Get Mystery Box with random crypto!

ከጠቅላይ ቤተክህነት የተሰጠ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት | VOA

ከጠቅላይ ቤተክህነት የተሰጠ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ለሕክምና ወደ ሰሜን አሜሪካ እንደሚሄዱ መገለፁን ተከትሎ ትናንት ምሽት ቅዱስነታቸው የአሜሪካ ጉዟቸውን መጀመራቸው ተገልጿል።

ቅዱስነታቸው ለሕክምና የሚሄዱ ቢሆንም በአዲስ አበባ ኤርፖርት በተገኙበት ወቅት ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት እና ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት ተፈቅደው በአድራሻ ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት የተጻፈ ሕጋዊ ደብዳቤ እንደሚያመለክተው

ቅዱስ ፓትርያርኩ ለአገልግሎት ይዘዋቸው የሚጓዙት ንዋያተ ቅድሳት

— ሁለት ጽላቶችን ፣
— 3 የወርቅ የእጅ መስቀሎችን (የግል ንብረታቸውንና ስማቸው የተፃፈባቸውን) ፣
— 5 አዲስ እትም የግእዝ መጽሐፍ ቅዱስ እና
— አንድ ሊትር ቅብዓ ሜሮን

መሆናቸውን ለቦሌ ኤርፖርት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተጻፈ ደብዳቤ ያሳያል።

ትክክለኛ ገፃችንን ይቀላቀሉ
............. .............
@VoiceofAmerica_VOA