Get Mystery Box with random crypto!

. ARMAGEDON እንግሊዛውያን ህንድን በቀኝ ግዛት ያስተዳድሩ በነበ | አርማጌዶን

. ARMAGEDON

እንግሊዛውያን ህንድን በቀኝ ግዛት ያስተዳድሩ በነበረበት ጊዜ እንዲህ ሆነ።

በህንድ ሀገር በደልሂ ከተማ የመርዘኛ ኮብራ እባቦች መበራከት አሳሳቢ ደረጃ ደረሰ። እንግሊዞችም የእባቦቹን ቁጥር ለመቀነስ መፍትሄ ያሉትን አስቀመጡ።ኮብራ እባብ ገሎ ይዞ ለሚመጣ ማንኛውም ግለሰብ ከመንግስት ሽልማት እንደሚበረከትለት አዋጅ አስነገሩ። ይህን ተከትሎም የእባቦቹን ቁጥር ለጥቂት ጊዜ ለመቀነስ ተቻለ። ከጊዜ በኋላ ግን ህንዳውያኑ ሽልማት ለማገኘት ሲሉ በየጓሮቸው እባብ ያረቡ ጀመር።ይህን የተረዳው የእንግሊዝ መንግስትም አዋጁን ሽሮ ሽልማት መስጠት አቆመ። በዚህ የተናደዱት ህንዳውያንም ያረብዋቸው የነበሩትን እባቦች ለቀቋቸው። የመርዘኛ ኮብራ እባቦች ቁጥርም ከፊቱ የባሰ ሆነ።..

ይህን ሁነት የጀርመኑ ኢኮኖሚስት Horst Siebert "cobra effect" ብሎ ይጠራዋል። cobra effect በቀላሉ ሲተረጎም፦ ለችግሩ የምንሰጠው መፍትሄና መፍትሄው ላስከተለው ችግር የምንሰነዝረው ምላሽ የከፋ ችግር ሲፈጥር ...እንደማለት ነው። የሀገራችንም ችግር ይሄው ይመስለኛል።

ናትናኤል
@wedefkr
@wedefkr