Get Mystery Box with random crypto!

#ሸር_ፖስት አትፍሩ ሸር አድርጉት:- ለሚመለከታችሁ! ከአሁን በፊት እንደገለፅኩት ከባባድ መሳሪያዎ | Wollo Addis

#ሸር_ፖስት አትፍሩ ሸር አድርጉት:- ለሚመለከታችሁ!
ከአሁን በፊት እንደገለፅኩት ከባባድ መሳሪያዎች አሁን ለያዝነው ትግል ዋጋ የላቸውም። ከዚህ ውጭ የቡድን መሳሪያ ድሽቃ፣ ብሬን፣ ስናይፐር ቢይዝም እኛም ከተራራ እና የቆረጠ ልብ ጋር ይዘናል። በተፈጥሮው የሚዋጋ ገዢ መሬት አለን። በመቀጠል የአማራን ህዝብ የመሰለ ደጀን ህዝብ አለን። ወራሪው ቡድንስ ውቂያኖስ ውስጥ ሁኖ መዋኘት ብቻ ነው። በህውሃት ጦርነት የተማርናቸውን እና ውጤታማ የነበሩ የትግል ተግባሮች በዚህኛውም ተፈፃሚ ይሆናሉ።

ሌላው ከህዝቡ መሀል ሁነው በስልክም በአካልም የሚያቃጥሩትን እየለየን እንመክራለን። የማይመከሩትን እንደየ ደረጃው እርምጃ ይወሰዳል። በስልክ የሚገናኙትን ያቋቋምነው የሳይበር ቡድን የደህንነት መስሪያ ቤት ከሚሠሩ ወንድሞቻችን ጋር እየሠራን ነው። የስልክ ግንኙነታቸው በቅጅ እና በሰነድ ተገልብጦ ይፋ ይሆናል።

በአካል የሚያቃጥሩትን በየአካባቢው ያለው ህቡዕ የሕዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪው የመለየት ስራውን ሲጨርስ ለህዝብ ይፋ እናደርጋለን። እስከዛው ግን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የወራሪ ተባባሪ የሆናችሁ ከድርጊታችሁ ታቀቡ። ህዝብን በዓለም ታሪክ ታግሎ ያሸነፈ የለም።

ድል ለአማራ ህዝብ

#AmharaStruggle
#Justice4Amhara
#AmharaGenocide