Get Mystery Box with random crypto!

እንኳን ለጽጌ ጾም በሰላም አደረሰን ጾመ ጽጌ ከመስከረም 26 እስከ ኀዳር 5 ያለው አንድ ወር ከ | ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

እንኳን ለጽጌ ጾም በሰላም አደረሰን

ጾመ ጽጌ ከመስከረም 26 እስከ ኀዳር 5 ያለው አንድ ወር ከአሥር ቀን ወይም 40 ቀን ወርኃ ጽጌ ፤ ዘመነ ጽጌ፤ ተብሎ ይጠራል!

=>ፅጌ ማለት አበባ ማለት ሲሆን በዚህ ወር የፅጌሬዳ አበባ የሚፈካበት ወር ነው ።

ጽጌሬዳ አበባ መአዛው እጅግ ያስደስታል
ለአይንም ይማርካል እመቤታችንም በአበባው እንመስላታለን ጉድፍ የሌለባት ለነፍስም ለስጋም ደስ የሚል ውበት የስጋ ድንግልና በነፍስም ድንግል ናትና
ጾመ ጽጌ እመቤታችን ስደቷን የምናስብበት ነው።

=> ጾመ ፅጌ የአዋጅ ፆም አይደለም የእመቤታችን ፍቅር ያለው ሰው በውዴት ይጾመዋል

=> ፆመ ፅጌ የድንግልን ስደት ለምለም አካላቷ ያልጠና ሰውነቷ በሀሩር በውርጭኝ ያለ ሀጥአቷ እንግልት በማየቷ በረከትን ለማግኘት እንጾማለን ማለት ነው።

=>ፆመ ጽጌ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ከተወለደ በኋላ የጥበብ ሰዎች በኮከብ መሪነት ሲጓዙ ከዛም ኮከቡም ተሰወረ ወደ ንጉስ ሄሮድስም ደረሱ የአይሁድ ንጉስ ወዴት አለ ብለውም ጠየቁ ሄሮድስም ደንግጦ በመልካም አቀባበልም ተቀበላቸው ተነስተውም ሲጓዙ ሄሮድስ የአይሁድ ንጉስ ሲሉት መንግስትነቱ የምድራዊ ንጉስ መስሎትም ንግስናዬን ይቀማኛል ብሎም ተሸበረ የጥበብ ሰዎችም ሲሸኛቸው ስለ ህጻኑ ባገኛችሁት ጊዜ መጥታችሁ ንገሩኝ እኔም እሰግድለት ዘንድ ብሎ ሸኛቸው

=> እነሱም ቀድሞ ይመራቸው የነበረ ኮከብ
ተገለጠላቸው።እየመራ ቤቴሌሄም እየተመሩ ወደ ህጻኑንም ከእናቱ ከድንግል ማርያም እና ከጠባቂዋ ዮሴፍ ጋር በቤቴሌሄም በከብቶች በረት አገኙት እጅ መንሻም ወርቅ እጣን ከርቤ አገቡለት
✥ወርቁ ለንግስናው
✥እጣኑ ለክህነቱ
✥ከርቤው በፍቃዱ ስለሰው ልጆች መሞቱ ያመለክታል።
ከዛም በመጡበት እንዳይመለሱ የእግዚአብሔር መልአክ በህልም ተገለጠላቸው በሌላ መንገድም ወደ ሀገራቸው ሄዱ።

=> እነርሱም ከሄዱ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ ተገልጦ እናቱና ህፃኑን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ እስክነግርህም ድረስ በዛ ቆይ አለው። ዮሴፍም እናቱና ህፃኑ ይዞ ስደት ጀመረ.። ሄሮድስም የጥበብ ሰዎች እንዳታለሉት ባወቀ ጊዜ አዋጅ አወጀ የሁዳ ሴቶች ሆይ እርዳታ እሰጣለሁ ልጆቻችሁ አስመዝግቡ ብለዎ አወጀ ከሁለት አመት ጅምሮ ያነሱትንም ህጻናት አሰበሰበ በነዚህ መካከል ሕጻኑ ክርስቶስን ያገኘ መስሎት ሁሉም በሰይፍ አሰየፋቸው ዲያብሎስም ለሄሮድስ በሞቱት ህፃናት መካከል እንደሌለ አማከረው ጭፍሮችም በፈረስ እንዲፈልጉትም ሽልማት አሲዞ ላካቸው ሌላው ሽልማት ሲያገኙት እንደሚሰጣቸው ተናግሮ
✥✥✥
ማቴ 2÷1........
•ጾሙ የበረከት የሰላም ያድርግልን ድንግል ሆይ በስደትሽ የጎበኘሻት ሀገር ኢትዮጵያ ዛሬም ጎብኛት
t.me/wdasemaryam

https://youtube.com/channel/UCzj1rOCD7-WVTFN7VU8RmZw
✥ደሳለኝ✥