Get Mystery Box with random crypto!

#TigrayEducationBureau በትግራይ ክልል ተቋርጦ የቆየውን የመማር ማስተማር ሥራ ለማስ | Students News & Well laptop®

#TigrayEducationBureau

በትግራይ ክልል ተቋርጦ የቆየውን የመማር ማስተማር ሥራ ለማስጀመር የተማሪዎች ምዝገባ ከሚያዝያ 18/2015 ዓ.ም ጀምሮ ይከናወናል።

የተማሪዎች ምዝገባው በሁሉም ትምህርት ቤቶች እንደሚከናወን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

በክልሉ ትምህርት ለማስጀመር ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ዳኘው አይጠገብ ለኢፕድ ተናግረዋል።

በዚህም ከቅድመ አንደኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትምህርት እንደሚጀምር ገልጸዋል።

መምህራንን የማሰባሰብ ሥራ ለማከናወን ሰነድ መዘጋጀቱን የገለጹት ኃላፊው፤ ደመወዝ ያልተከፈላቸው ሰራተኞች እንዲከፈላቸውና ወደ ትምህርት እንዲገባም ውሳኔ ላይ ተደርሷል ብለዋል።

የጊዜያዊ መንግስት በተቋቋመባቸው የክልሉ አካባቢዎች መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ መደበኛ ሚያዝያ 23/2015 ዓ.ም እንደሚጀመር ቢሮው ከዚህ ቀደም መግለጹ ይታወሳል፡፡

@welllaptops