Get Mystery Box with random crypto!

, #ሰይጣናዊ_ፍቅር!! እጅግ ያበላሽ የብዙ ሰው ህይዎት ሰይጣናዊ ፍቅር ኒ | ➪የሰለፍያ እንስቶች ቻናል🌺

, #ሰይጣናዊ_ፍቅር!!


እጅግ ያበላሽ የብዙ ሰው ህይዎት
ሰይጣናዊ ፍቅር ኒካህ የሌለበት
ታስቦበት ሳይሆን ጅምር ሲመሰረት
ለትዳር አይደለ ሂዎትን ለመምራት
ሌሎቹ ሲያደርጎቱ ኮርጆ በፍጥነት
ፊልም በመመልከት ሙዚቃ በመስማት
እቅዱ አውጥቶ በነዚህ መሰረት
''ሀ'' ብሎ ጅማሮ ይቀጥላል እብደት
እርሷ ላታገኘው እርሱም ላያገባት
መብሰልሰል መዳረቅ አቅፎ ባዶ ምኞት
አደጋ በሽታ ለክፎት ትምህርት ቤት
ቆይቶ እያተላ ውስጡን በመሰርጀት
ከልጅነት ይዞ አይለቅ እስከ ማርጀት
ትዳርም አይጥመው ቢያገባ ምናልባት
<:-------:------:--------:--------:-------:>
እውነትም ጅኒአዊይ ሰይጣናዊ ተንኮል
አፍቃሪ ተብየው አያገኝ አንድ ውል
ወንዱን ስትመርጥ ሴቷም አታስተውል
መስፈርታቸው ሲታይ ከልብ ያሳዝናል
/
ሲሬስ ኩራተኛ ሲሆን ባለ ጉራ
ሀሳብ ጭንቀት የለሽ ዝጋታም ቀብራራ
ቃሚ አጫሽ የሆነ የማይባል ፋራ
ጠጥቶ ሚሰክር የሚያውቅ ጭፈራ
ቁም ነገር የማይወድ ከቀልድ ከፉገራ
ሱሪውን ጎታቺ ፀጉሩ ተቁጠርጣሪ ሲበዛም ጨብራራ
ይሄን አይነቱን ወንድ የሆነ አባሙራ
ወደድኩት ትላለች ይሄን ሰው አፍቅራ
<:--------:------:--------:--------:-------:>
ወንዱ ሲል ይሰማል ጭራሽ በርሱ ብሶ
በጫማ ተመቶ ደርዘን ስድብ ቀምሶ
የተገላቢጦሽ ፍቅር በርሱ ደርሶ
ቦታ የማትሰጠው የሆንች ኮስኳሶ
ቡል ሲል ይኖራል እንደ ደረቅ በሶ
/
ሁኔታዋ አማሎት ስቦት ልቅነቷ
ቁጣ ግልማጤ ጣጣ ቢስነቷ
ሲቃጠል ይኖራል ለዚህ ማንነቷ
<:-------:-------:--------:--------:-------:>
ሳያገኛት ሲቀር ሌላ ስታገባ
ያኔ እሱ አለቀለት አብዶ ጫካ ገባ
ሚስት ሚባል ትቶ ሰይጣንን አገባ
በየ በረንዳው ላይ ወደቀ እንዳይረባ
ትዳር ሳይመሰርት ይሞላዋል አርባ
ትላንት የገጠመኝ ሆድን የሚያባባ
አርባ አምስት አመቱ ሚስት ሳያገባ
አይምሮው ተዛቦቶ ግራ እየተጋባ
ይሄው ዛሬ ድረስ አለ አድስ አበባ
መንሰኤ ስጠይቅ ምክንያት ሳስተጋባ
ፍቅር የሚሉት ጉድ ሰይጣናዊ ጎርባ
አሳብዶት ቀረቶ ገደል ይዞት ገባ
<:-------:-------:---------:--------:-------:>
አብሮ መተሳሰብ የሌለበት ዋይታ
አንዱ ሲያብድ ሲውል ሌላው ሳይሰጥ ደንታ
ዘመን ይሻገራል ነዶ በጧት ማታ
ህልም ሩጫ ሆነ በምኞት እርካታ
የሚታይ ተጨባጭ ሳይገኘው ደስታ
ህይዎት ስትቀየር የሁሉ እጣ ፈንታ
ዘመን ያስቆጥራ ሀሌ ሲንገላታ
<:-------:--------:---------:--------:-------:>
ሰፈሩን ሰፈሯን ሳይቀር ካፈቀሩ
ሞላ አካባቢውን ጠቅላላ መንደሩ
ከእንሰሳ ጀምሮ ከድንጋይ ካፈሩ
ከልባቸው ወደው ነገር ካመረሩ
እውነተኛ ፍቅር እንዲህ ነው ሚስጥሩ?
እብደትና ምኞት በአንድ ላይ ካደሩ
የሰይጣኖች ሴራ ካልሆነ ችግሩ
ይሄ ፍርቅር ነው ወይ እስኪ ተናገሩ
በሙዚቃኮ ነው የጠፋው ሀገሩ
የሚናገሩትን እነሱ የማይሰሩ
በሀሳብ ላይ ዘምተው ህልመኛ እያዎሩ
ብዙውን ገደሉት አይኑን አሳዎሩ
/
ቆም ብሎ ሳያስብ ለውሳኔ በቃ
ወደ ፍቅር ብሎ ገጠመው አሮንቃ

አብዱረህማን ዑመር
https://t.me/Abdurhman_oumer/2743