Get Mystery Box with random crypto!

መምህር ኃይለማርያም ዘውዱ ( Hailemariam Zewdu ) ማን ናቸው? መምህር ኃይለማርያም ዘ | ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

መምህር ኃይለማርያም ዘውዱ ( Hailemariam Zewdu ) ማን ናቸው?

መምህር ኃይለማርያም ዘውዱ በአብነት ጉባኤ ቤት የዜማ፣ የቅኔ፣ የአቋቋም እና የትርጓሜ መጻሕፍት ትምህርቶችን በሚገባ የተማሩ፤ በዘመናዊ ትምህርትም የኢኮኖሚክስ ባለሙያ የሆኑ፡፡ በቦሩ ሜዳ በታላቁ ሊቅ በመምህር አካለ ወልድ የመጻሕፍት ትርጓሜ ት/ቤት የሐዲስ ኪዳን የትርጓሜ መጻሕፍትን ጉባኤ ዘርግተው ለበርካታ ዓመታት በማስተማር በርካታ ስመ ጥር መምህራንን ለቤተክርስቲያን ያበረከቱ እና እያበረከቱ የሚገኙ እንዲሁም በአሁኑ ጊዜ በወሎ ዩኒቨርሲቲ የግእዝ መምህር ሆነው በማስተማር ላይ የሚገኙ ናቸው።

ዛሬ ላይ እኚህ የመምህር አካለ ወልድ ጉባኤ ቤት መምህር የኔታ ኃይለ ማርያም በእስር ላይ ናቸው። ለዲያቆን Yaregal Abegaz Kebede ጽሑፍ መልስ ለመስጠት የፈጠነ ጠቅላይ ቤተክህነት ሊቁ ታፍነው ባላየ ባልሰማ ድምጹን ማጥፋቱ የሆነ ጥርጣሬን እና ግርምትን ይፈጥራል።

SHARE

@wdasemaryam
@wdasemaryam
@wdasemaryam