸውን ከፍተኛ ተሳትፎ አሁንም በሚኖራቸው ሀገራዊ ሚና እንዲወጡ በውይይቱ ለማየት ተችሏል፡፡

የዜናው ምንጭ ኮልፌ ወረዳ 01 አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት
መረጃዎቻችንን በአማራጭ ለማግኘት ከታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ:-
የቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/woreda01youthleague
በፌስቡክ: የኮሚኒኬሽን https://www.facebook.com/profile.php?id=100031500227693
የብልፅግና ወጣቶች ሊግ ፌስቡክ:-https://www.facebook.com/profile.php?id=100076300563488
የብልፅግና ወጣቶች ሊግ ፌስቡክ:-https://www.facebook.com/profile.php?id=100075869087632