Get Mystery Box with random crypto!

Wollo university kombolcha campus student union

የቴሌግራም ቻናል አርማ wollostu — Wollo university kombolcha campus student union W
የቴሌግራም ቻናል አርማ wollostu — Wollo university kombolcha campus student union
የሰርጥ አድራሻ: @wollostu
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.96K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በተማሪዎች ህብረት በኩል መረጃ የሚያገኙበት ቻናል ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ
👇👇👇👇
wollostu@2012
👇👇👇👇👇👇
ለጥያቄ፡ ለአስተያየትወ ይሄን ይጠቀሙ
🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻
@Wollouniversitystudentunionbot

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 09:51:34 ማስታወቂያ
ለካፌ ተጠቃሚወች በሙሉ ዛሬ ማለትም 26/12/14 የምሳ ሜኑ ስጋ መሆኑ ይታወቃል። ነገር ግን ባጋጠመን የማሽን ብልሽት ምክንያት ሜኑ የተቀየረ መሆኑን እየገለፅን
ስለተፈጠረዉ የሜኑ መቀያየር ይቅርታ እንጠይቃለን
የተ/ህ/ጽ/ቤት
934 viewsedited  06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 15:38:28 ማስታወቂያ
በኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ግቢ ዉስት ለምትገኙ ተማሪዎች በሙሉ
እንደሚታወቀው አሁን ባለዉ ሀገራዊ ጉዳይ የግቢያችንን እና በግቢ ዉስጥ የሚገኙ ተማሪወችን ሰላም እና ደህንንነት ለማስጠበቅ ተማሪዎች ወደ ግቢ መግቢያ ሰአት ማሻሻያ ተደርጓል።ስለሆነም ከዛሪ ማለትም 25/12/14 ጀምሮ ወደ ግቢ መግባት የሚቻለዉ እስከ 11:00 ድረስ መሆኑን እንገልፃለን።
ይህንንም በመረዳት ተማሪዎች በሰአቱ ወደ ግቢ እንድትገቡ እናሳስባለን።
የተማሪዎች ህብረት ጸ/ቤት
868 viewsedited  12:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:28:34 ሰላም ውድ የግቢያችን ተማሪዎች እንደሚታወቀው በሀገራዊ ጉዳይ ላይ በተደጋጋሚ የግቢውን ውሳኔ በተመለከተ ምንድን ነው የሚል ጥያቄ ነበር ።ሆኖም ግቢው ይሄንን በተመለከተ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ምንም ትምህርት ዘግቶ የሚያስኬድ ባለመሆኑ ተረጋግታችሁ መጨረስ ያልባችሁን እንድትጨርሱ ።ከዚህ በተረፈ አድስ ነገር ከተፈጠረ ማለትም ችግሩ ወደዚህ የሚመጣ ከሆነ ቀድሞ ግቢው በግልጽ የሚያሳውቅ ይሆናል።እናም ራሳችሁን ከሀሰተኛ መረጃ በማራቅ ለግቢያችን ሰላም የየራሳችንን ድርሻ እንወጣ ። የተ/ህ/ጽ/ቤት
780 views16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:17:41
#ATTENTION

ኮምቦልቻ !

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ምክር ቤት የከተማድን ሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ከመከረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

ከውሳኔዎቹ መካከል ፦

- ከዛሬ ነሀሴ 24/2014ዓ.ም ጀምሮ ማንኛውም የከተማው ነዋሪ ከ11 ጀምሮ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

- በማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም አላስፈላጊ ህዝብን ወደ አለመረጋጋት የሚወስዱ የተዛቡ መረጃዎችን መልቀቅ በህግ ያስጠይቃል።

- በከተማው አሉባልታ ማናፈስ በህብረተሰብ መካከል ሽብርና ውዥንብር የሚነዙ የተሳሳተ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት በህግ እንዲጠየቁ ተወስኗል።

- በከተማ ደረጃ  አገልግሎት የሚሰጡ  ታክሲዎች እስከ 11 ሰዓት ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ  ተወስኗል።

- ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተንተርሶ የከተማችን ነዋሪ ላይ ያለ አግባብ ዋጋ ጭማሪ በማድረግ እና ሸቀጦችን በመከዘን በገበያ ላይ እጥረትን  በመፍጠር ነዋሪውን ለተጨማሪ ወጭና የኑሮ ጫና የሚጥሉ አካላት ላይ ህጋዊ እረምጃ  እንዲወሰድ ታዟል።

- በምግብ ቤቶች ፣ መጠጥ ቤቶች፣ ካፌዎችና ግረሶሪዎች ከ11 ስዓት ጀምሮ ማንኛውም አገልግሎት መሰጠት ተከልክሏል።

- DSTV ማሳያ ቤቶች ፣የቡና መሸጫ ቤቶች ፣የሺሻና የጫት ማስቃሚያ ቤቶች ውስጥ ተሰብስቦ  ጫት መቃም በህግ ያስጠይቃል።

- የአልጋ አከራ ሆቴሎች፣ የመኖሪያ እና መደብ አከራዮችን አገልግሎት ሲሰጡ የተገልጋዩን ማንነት የሚገልፅ መረጃ በመያዝ አገልግሎት እንዲሰጡና መታወቂያ ኮፒ ማድረግ እንዳይዘነጉ ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

ለመረጃ እና ጥቆማ፦ በስልክ ቁጥሮች 0335510005
0335510945
0921038804 ላይ መደወል ይቻላል።

@tikvahethiopia
792 views16:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 12:06:09
ውድ ተማሪዎች !!!
በአሁኑ ስዓት በግቢያችን ውስጥ ትምህርታችሁን እየተከታተላችሁ የምትገኙ ተማሪዎች በሙሉ እንደሚታወቀው ሃገራዊ ችግሩን ምክኒያት በማድረግ ውስጣችሁ እንደተረበሸ እንደሆነ በተማሪዎች ህብረት ቢሮ መጣችሁ ማመልከታችሁ ይታወቃል።
ስለሆነም ተማሪዎች ህብረት ጥያቄያችሁን ለሚመለከተው አካል አቅርቧል።

ስለዚህ ዩኒቨርስቲው በአሁኑ ስዓት ስለጉዳዩ ውይይት እያደረገ በመሆኑ በአሁኑ ስዓት ግን ከተለያዩ ውዝግቦች ራሳችሁን አግላችሁ ተረጋግታችሁ ትምህርታችሁን እንድትከታተሉና አስፈላጊ በሚሆን ስዓት ዩኒቨርስቲው ውሳኔውን ያሳውቃል።

ማሳሰቢያ ትምህርታችሁን አጠናቃችሁ እየወጣችሁ ያላችሁ የአንደኛ አመት መደበኛ ተማሪዎች ግን ካለአግባብ ወጪና እንግልት ተቆጥባችሁ በዝግታ አጣራታችሁ ጉዞ እንድታደርጉ እናሳስባለን።

ስለዩኒቨርስቲያችን አዲስ ነገር
መልሰን እናሳውቃለን።

የተማ/ህ/ፅ/ቤት
1.1K views09:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 14:06:09
ወሎ ዩኒቨርስቲ ኮምቦልቻ ካምፓስ በዛሪዉ እለት ለአንደኛ አመት ተማሪወች ኮሌጅ መረጣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ።
የሚመርጦቸው ኮሌጆች ብዛት 6 ሲሆኑ እነሱም:-1 Medicine
2 anesthesia
3 pharmacy
4 veterinary
5 other natural since and
6 engineering vs technology
ሲሆኑ ከነዚህም ዉስጥ ከ1እስከ4 ያሉት ኮሌጆች coc ይኖራቸዋል። coc የሚሰጥበት ቀን እሮብ ማለትም 25/12/14 ነው።
በተጨማሪም ኮሌጆቹን መምረጥ የሜቻለዉ ከዛሪ 23/12/14 ጀምሮ እስከነገ24/12/14 ድረስ ነዉ።
የተማሪዎች ህብረት ጸ/ቤት
1.3K views11:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 17:18:16
1.9K views14:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 19:49:49 ማስታወቂያ

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረዉ የ2014 gc cup የእግር ኳስ ዉድድር ነገ ማለትም በ20/12/14 የመክፈቻ ጨዋታውን አዘጋጅቶል።
በነገውም እለት ሁለት ጨዋታወች ሲኖሩ:- #የመጀመሪያው Electrical Vs M.C.A ከቀኑ 8:00 ሰአት ላይ ሲጀምር
#ሁለተኛዉ mechanical Vs software,It ከቀኑ 10:00 ሰአት ላይ ይጀመራል።
የተማሪዎች ህብረት
2.0K viewsedited  16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 11:17:17 አስቸኳይ ማስታወቂያ


የዛሬ( ሃሙስ) ሜኑ ምሳ ላይ ስጋ በሙሉ እንጀራ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ነገር ግን ስጋ አቅራቢው ድርጅት ጥራቱን የጠበቀ ስጋ ባለማቅረቡ ምክንያት ተመላሽ የሆነ ስለሆነ
በምትኩ ምስር እንዲቀርብ አድርገናል፡፡
ስለሆነም ውድ ተማሪዎቻችን የዛሬ ምሳ ሜኑ ምስር መሆኑን አውቃችህ የተለመደ ትብብራችሁን እንድታደርጉ እናሳውቃለን በቀጣይ ማክሰኞ የስጋውን ማካካሻ የምናደርግ መሆኑን እየገለፅን
ስለተፈጠረው የሜኑ መቀያየር ታላቅ ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት

https://t.me/wollostu
2.6K viewsedited  08:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 21:34:13 ለኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ
የሃገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ፈተና ከመስከረም 28 ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጥ መሆኑን ተከትሎ ዛሬ የዩኒቨርሲቲው ሰኔት በስብሰባው የሚከትሉን ውሳኒዎች አሳርፏል።
#1. ተመራቂ ተማሪወች መስከረም 15 ትምህርታቸውን አጠናቀው ይወጣሉ። ይህም ባለው አጭር ጊዜ ጊዜያችሁን በአግባቡ በመጠቀም እስከ መስከረም 15/01/15 እንዲታጠናቅቁ የሚደረግ ሲሆን
#2. ጊዜዊ የ መመረቂያ ቀን ( graduation event : ጥቅምት 26 እና 27) ሆኖ የተወሰነ ሲሆን ይህም ከ መስከረም 28 እሰከ ጥቅምት 17 ድረስ የ 12 ኛ ክፍል የሚፈተኑበት ግዜ በመሆኑ ማንኛውም ተማሪ ከግቢ እንዲወጣ የኢ/ከ/ትም/ት ተቋም ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በሚኒስተር መስሪያ ቤቱ ከተዋቀረ የፈተና ኮሚቴ ውጭ ግቢ ውስጥ ማንም መቆዬት እንደማይችል ያሳወቀ በመሆኑ እስከ ተጠቀሰው ቀን ብቻ አጠናቃችሁ እንድትወጡ ተወስኗል።

የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት
3.0K views18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ