Get Mystery Box with random crypto!

#ጥቆማ የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከGIZ-QEP ጋር በመተባበር ከ2011 ጀምሮ በአጭር የ | WALLPAPERS ET Daily

#ጥቆማ

የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከGIZ-QEP ጋር በመተባበር ከ2011 ጀምሮ በአጭር የስልጠና መርሀ ግብር የተግባር እና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና በማሰልጠን ላይ ይገኛል።

በ2014 ዓ.ም የስልጠና ዘመንም የ6ኛ ዙር የስልጠና ፕሮግራም ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ዝግጅት መጨረሱን አስታውቋል።

በዚህም ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የሙያ ዘርፎች የመመዝገቢያ መስፈርቶችን የምታሟሉ ሰልጣኞች እንድትመዘገቡ ጥሪ አቅርቧል።

የሙያ ዘርፎች፦

1. Automotive (አውቶሞቲቭ)
2. Food Preparation and Bakery(ምግብ ዝግጅት እና ዳቦ እና ኬክ ስራ)
3. Electrical installation and Sanitary የኤሌክትሪክ እና ሳኒተሪ መስመር ዝርጋታ)
4. Garment (ልብስ ስፌት)
5. Leather Products(የቆዳ ስራ)

ስልጠናው ከመስከረም 05 እስከ የካቲት 30 2015 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን ተመዝጋቢዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት (ነሐሴ 9/2014) ባሉ ተከታታይ 6 የስራ ቀናት ውስጥ በኮሌጁ ሬጅስትራር ፅ/ቤት በአካል በመገኘት መመዝገብ ይጠበቅባቸዋል።

ኮሌጁ ያለው ቦታ ውስን በመሆኑ የተመዝጋቢ ቁጥሩን አይቶ የመግቢያ ፈተና ካለ እንደየአስፈላጊነቱ በውስጥ ማስታወቂያ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

* ተጨማሪ መረጃ ከላይ ከተያያዘው ማስታወቂያ ማግኘት ይችላሉ።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot