Get Mystery Box with random crypto!

☞ሰኔ 21 አምላክን የወለደች በውስጥ በአፍአ ንጽሐት የምትሆን የብርሃን እናቱ እመቤታችን እግዚእት | ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

☞ሰኔ 21 አምላክን የወለደች በውስጥ በአፍአ ንጽሐት የምትሆን የብርሃን እናቱ
እመቤታችን እግዚእትነ ማርያም በሰኔ 21 በጎለጎታ ይኸውም የጌታችን
የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መካነ መቃብር በሚሆን የጸለየችበት ዓመቲዊ
በዓሏ ነው፡፡
☞በዚች በሰኔ 21 ቀን የጸለየችው ጸሎት ይህ ነው፡፡
☞---አቤቱ እኔ እናትህና ገረድህ የምሆን በማኅፀኔ 9 ወር ከ 5 ቀን
ተሸክሜሃለሁ ጡቶቼንም 4 ዓመት እየጠባህ አድገሃልና እለምንሃለሁ፡፡
☞ሄሮድስ በምቀኝነት ሊገድልህ በፈለገ ጊዜ አንተን በጀርባዬ አዠዬ 4 አመት
ከአንድ ሀገር ወደ ሀገር ተሰድጃለሁ አቤቱ ጌታዬና አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ
ሆይ ጸሎቴንና ልመናዬን ሰማኝ፡፡
☞አቤቱ ማኅፀኔን ዓለም አድርገህ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን የተሸከምኩህን
አቤቱ በቁርና በብርድ ወራት በቤተልሔም ከኔ መውለድህ አሰብ፡፡
☞አቤቱ ከአንተ ጋር ሀገር ለሀገር መሰደዴን የደረሰብኝን ጭንቅና መከራን
ረሀብና ጥም አሰብ የምለምንህም ለደጋጎቼ ለጻድቃን ብቻ አይደለም በዚህ
ዓለም ሣሉ ስሜን ለሚጠሩ መታሰቢያዬን ለሚያደርጉ በማልጅነቴ ለሚተማመኑ
ኃጥአንም ነው እንጂ አቤቱ ጸሎቴንና አሰተውል ከአንተ ዘንድ የምሻውን የቃሌን
ልመና ትሰማኝ ዘንድ የልቡናዬንም ሃሳብ ትፈጽምልኝ ዘንድ፡፡
☞ልጄ ወዳጄ ሆይ አራቴ ዓመት ወተታቸውን እጠባህ(እየተመገብህ)ባሰደጉህ
ሁለት ጡቶቼ ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
☞ልጄ ወዳጄ ሆይ ከርጉም ሄሮዶስ ፊት ሸሽትን ወደ ግብፅ አካባቢ እስክንደርስ
ድረስ በደረሰብኝ ረኃብና ጥም ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡
☞ልጄ ወዳጄ ሆይ ምንም ሊቀርብህ የማይችል አንተን በሳሙ ከንፈሮቼ ኪዳነ
ትገባልኝ ዘንድ አለምንሃለሁ፡፡
☞ልጄ ወዳጄ ሆይ በተቸነኩሩት እጆችህና እግሮችህ በቅዱስ ሥጋህና በክቡር
ደምህ ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ አማልድሃለሁ፡፡
☞ልጄ ወዳጄ ሆይ ለሰው ልጅ ስትል በተቀበልከው መከራ ሞትህ ቃል ኪዳን
ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
☞ልጄ ወዳጄ ሆይ ሦስት ሌሊት ሦስት መዓልት በከርሠ መቃብር ባደርክበት
ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ አማልድሃለሁ፡፡
☞ልጄ ወዳጄ ሆይ ሳላዶር አላዶር ዳናት አዴራ ሮዳስ በተባሉ በአምስቱ ቅንዋተ
መስቀል ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
☞---አቤቱቱ አቤቱ ጸሎቴንና ልመናየን ሰማኝ የአንደበቴን ቃል አድምጥ የምንግርህን ሁሉ መታሰቢያን ሰለሚያደርጉ በስሜም ቤተ ክርስቲያን ስለሚሠሩ አንተ የብርሃን ማኅደር አዘጋጅላቸው፡፡
☞አቤቱ ስለኔ የታረዘውን ያለበሰ በሰው እጅ ያልተሠራ ዕፅብ ድንቅ የሆነውን የማይጠፋውን የማያረጀውን ዕውነተኛውን ልብስ አልብሰው፡፡
]አቤቱ ስለኔ ስም በሽተኞችን የጎበኘ(የጠየቀ) በቸርነትህ በይቅርታው ጎብኘው፡፡
]አቤቱ ስለስሜም ብሎ ለተራበ ያበላውን የሕይወት እንጀራ አብለው ሰማያዊ በሆነ ማዕድህ አስቀምጠው ለተጠማ ያጠጣውን በኤዶም ገነት ከሚፈሰው የሕይወት ውሃ አጠጣው፡፡
☞---ጌታችንም ይሁን እንደወደድሽ ይደረግልሽ አላት በአንቺ ስም ቤተክርስቲያን ያሳነፀውን የብርሃን ቦታ አዘጋጅለታለሁ፡፡ በመንግስተ ሰማያትም ንጽሕ ማደሪያን አስጠዋለሁ፡፡
☞የታመመውንም በስምሽ የጎበኘ ታሞ በአልጋ ላይ በተኛ ጊዜ እጎበኘዋለሁ፡፡ ከዚህ ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም በሞት በተለየ መሪር የሆነ የሞት ጽዋን አላጠጣውም፡፡ ወደመንግሥተ ሰማያት እስኪገባ ድረስ አልለየውም ርኩሳን መናፍስትም በተከራከሩት ግዜ እኔ ጠበቃ እሆነዋለሁ፡፡ በችግሩም ጊዜ ረዳት እሆነዋለሁ፡፡
☞ዳግመኛም በስምሽ ለታረዘ(ለተራቆተ) ያለሰውን በሰው እጅ ያልተፈተለና ያልተሠራ ኅብሩ ዕፁብ ድንቅ የሆነ የሕይወት ልብስ አለብሰዋለሁ፡፡
☞ሰለ አንቺ ብሎ ከዕለት ጉርሱ ለተራበ ያበላ ምድራዊ ያይደለ ሰማያዊ የሆነ የሕይወት እንጀራ አበላዋለሁ፡፡ ለተጠማ ያጠጣ ከመዓር ከስኳር የሚጣፍጥ ከወተት እጅግ ነጭ የሆነ ከኤዶም ገነት ከሚፈሰው የሕይወት ውኃ አጠጣዋለሁ፡፡
☞በስምሽ ያዘነውን ያረጋጋ ኅዘንና ችግር በደረሰበት ጊዜ እኔ አረጋጋዋለሁ፡፡
☞(የሰኔ ጎለጎታ)
☞ስለ እናት ስለ እናታችን ስለገባህላት ቃልኪዳን ብለህ ማረን ይቅር በለን፡፡
☞የእመቤታችን የቃልኪዳኗ ተካፋይ ያድርገን፡፡
☞በዚች በሰኔ 21 የሰኔ ጎለጎልታን ጸልየን በረከት እና የድንግል ማርያምን አማላጅነት የልጇን ቸርነት ለማግኘት ያብቃን፡፡
☞20-10-2014