Get Mystery Box with random crypto!

,. .. መርዘኛው ቅጠል ጫት! ይህ መርዘኛ ቅጠል ምነኛ ጎዳን ወንድሞችን ሁ | WEDE_HAK_TUBE

,. .. መርዘኛው ቅጠል ጫት!


ይህ መርዘኛ ቅጠል ምነኛ ጎዳን
ወንድሞችን ሁሉ አበላሸብን
ስንት አሳቢ ወጣት አሳበደብን
በፊት የነበረውን ቀልጣፋ ፈጣን
በሌሊት ተነስቶ የሚብከነከን
ጫት በመቃም ሰበብ አጥቷል ማንነቱን
በመጥፎ ተግባር ላይ ዘፍቋል ሂዎቱን
በጫቱ ሱስ ሰበብ አቁሟል መሮጡን
ብቻ ተቀምጦ ይጠብቃል ሞቱን
ሀቋን አያሟላም ያችን ባለቤቱን
በጫት ቢዚ ሁኖ ገድሎበት ስሜቱን
ያለ መጋርጃ አሰቀምጦ ሚስቱን
ቡና ቅጅ ይላል ጠርቶ ጓደኞቹን
ይህ መረዘኛ ቅጠል አጥፍቶት ቅናቱን
መቀለቡን ትቷል ሰርቶ ቤተሰቡን
እንደውም ይመኛል ከሚስቱ ገንዘብን
ወዳ ከሰጠችው ካልሆነ ፖርሳዋን
እሷ መች አወቀኝ ዱሮ ሚስራውን
ሳያገባት በፊት ሲያስለቅስ እናቱን
በስርቆት ተሰማርቶ ሲፈትሽ ጭጎቱን
ስለዚህ እህቴም ምረጭ ባልሽን
ጫት ቃሚ እዳትመርጭ እንዳትከፍቺ በሩን
ይዘሽ እንዳትመጭ በሱስ ያበደውን
ምን ያደርግልሻል አብዶ ከጨለለ
የፍየሏን ምግብ ልሙትበት ካለ
እንደ ግመል ምንጃክ ጉንጩን ከቆለለ
አፉ ተበላሽቶ ጨጓራ ከመሰለ
ለእርኩስ ጫት ብሎ አንችን ካታለለ
የጫትን ጥፋቶች መዘርዘር ይከብዳል
ትንሽ ግን መመልከት ዛሬ ግድ ሁኗል
ሲጋራ ለማጨስ በሮችን ይከፍታል
ወደ አሰካሪ መጠጥ በግድ ይገፋፋል
በጣም ያሳዝናል ሲቀባ በኢስላም ቅብ
አላማውን ቀይረው የፍየሏን ምግብ
ሲያላምጥ ይቆያል ያለ ጌዜ ገደብ
ቁጭ ብሎ እየዋለ በጁምዓ በሮብ
ሶላትን ኢባዳን በጫማው ስር ጥሎ
የሰይጣንን ድንኳን በሀድራ ስም ተክሎ
በሱፍዮች መንሀጅ ጫት ይሻላል ብሎ
በሸርክ በቢድዓ በጫት ተጠቅልሎ
ባጥማሚ ዱዓቶች ጋርዶ ተጠልሎ
ድን እያጠፋ ነው እነሱን ተከልሎ
https://t.me/Wede_Hak_Tube
አብዱረህማን ዑመር