Get Mystery Box with random crypto!

☞ ነሐሴ 16 እንኳን ለእናታችን ለእመቤታች ለቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገቷ በዓል በሰላም አደረ | ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

☞ ነሐሴ 16 እንኳን ለእናታችን ለእመቤታች ለቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገቷ በዓል
በሰላም አደረሳችሁ፡፡
☞ሞትን የረገጠ ልጅሽ ካንቺ ጋር ነው
☞ውጦ የሚያስቀርሽ የቱ መቃብር ነው፡፡
☞የዕረገትሽን ዜና ከቶማስ ሰምተናል
☞ትንሻኤሽ እውነት ነው ሰበዝንሽ አይተናል
☞ሞትማ በሞት ተሸንፍል
☞በአንቺ ላይ እንዴት ሀይል ያገኛል፡፡
☞እመቤቴ ቅድስት ድንግል ሆይ መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል
የክርስቶስ የትንሣኤው ምሳሌ ለሆነ የሥጋሽ ትንሣኤ ሰላምታ ይገባል፡፡
☞እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ሕያው የሆነ ባሕርዩን በውስጧ
ሠውሮ ከሞት ለተነሣባት የክርስቶስ ትንሤኤ መንትያ ለሆነች ትንሣኤ ሥጋሽ
ሰላምታ ይገባል፡፡
☞እመብቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ አንቺን ለሚያመሰግኑ ቅዱሳን ሰዎች
ሁሉ የዕርገታቸው ምሳሌ ለሆነ ዕርገተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ እመቤቴ
ማርያም ሆይ የካህናት አለቃ የተባለ የአሮን የሽቱ ጌጥ አንቺ ነሽ በአንደበታችን
የሚነገረው የምስጋናሽ ፍሬ ሁሉ በውስጥ በውጭ ባለው ልብስሽ ላይ በሥዕል
መልክ ተቀርጾ ይኑር፡፡
☞እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ እግዚአብሔር ለተዋሐዳትና ሥነ
ሥርዓቷን ለተካፈላት ፍልሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡
☞እመቤቴ ማርያም ሆይ በፍለስትሽ ጊዜ በምድረ ይሁዳና በኢየሩሳሌም
አደባባይ የተርሴስና የደስያት ነገሥታት ስለ ክብርሽ መዓዛቸው የጣፈጠ ልዩ ልዩ
እጅ መንሻዎችን አቀረቡልሽ ሰገዱልሽም፡፡
☞እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ከሴሎ ነቢይ ከኤልያስ ፍልስት ይልቅ
እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ላደረገው ፍልሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡
☞እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ከዚህ በፊት የልጅሽ ሥጋ ወደ
ፈለሰበት ወደ አዲሱ የሕይወት ሕንፃ አዳራሽ ለተዛወረው የሥጋሽ ፍልሰት
ሰላምታ ይገባል፡፡
☞እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ጥበበኛዋና ሐናፂዋ በሆነ
በእግዚአብሔር ፈቃድ ወደ አማረው ተድላ ደስታ ወደ አለበት ለፈለሰው ፍልሰተ
ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ እጅግ መሪር ከሆነ ከሞት አገዛዝ እኔን ልጅሽን ነፃ
አውጭኝ የሰማይ የምድር ንግሥት ማርያም ሆይ አንቺ ከፈቀድሽ ኃጥኡን ጻድቅ
ማድረግ ይቻልሻልና፡፡
☞እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ሕያዊት ከሆነች ነፍስሽ ጋር በፍጹም
ተዋህዶ ለተከናወነው ፍለሰተ ሥጋሽ ፈጽሞ ሰላምታ ይገባል፡፡
☞እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ፈጽሞ ኅዘንና ትካዜን ወደ ማያስቡበት
ደስታ ወደ አለበት ለተጓዘው ፍለሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡
☞እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በምስራቃዊ ተክለ ገነት መካከል
የብርሃን ድንኳኖች ወደ ተተከሉባት ለዐረገ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ ድንግል
ማርያም ሆይ በሁሉ አንደበት መመስገን የተገባሽ ሰለሆነ በሰማይ ካሉ
መላእክትና በምድርም ከሚኖሩ ደቂቀ አዳም ሁል ጊዜ ምስጋና ሊቀርብልሽ
ይገባል፡፡
☞እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ከፀሐይ ከጨረቃ ስነ ጸዳል ይልቅ
ፈጽሞ ለሚያበራው ፍጹም ምስጋና ለተገባው ፍልሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባሻል፡፡
☞ድንግል ማርያም ሆይ ቀናንም የተባለ ሽቱ ነሽ የልዩ ሽቱ ዐይነትም መገኛነሽና
ስለዚህም ብርሃንን ለብሰው የብርሃን ነጸብራቅ ተገናጽፈው የፍልስትሽን በዓል
መላእክት ያከብራሉ፡፡
☞እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ የጌታ ወዳጅ ከሆነ ያዕቆብ ፍልሰት
ይልቅ ይክብርና ምስጋና ለተሰጠው ፍለሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡
☞እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ክብሩ ለማይጠፋ ባለሟልነቱ
ለማይጎድል የሰዎችን ልብ ደስ ለሚያሰኝ ፍልሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡
☞እመቤቴ ማርያም ሆይ የእግዚአብሔር የምስጋናው አዳራሽ ስለሆንሽ
በፍልስትሽ ጊዜ አንቺ የተቀበሉ መላእክት ሁሉ ማርያምስ በሰማይና በምድረ
የከበረች ነች ተባባሉ፡፡
☞እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ለተመረጡት ለአዳምና ለሄዋን ልጆች
እናት ትሆናቸው ዘንድ ምጡቅ በሆነ በብርሃን ሠረገላ በክብር ተቀምጦ ለዓረገ
ፍልሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡
☞እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በሥጋዊና በደማዊ አንደበት ሁሉ
ለአንቺ ምስጋና ይገባል፡፡ በመላእክት አንደበት ለአንቺ ምስጋና ይገባል፡፡ እመቤቴ
ማርያም ሆይ የደብተራ ኦሪት ቃል ኪዳን የተጻፈብሽ የሕግ ታቦት ለአንቺ ምስጋና
ይገባል፡፡ የጌታ ባለሟል በሆኑ ቅዱሳን ጉባኤ ፊትም ለአንቺ ምስጋና ይገባል፡፡
አሜን፡፡
☞(መልክአ ፍልሰታ ለማርያም)
☞እመቤታችን ድንግል ማርያም የእኛንም የሀጥያቶችሽ ልጆችሽ ፀሎት ወደ ላይ
አሳሪጊ፡፡
☞በዚህ ሰዓት በጭንቅ በመረረ ሀዘን ላሉ አንቺ የጭንቅ ደራሽ ነሽ እና አለሁ
በያቸው፡፡
☞በቃና ዘገሊላ ውሃውን ወደ፡ወይን እንዲለውጥ ልጅሽን እንዳሰሰብሽ ጎዳቸው
ቦዶ ሆኖ የሚላስ የሚቀመስ ላጡ ጉታቸው እና ጉተራቸው በበረከት እንዲሞላ
አሳስቢልን፡፡
https://youtube.com/channel/UCzj1rOCD7-WVTFN7VU8RmZw