Get Mystery Box with random crypto!

በስምንት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የወንጀል ምርመራ እንዲጀመር መወሰኑ ተሠማ። ይህ የተገለጸ | መከላከያው ሰራዊት ዜና ከየ አቅጣጫው

በስምንት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የወንጀል ምርመራ እንዲጀመር መወሰኑ ተሠማ።

ይህ የተገለጸው የሕ/ተ/ም/ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2014 በጀት ዓመት የኦዲት ባለድርሻ አካላትን የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ሰኞ ኅዳር 26/2015 ዓ.ም በገመገመበት ወቅት ነው፡፡

የቋሚ ኮሚቴው የፐብሊክ ፋይናንስ ኦፊሰር አቶ ዘሪሁን አስፋው እንደተናገሩት፥ የመንግሥትን ሀብት በመመዝበር በተለዩ ስምንት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የወንጀል ምርመራ እንዲካሄድ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በፍትሕ ሚኒስቴር ዓቃቤ ሕግ የወንጀል ጭብጦችን የመለየት ሥራ በመከናወን ላይ ነው።

የወንጀል ምርመራ እንዲካሄድባቸው የተለዩት ዩኒቨርሲቲዎችም ቡሌ ሆራ፣ አርባ ምንጭ፣ ወልድያ፣ ሀዋሳ፣ መቱ፣ ደብረ ታቦር፣ ዲላ እና ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

(ሪፖርተር)
@EthioipaNews