Get Mystery Box with random crypto!

በመዲናችን የሚገኘው አስገራሚው ባስ (በክረምት መንገዶች በጎርፍ ሲሞሉ ወደ መርከብነት ይቀየራል) | የወሎ ድምፅ/Voice Of Wollo

በመዲናችን የሚገኘው አስገራሚው ባስ (በክረምት መንገዶች በጎርፍ ሲሞሉ ወደ መርከብነት ይቀየራል)

ሰሞኑን ሰው ሁሉ በ19 ሚሊዮን ብር ስለተገዛው አዲሱ ባስ ሲያወራ ለምን ሄጄበት አልሞክረውም ብዬ ዛሬ ከጀሞ 1 ወደ ሜክሲኮ ሄጄ ነበር።
...
ባስ ስቴሽኑ ጋ የደረስኩት ከጠዋቱ 12 ሰአት ሲሆን ከተደረደሩት አዲስ ባሶች ውስጥ አንዱን መርጩ ገባሁ። በር ላይ ሚኒ ስከርት የለበሰች አስተናጋጅ በፈገግታ ተቀብላኝ ጉንጬን ከሳመችኝ በኋላ ስልኳን ሰጥታኝ ወደ ውስጥ አስገብታ ወንበር አስያዘችኝ።
...
በጣም ብርድ ስለነበር ከወንበሬ አጠገብ የነበረውን Heat የሚለውን በተን ክሊክ ሳደርገው ወዲያውን ከወንበሬ ዙሪያ ጠርዝ ላይ ነጭ ጋቢ ወጥቶ ሙሉ ሰውነቴን አለበሰው። በዚህ ተገርሜ እንደምንም ከጋቢ ውስጥ እጄን አውጥቼ ፊት ለፊቴ ያለውን ስክሪን ሳበራው መኪናው ላይ ስለተገጠሙት ቴክኖሎጂዎች የሚገልፅ ፅሁፍ መጣልኝ።
...
ፅሁፍ ላይ እንዳነበብኩት ከሆነ ክረምት ክረምት መንገዶች በጎርፍ ሲሞሉ ይሄ ባስ ወዲያውን ቅርፁን ወደ ዝርግነት በመቀየር ወደ መርከብነት የሚለወጥ ሲሆን በውስጡም መለስተኛ ኳስ ሜዳ እና የባስኬት ቦል ኮርቶች እንዲሁም ለፈረስ ግልቢያ የሚሆን ሰፊ ሜዳ ይዟል።
...
ምናልባት ከቤቱ ተቻኮሎ ፊቱን ሳይታጠብ የመጣ ተሳፋሪ ካለ ባሱ የራሱን የፊት ሳሙና እና የጥርስ ብሩሽ ከኮልጌት ጋር እንዲሁም ከማይመለስ አንድ ፎጣ ጋር የሚያቀርብ ሲሆን ስቲም እና ሳውናም ከሾፌሩ ጀርባ ባለው ክፍል ውስጥ ዝግጁ ሆኖ ተሳፋሪዎቹን ይጠብቃል።
...
በተጨማሪም መንገድ በሚዘጋበት ጊዜ ከጎን እና ከጎን ክንፎቹን በመዘርጋት ልክ እንደ ዴር 33 ከራዳር እይታ ውጪ መብረር የሚችል ሲሆን ምናልባት በሰማይ ላይ እያለ የሰማይ ትራፊክ መጨናነቅ ቢያጋጥመው እንኳን ከስሩ እሳት በመፍጠር ራሱን ወደ መንኮራኩነት በመቀየር ወደ ጨረቃ የሚያምዘገዝግ የሮኬት ቴክኖሎጂ ተገጥሞለታል።
...
ለባለስልጣኖች ራሱን የቻለ መኝታ ቤት ያለው ሲሆን ለሰፊው ህዝብ ደግሞ ትኬት ሳይቆርጥ የገባን ቆርጦ ከገባው የሚለይ ሴንሰር ተገጥሞለታል። የሚገርመው ትኬት ያልቆረጡትን ሰዎች በስም መለየት የሚችል ሲሆን አንዱ ተሳፋሪ ሳይቆርጥ ገብቶ ወዲያኑ "ደጀኔ እባክህ ወይ ቁረጥ ወይ ውረድ አትሞላፈጥ" በሚል ድምፅ ተሳፋሪውን ሲያስጠነቅቅ በጆሮዬ ሰምቻለሁ።
...
በመጨረሻም ሜክሲኮ ባስ ስቴሽን ደርሰን ስንወርድ ለሁላችንም የጫማ ማስጠረጊያ እና ለቀጣይ ታክሲ መሄጃ ስልሳ ስልሳ ብር የተሰጠን ሲሆን ሾፌሩን ጨምሮ ሁሉም የባሱ ሰራተኞች በእግራቸው የተወሰነ መንገድ ሸኝተውናል። በእኔ እይታ ይሄ ባስ 19 ሚሊየን ሲያንስበት እንጂ ከዚህም በላይ ይገባዋል። Thank you አዴክስ ጭሷ!

በዳጊ ተፃፈ

☞ የወሎ ድምፅ Voice Of Wollo
https://t.me/VoiceOfWollo