Get Mystery Box with random crypto!

በአማራ ክልል ከ215 ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለ2015 ዓ.ም ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና መ | Students News & Well laptop®

በአማራ ክልል ከ215 ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለ2015 ዓ.ም ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና መመዝገባቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል፡፡

የተፈታኞቹ ምዝገባ በክልሉ በሚገኙ 575 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በበይነ መረብ ብቻ እንደተካሄደ በቢሮው የፈተናና ምዘና ቡድን መሪ ዝጋለ ማሩ ለአሚኮ ተናግረዋል፡፡

በሰሜን ጎንደር እና በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር የሚገኙ አራት ትምህርት ቤቶች በአካባቢዎቹ በተነሳ ጦርነት ምክንያት የተማሪዎች ምዝገባ ማድረግ አለመቻላቸውን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

በክልሉ 215 ሺህ 760 ተማሪዎች የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለመውሰድ መመዝገባቸውን ጠቁመዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ

https://t.me/welllaptops