2021-10-30 14:30:55
የደሴ ግንባር
የወገን ጦር አሁንም እየተዋደቀ ነው። የወራሪው ኃይል እንደ ዞምቢ እየረገፈ
ይገኛል። በራዲዮ ጠለፋ እንደተረጋገጠው የሞተው ሞቶ የተረፈው ወደፊት
በማዕበል መልክ መግፋት አለብን ብለው እየተንቀሳቀሱ ነው። ከላይ ከመቀሌ
ወደ ግንባሩ የሚተላለፈው መልዕክት "ደሴን ተቆጣጠሩ" የሚል ነው። ግንባር
ያለው ወራሪ በተደጋጋሚ አቅማችን ደክሟል አንችልም ሲል ይደመጣል።
በደሴ ዙሪያ ያለው የወገን ኃይል እንደበረታ ነው። ነገር ግን በአንድ ግንባር
በተፈጠረ መጠነኛ የስልት ትግበራ ስህተት ጥቂት የወራሪው ታጣቂዎች
ሾልከው ወደ ከተማው የመግባት ሙከራ አድርገው ነበር። እሱን ለማስተካከል
ከፍተኛ ርብርብ ተደርጎ አሁን ነገሮች በተሻለ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ።
በከተማው ያለው የሕዝብ ስብጥር ሁኔታ ነገሮችን ውስብስብ አድርጓቸዋል።
በአሥር ሺህዎች የሚቆጠሩ ትግ*ዎች ደሴ ውስጥ ይኖራሉ። አብዛኛው እንደ
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሰላማዊ ሲቪሊያን ቢሆኑም ከመካከላቸው ለትህነግ
የሚሰሩ እንዳሉ በግልፅ ታይቷል። በዚህ ሁለት ቀን ውዥንብር ሲነሳ ሲጨፍሩ
የታዩ ሁሉ ነበሩ።
ደሴ ከተማ በከፍተኛ መጠን የትህነግ ሰላዮች ያሉባት መሆኗ ተረጋግጧል።
ቅድም እነቶማስ ባረፉበት ሆቴል ውስጥ የሞርታር ጥቃት ተፈፅሟል። በጣም
የሚገርመው ይዘውት የነበረው አልጋ ተመትቷል። ይህ የሚያመለክተው
አስተኳሹ ሆቴሉ ውስጥ ያለ/የነበረ ግለሰብ ሊሆን የሚችልበት ዕድል ያለ
መሆኑን ነው። በሌሎች ቢያንስ በአራት ሆቴሎች ላይ ተመሳሳይ ነገር ተሞክራል።
ከእነዚህ መካከል የመከላከያ ሰራዊት ጄኔራሎች አርፈውበት የነበረ ቦታ ይገኛል።
ይህ ሁሉ የሽብርና የማወናበድ እንቅስቃሴ የሚፈፀመው የኢትዮጵያ
መንግሥት በሚለቀው የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት አማካኝነት ነው።
መንግሥት ከቆቦ ጀምሮ ለምን ኢንተርኔትና ስልክ ሳያጠፋ ለአሸባሪው ምቹ
ሁኔታ እንደሚፈጥር ግልፅ አይደለም።
ደሴ እና አካባቢው ያለው የመንግሥት መዋቅር በጣም ደክሟል። ከተማው
አስተማማኝ ጥበቃ እየተደረገበት አልነበረም/አሁንም አጠራጣሪ ነው።
ከከተማው ለሚገባና ለሚወጣ እንቅስቃሴ ኬላዎች እስከ ቅርብ ጊዜ
እንዳልነበሩ መረጃዎች ያሳያሉ። እንደ ጦርነት ቀጠና ይህ ከወራት በፊት መደረግ
የነበረበት ነው። ሁኔታው ሰርጎ ገብ እንደልቡ እንዲወጣ እንዲገባ ዕድል
ፈጥሯል።
ዘወትር እንደምናገረው ዝቅተኛው መዋቅር (የወረዳና የቀበሌ) በጣም
ቁልፍ ሲሆን ሕዝቡን ያለዚህ መዋቅር በተጨባጭ ማንቀሳቀስ ከባድ ነው። ይህ
መዋቅር እንዲጠናከር በጣም በጣም መስራት ይገባል።
ጊዜያዊ መፍትሔ!
ደሴና አካባቢው በወታደራዊ ቁጥጥር ስር መግባት አለባት። የሲቪል
መዋቅሩ ለጊዜው "freeze" መደረግ አለበት። ማርሻል ሩል መተግባር አለበት።
ሌላ አማራጭ የለም።
2.4K viewsMIF_ነኝ 𝙚𝙗𝙣𝙪𝙡 haiky, 11:30