Get Mystery Box with random crypto!

☞እመቤታች ድንግል ማርያም ሆይ ☞መልካሚቱ ምድር ድንግል ሆይ ከጤነኞችም ይልቅ እኛ ሕሙማን እንሻሸ | ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

☞እመቤታች ድንግል ማርያም ሆይ
☞መልካሚቱ ምድር ድንግል ሆይ ከጤነኞችም ይልቅ እኛ ሕሙማን እንሻሸለን፡፡
አንቺ የሕሙማን መድኃኒት ነሽና፡፡፡
☞እመቤታችን ድንግል ማርያም ሆይ ከጻድቃን ይልቅ እኛ ኃጢኣን እንወድሻለን፡፡
ንሥሓ ለሚገቡ ኹሉ አንቺ አማላጃቸው ነሽና፡፡
☞እመቤታችን ድንግል ማርያም ሆይ ከብዑላን ይልቅ እኛ ነዳያን እንወድሻለን፡፡
አንቺ የተቸገሩ መነሻ ነሽና፡፡
☞እመቤታችን ሆይ ከፍሡሓን ይልቅ እኛ ኅዙናን እንወድሻለን የተከዙት ደስ
የምታሰኚ ነሽና፡፡
☞እመቤታችን ሆይ ከክቡራኑም ይልቅ እኛ የተናቅን እንወድሻለን አንቺ ለተናቁ
ሞገሳቸው ነሽና፡፡
☞እመቤታችን ድንግል ማርያም ሆይ ዓለም የሚጠላን እኛ ክርስቲያን
እንወድሻላን አንቺ የተጠሉትንና የተናቁትን የምትወጂ ነሽና፡፡
☞እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ንጹሓን የአይደለን እኛ ኃጢአትን
የፈጸምን በደለኞች ልጆችሽ እንወድሻለን በኃጢአት ለተዳደፋ አንቺ
በአማላጅነትሽ የሚነጹ ብሽ ነሽና፡፡
☞ጠቢባን የእይደለን ሰነፎች እኛ እንወድሻለን የሰነፎች ጥበባቸው አንቺ ነሽና፡፡
☞ብርቱዎች የአይደለን እና ደካሞች እንወድሻለን የደካሞች ኃይላቸው አንቺ
ነሽና፡፡
☞የአልጠገብን እኛ ርኁባን ልጆችሽ እንወድሻለን የርኁባን ጥጋብ በረከታቸው
አንቺ ነሽና፡፡
☞እመቤታችን ድንግል ማርያም በመታመን ለለመነሽ ጩኹቱን የምትሰሚ
የማዳን ደጃፋ የይቅርታ በር አንቺ ነሽ፡፡ አሁንም በአማላጅነትሽ አምነው
ለሚጠሩሽ ለሚማጸኑሽ ፈጥነሽ ድረሺ፡፡
☞(ከእመቤታችን ወዳጅ ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ድርሰት ከሆነው"ዕንዚራ
ስብሐት"ድረሰት የተወሰደው፡፡

https://youtube.com/channel/UCzj1rOCD7-WVTFN7VU8RmZw