Get Mystery Box with random crypto!

ውሸት ተከታዮቹን ስላበዛ እውነት አይሆንም ስለ ውሸት ሰሞኑን የገባኝን ትንሽ ነገር ልበላችሁ። | WORD OF GOD

ውሸት ተከታዮቹን ስላበዛ እውነት አይሆንም

ስለ ውሸት ሰሞኑን የገባኝን ትንሽ ነገር ልበላችሁ።
በህይወት መንገድ (በክርስትና ሕይወት ) Majority ሚባል ነገር የለም።
ህይወታችንን የምንመራው ህወታችንን እንዲመራ ከሰጠነው አካል በሚሰጠን መተደደሪያ ደንብ ነው። ይሄን ደንብ የምንቀበለውና የምንተገብረው ህይወታችንን ካስገዛንለት አካል አንጻር እንጂ በዙሪያችን ካሉ ሰዎች አይደለም።

፦ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያስተዋልኩት ይህንን ነው። የሚሄድበት የእውነት መንገድ ትክክል አይደለም እንዴ ብዬ ራሴን እስክጠይቅ በአብላጫ(majority ) የውሸት ድምጽ ግራ የተጋባሁባቸው ጊዜያት ነበሩ።
# አብላጫው ተቀብለው እየኖሩበት ነው ማለት ትክክል ነው ማለት አይደለም።
# አብላጫው normal ነው ያለው ጉዳይ ትክክል ነው ማለት አይደለም።

ይህ ስላቹ አሁን ያላቹበትን መንገድ እንድታጤኑ ነው።
፨ የህይወት መንገዳቹን የሚመራው ማን ነው?
፨የምታስቡት፣ የምትናገሩት፣ የምትኖሩት፣ የምትለብሱትና ለነገሮች ያላቹ አመለካከት፥በዙሪያቹ ባሉ አብዛኛ ሰዎች በሚከተሉትን እውነት በሚመስል በውሸት መንገድ ከሆነ፥አንድም ህይወታቹን ካስገዛቹለት አካልና ከሰጣቹ ደንብ ወጥታችዋል።ሌላም ማንነታቹን ጥላቹ በአብላጫ (majority) ድምጽ ውስጥ ተጨፍልቃችዋል(ተውጣችዋል)።

ይህን እርግጠኞች ሁኑ ራሳቹን የሰጣቹት አካል እውነተኛ መሪ እንደሆነ እና የሰጣቹ መመሪያን ከልባቹ እንደተቀበላቹና እርሱም ትክክል እንደሆነ። ከዛ ከእርሱ ውጪ የትኛውንም የአብላጫ ድምጽ እንዳትሰሙ በመንገዳቸውም እንዳትሄዱ።
፨አዎ በዚህ የህይወት ሕግ ስንመላለስ ብዙ የምናጣቸው ነገሮች፣የምናስቀይማቸው(የማናስደስታቸው)የቅርብ የምንላቸው ሰዎች ይኖራሉ። እነዚህን ግን ከያዝነው እውነት ጋር ማነጻጸር በፍጹም የለብንም። እውነትን እንደ መኖር "ደስታን" የሚሰጥ ነገር የለም።
፨በዚች ምድር ሁለት እውነት የለም።
የያዛችሁትን እውነት አጥብቃቹ ያዙ


ውሸት ተከታዮቹን ስላበዛ እውነት አይሆንም!!
28/8/2014
በኤደን ተጻፈ