Get Mystery Box with random crypto!

እኛ እና እነሱ ስትዋሸኝ፤ ስዋሽህ ስትጎዳኝ፤ ስጎዳህ ስትጠላኝ፤ ስጠላህ ስትገለኝ፤ስገልህ ስትቀብ | Wonder Soul 💭

እኛ እና እነሱ

ስትዋሸኝ፤ ስዋሽህ
ስትጎዳኝ፤ ስጎዳህ
ስትጠላኝ፤ ስጠላህ
ስትገለኝ፤ስገልህ
ስትቀብረኝ፤ ስቀብርህ
እራሴን ረስቼ፤ ላንተ መልስ ሳስስ
አንተን ሆኜ ቀረው፤ ያንተን ቁስል ሳምስ

ያደረጉንን ስናደርግ፤ የሁኑትን ስንሆን፤
በደልን በበደል፤ ህመምን በህመም
መልሳችን ከሆን፤ የእጃቸውን በእጃችን
ቦታ ተቀያየርን አንጂ፤ ከእነሱ በምን ተሻልን ??
እነሱ እኛ ነን፤ እኛም እነሱን ነን
ከላይ ለሚያየን ሰው
እኛው በዳይ፤ እኛው ተበዳይ ነን

የሰበረን መስበር፤ የወጋንን መውጋት
ያፋረሰን ማፍረስ፤ የጠላንን መጥላት
ያቆሰለን ማቁሰል፤ የገደለን መግደል
ያዋረደንን ማዋረድ፤ ያቀለለንን ማቀለል
ቢሆን ኖሮ መላው፤ መፍትሄው ማበጃው
ያረጉትን ማድረግ ፤ የሆኑትን መሆን
በዚህ ሁሉ ጊዜ፤ የት እና የት በደረስን

WonderSoul