Get Mystery Box with random crypto!

#የትምህርትና_ስልጠና_ባለሥልጣን የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና የ | Students News & Well laptop®

#የትምህርትና_ስልጠና_ባለሥልጣን

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን መረጃ አሟልተው የላኩ 162 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

እስካሁን የተሟላ ዝርዝር ከላኩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል አምስት ዩኒቨርሲቲዎች ማለትም ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ፣ ሐራምቤ ዩኒቨርሲቲ፣ አድማስ ዩኒቨርሲቲ፣ ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ እና ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ይገኙበታል።

በ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና እንዲወስዱ ከግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላኩ የተማሪዎችን መረጃ ትክክለኛነት እያጣራ መሆኑን የገለጸው ባለሥልጣኑ፤ የተማሪዎችን መረጃ አጣርቶ እንደጨረሰ ለመውጫ ፈተና የሚቀመጡ ተማሪዎችን ዝርዝር እንደሚያሳውቅ ገልጿል፡፡

(የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን የተሟላ መረጃ የላኩ 162 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ዝርዝር ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ።)

ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
 @TemhertMinisterbot

#ለፈጣን እና ታማኝ መረጃ



#share
#share



https://t.me/Temhert_Minister
https://t.me/Temhert_Minister
https://t.me/Temhert_Minister