Get Mystery Box with random crypto!

' ውሳኔው ተገቢነት የሌለው ነው ፤ ፈተናው ከተቻለ አሁን ካልሆነ በቅርብ ቀናት ውስጥ ሊሰጥ ይገባ | Students News & Well laptop®

" ውሳኔው ተገቢነት የሌለው ነው ፤ ፈተናው ከተቻለ አሁን ካልሆነ በቅርብ ቀናት ውስጥ ሊሰጥ ይገባል " - ተማሪዎች / የተማሪ ወላጆች

የሬሜዲያል መርሀግብር ሲከታተሉ ቆይተው ፈተናው ወደ መስከረም 2016 ዓ/ም የተሸጋገረባቸው ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች የትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ ከፍተኛ ቅሬታ እንዳሳደረባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ እና ወላጆቻቸው ለወራት ያህል ገንዘባቸውን እየከፈሉ ትምህርቱን ከተከታተሉና የመጀመሪያ ቀን ፈተና ከወሰዱ በኃላ ሚኒስቴሩ ፈተናው ወደ መስከረም ወር መራዘሙን ማሳወቁ ፍፁም ተገቢ አይደለም በማለት ተቃውመዋል።

አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ክልል ከተሞች የሚገኙ ተማሪዎች ውሳኔ እንዲቀለበስ የሚመለከታቸውን አካላት ተሰባስበው ለመጠየቅ ጥረት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ለአብነት በአዲስ አበባ 4 ኪሎ፤ ትምህርት ሚኒስቴር አካባቢ ጥያቄ አለን ያሉ ተማሪዎች ተሰባስበው ጥያቄያቸውን ለማቅረብ ጥረት አድርገዋል፤ ከጅማ እንዲሁም ከሀዋሳ የግል ተፈኞች ጥያቄያቸውን ተሰባስበው ለማሳመት እንደጣሩ ለመረዳት ችለናል።

ውሳኔውን ቅሬታ አሳድሮብናል ያሉት የሬሜዲያል የግል ተፈታኝ ተማሪዎች፤ " ብዙ መሰዋትነት ከፍለን ነው የተማርነው ፤ ከቤተሰብ ተለይተን የቤት ክራይ እየከፈልን የት/ት ወርሀዊ ክፍያ እየከፈልን የተማርንም አለን፤ ቤተሰብም እኛን ለማስተማር ሲል ከፍተኛ ዋጋ ከፍሏል ፤ ይህን ሁሉ ተቋቁመን ለ4 ወር ያክል ቆይተን አሁን ፈተናውን እኛ የግል ት/ት ቤት ተማሪዎች ብቻ አትፈተኑም መባላችን ትክክል አይደለም፤ ይህ ውሳኔ ከፍተኛ የስነ ልቦና ጫና ያደርስብናል " ሲሉ ገልጸዋል።

በተመሳሳይ የተማሪ ወላጆች ውሳኔው ልጆቻቸው ብዙ የደከሙበትን ጥረት ወደኃላ የሚመልስ መሆኑን በመግለፅ፤ በጥናታቸው ላይ የሚያሳድረውን ስነልቦናዊ ጫና በመገንዘብ ትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔውን በማጠፍ ልጆቻቸው ፈተናቸውን ልክ እንደ ሌሎች ተማሪዎች በተመሳሳይ ጊዜ እና ወቅት እንዲወስዱ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

ፈተናውን አሁን ካልተቻለም ደግሞ የተማሪዎች ለፈተናው ያደረጉት ዝግጅት ብዙ ሳይጠፋባቸው በአጭር ቀናት ውስጥ እንዲሆን ተማሪዎቹ እና ወላጆቻቸው ጠይቀዋል።

ተማሪዎቹም ሆኑ ወላጆቻቸው በአሰራር ጉድለት እና በተፈጠረው ችግር ይህ ውሳኔ መተላለፉ በተማሪዎች ህይወት፣ ጊዜ እና እድሜ ላይ ጫና እንዳለው አስረድተዋል። ለዚህ የአሰራር ጉድለት ተወቃሹ ሚኒስቴሩ ሆኖ ሳለ ይህን መሰሉ ውሳኔ ተላልፎ በተማሪዎች ላይ ለሚደርሰው ጫና ማነው ተጠያቂው ? ሲሉም ጠይቀዋል።

በተወሰነው ውሳኔ " የተማሪዎች ሞራል ሊጎዳ አይገባም " ያሉ አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ደግሞ ፤ ተፈጠረ የተባለው ችግር የት እና በማን ተፈጠረ የሚለውን ተጣርቶ ውሳኔ ሊተላለፍ ይገባ ነበር የጅምላ ውሳኔ ተገቢ አይደለም ብለዋል።

" ከጅምሩ እንዲህ ያለ ስጋት ካለ ሁሉም የግል ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ተማሪ በመንግስት ዩኒቨርሲቲ ገብቶ እንዲፈተኑ ማድረግ ይቻል ነበር፤ ከዚህ አለፍ ሲልም ሚኒስቴሩ Plan B ሊኖረው ይገባ ነበር " ሲሉ ውሳኔውን ተቃውመዋል። ፈተና በተቻለ ፍጥነት በአጭር ጊዜ ቢሰጥ ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለተማሪዎቹና ወላጆቻቸውን ቅሬታ በተመለከተ ከሚመለከተው አካል ምላሽ ለማግኘት ጥረት ያደርጋል።

ትምህርት ሚኒስቴር፤ ቀደም ብሎ በሁሉም ሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ባላቸው ተቋማት ፈተናውን በአንድ ጊዜ ለመስጠት የታቀደው ተሻሽሎ በተለይም ከ150 በላይ የሆኑና ከ200 በላይ ካምፓስ ያላቸውን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈተና ቀርቶ  ወደ ፊት  በሚወሰን አግባብ ፈተናው በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም  እንዲሰጥ መወሰኑ ይታወቃል።
#ለፈጣን እና ታማኝ መረጃ



#Share
#Share



Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
https://t.me/Temhert_Minister
https://t.me/Temhert_Minister