Get Mystery Box with random crypto!

ፀሐይ ባንክ ሐምሌ 16 ቀን 2014 በይፋ ሥራ ጀምራለሁ ብሏል፡፡ ባንኩ በ2 ነጥብ 9 ቢሊዮን | Wegegta Media

ፀሐይ ባንክ ሐምሌ 16 ቀን 2014 በይፋ ሥራ ጀምራለሁ ብሏል፡፡

ባንኩ በ2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር የተፈረመና በ734 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል ተቋቁሟል፡፡

“ለሁሉ” በሚል መሪ ቃል የፊታችን ሐምሌ 16 ቀን 2014 በይፋ ሥራ እንደሚጀምር ያስታወቀው ባንኩ፣ ዝቅተኛ የአክሲዮን ግዢውን ከብር 100 ሺህ በመጀመር፣ በ373 ባለአክሲዮኖች መመስረቱን አስታውቋል፡፡

የመስራች ጉባኤውን የካቲት 11 ቀን 2013 በማካሄድ የባንክ ኢንዱስትሪውን መቀላቀሉን የባንኩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ያሬድ መስፍን አስታዉሰዋል፡፡

ዓላማችን የባንክ አገልግሎት ብቻ ሳይሆን በፋይናንስ ዘርፉ በቂ ትኩረት ያላገኙትን የስራ ፈጠራን እና የስራ ፈጣሪዎችን፤ የጥቃቅንና አነስተኛ፣ የግብርናውን ዘርፍ እንዲሁም የአምራች ኢንዱስትሪውን ተደራሽ ለመሆን አልመናል ብለዋል፡፡
“ለሁሉም የሆነ ባንክ” እንዲሆን የአገልጋይነትን ዕሴትን ተላብሶ ሃምሌ 16 ስራ ይጀምራል የተባለው ባንኩ፣ በእለቱ 30 ቅርንጫፎች የባንክ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ ተገልጿል፡፡

በቅርቡም ባንኩ የቅርንጫፎቹን ቁጥር ከ50 በላይ የማሳደግ እቅድ ያለው መሆኑን የገለፀ ሲሆን፣ በአንድ አመት ውስጥም በመላው የሃገራች አካባቢዎች 100 የሚሆኑ ቅርጫፎችን ወደ ስራ ለማስገባት ማቀዱን ባንኩ ይፋ አድርጓል፡፡

Via ethio fm

@wegegta_media