Get Mystery Box with random crypto!

መስቀሉን ፍለጋ ከሶስቱ ተራሮች በአንዱ ተቀብሮ፣ ሁሉም ከበዓቱ ቆሻሻን ጨምሮ። አይሁድ ተመ | ውስተ ቀራንዮ ነጽሩ(የምድያም ምድር)



መስቀሉን ፍለጋ


ከሶስቱ ተራሮች በአንዱ ተቀብሮ፣
ሁሉም ከበዓቱ ቆሻሻን ጨምሮ።
አይሁድ ተመሣጥረዉ ፍቅርን ሊሸሽጉ፣
ለክርስቲያን ወገን መድኃኒት ሊነፍጉ።
ጌታ አልተነሳም ብለዉ ሊያስወሩ፣
የመስቀሉን ካሳ ዱካ ሊሰዉሩ።
ድዉይ እንዳይፈዉስ ሙት እንዳያነሳ፣
ምሥጢሩ እንዲሸሸግ ክብሩ እንዲረሳ።
የመስቀሉ ፍቅር ልቧን ቢያቃጥለዉ፣
የንግስቷን ሀሳብ ሰቅዞ ቢይዘዉ።
የጌታዋ መስቀል ባለም እንዲያበራ፣
መሻቷን ልትፈፅም ተራራ አስቆፍራ።
የንግስቷ አሽከሮች ስፍራዉ ጠፍቶባቸዉ፣
ቦታዉን ለማግኘት ተሟጦ ተስፋቸዉ።
ዉዝግቡ ቆሞ ልባቸዉ ሲረጋ፣
ታሪክ የሚያዉቁትን ተነሱ ፍለጋ።
አንድ ሽማግሌ ምሥጢሩን ያወቀ፣
ያባቶቹን ባህል ትዉፊት ያስጠበቀ።
መድኃኒት ስትፈልግ ኪራኮስን ይዛ፣
እምነትን ተጫምታ ወንጌል ተመርኩዛ።
እሳቱን ለኩሳ ደመራ አስደምራ፣
ጢሱ እንዲመራት እጣንን ጨምራ።
የደመራዉ ጢስ ወደላይ ነጎደ፣
መስቀል ወዳለበት ተራራ ሰገደ።
የነፃነት አርማ የድህነት ምልክት፣
ከባርነት መዉጫ መዳኛ ትምክህት።
የተዋህዶን ንጉስ አንግሱ በተስፋ፣
ዕፀ_መስቀል ያዙ ጠላት እንዲጠፋ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ኤደን