Get Mystery Box with random crypto!

ፀደይ ባንክ Tsedey Bank S.C.

የቴሌግራም ቻናል አርማ tsedey_bank_office — ፀደይ ባንክ Tsedey Bank S.C.
የቴሌግራም ቻናል አርማ tsedey_bank_office — ፀደይ ባንክ Tsedey Bank S.C.
የሰርጥ አድራሻ: @tsedey_bank_office
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.72K
የሰርጥ መግለጫ

ፀደይ ባንክ (ACSI አብቁተ)🇪🇹 (Channel)
https://t.me/tsedey_bank_of
ፀደይ ባንክ (ACSI አብቁተ)🇪🇹(Group)
https://t.me/tsedeybank12
ፀደይ ባንክ (ACSI አብቁተ)🇪🇹 (Bot)
@backtube_bot
ፀደይ ባንክ (ACSI አብቁተ)🇪🇹(Page)
https://www.facebook.c

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-30 16:22:19 በመጨረሻ እንደ ፀደይ ባንክና እንደ ፀደይ ቤተሰብ ሁላችንም የሚጠበቅብንን በመፈጸም የባንኩን ጅማሮ ለማብሰር መዘጋጀት ይኖርብናል፡፡ ሁሉም ፍላጎቶቻችን ወቅቱን ጠብቀው መፈጸማቸው አይቀሬ ሆኖ ሳላ በትንሹም ሆነ በትልቁ በውዥንብር እየተዘባን ከምህዋራችን ወይም ከሃዲዱ መውጣት የለብንም፡፡ አንዴ ከሃዲዱ ከወጣን ለመመለስ በእጅጉ አስቸጋሪ ነው፡፡ ከጀንዋሪ ጀምሮ ባደረግነው ጥረት ቁስላችንን ለማከም ጥረት አድርገናል፡፡ ምንም እንኳ ህክምናው ቁስሉ መልሶ በማያመረቅዝበት ሁኔታ ላይ ባያደርሰውም፤ አሁን ደግሞ በመዘናጋትና በሥራችን ላይ ያለንን ትኩረት አላግባብ በመቀነሳችን ችግሩ እንዲያገረሽ እድል ፈጥረናል፡፡ የሚያገረሽ በሽታ ከዋናው ህመም በላይ በህክምና የመዳን እድሉ በጣም ዝቅተኛ ስለሆነ ጊዜ ሳንሰጥ በፍጥነት ለማዳን መረባረብ ይገባላናል፡፡

የፀደይ ባንክ ጅማሮ በታታሪና ውጤታማ ሰራተኞቻችን ይረጋግጣል!!
4.4K viewsB G, 13:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 16:21:21 ለፀደይ ባንክ ዲስትሪክት ማኔጀሮችና የቅ/ጽ/ት ቤት ሥራ አስኪሃጆች ሰላም እንዲሆንላችሁ ምኞታችን ትልቅ ነው!!!

ይህ ሳምንት በአዲሱ በጀት አመት 3ኛው ሳምንት ሲሆን እቅድ ፀድቆ ወይም በታሳቢ ግብ ተይዞ በተሟላ አቅም ወደ አፈጻጸም የምንገባበት ጊዜ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ሆኖም በአመቱ ተጨማሪ ተልዕኮዎችን ወስደን ወደ ባንክ ትራንስፎርሜሽን ሥራ ስለገባን ተግባራችን በጣም ብዙ እና የተወሳሰበም ሆኗል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ የባንኩ የአምስት አመት ስትራቴጂክ እና አመታዊ ግቡ በዚህ ወር መጨረሻ በባንኩ አመራር ቦርድ ፀድቆ ለባንኩ ሰራተኞች የኦረንቴሽን ፕሮግራሙ በሚቀጥለው ወር ሶስተኛ ሳምንት ላይ በየአደረጃጀቱ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡ ይህን ለማድረግ ግን አስቀድመው መፈፀም የሚኖርባቸው ወሳኝ የሚባሉ ተግባራት ይኖራሉ፡፡ ከነዚህ ተግባራት ውስጥ በመጀመሪያው ዙር ፈጥነው የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡትን የባንክ ቅ/ጽ/ቤቶች ስታንዳርድ ከነውስጥ የአገልገሎት ቁሳቁሳቸው ጨምሮ እንዲያሟሉ በማስቻል፣ የሰው ሃይል የምደባ ሥራ በማጠናቀቅ፣ ሥልጠና በመስጠት፣ የባንኩን አሰራር ሥርአት በመዘርጋት (ኮር ባንኪንግ ሲስተም ማሻሻል፣ ሌሎች አስፈላጊና ጠቃሚ የቢዝነስ ቻናሎችን በመግዛት ወይም በማበልፀግ፣ ፖሊሲ፣ ፕሮሲጀርና ማኑዋል አዘጋጅቶ በሚመለከታቸው በማፀደቅ… በብሔራዊ መረማሪ ቡድን አሳይቶ ተቀባይነት እንዲያገኝ በማድረግ ሥራ መጀመር ያስፈልጋል..) እና በብሔራዊ ባንክ የኢንቨስትጌሽን ምርመራ እንዲካሄድ በማደረግ ሥራ ማስጀመርን ግምት ውስጥ ያስገባል፡፡ ሆኖም ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ እስከ በጀት አመቱ መጨረሻ መልካም የነበረው የተቋሙ አፈጻጸም የ2021 በጀት አመት እንደተገባደደ በከፍተኛ ደረጃ ማሽቆልቀል ጀምሯል፡፡ ይህ በፍጥነት እና በአጥገቢ ሁኔታ ካልተቀለበሰ አደጋው እጅግ አሳሳቢ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ወሳኙን ሚና የሚጫወቱት የዲስትሪክቱ ማኔጀሮችና የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሥራ አስኪሃጆች ይሆናሉ፡፡ በዚህ ጉዳይ ምንም ምክንያት መስጠት ጠቀሜታ የለውም፡፡ ለምሳሌ ሌላ የምደባ ሥራ ስለያዝኩ ነው፤በምደባው ቅር ስላለን ሥራውንም ማስታወል አልቻልንም፤ የምደባዬን ቦታና ደረጃ አላወቅሁም፤ …የመሳሰሉት ብዙም ውሃ የሚያነሱ አይደሉም፡፡ ሁሉም አልቆ ችግሮችም ተፈተው ወደ ሥራ ስንገባ ቁጭት ቢሰማን እንኳ በጣም ስለሚረፍድ ምንም ትርጉም የለውም፡፡ በመሆኑም መፍትሔውን ማሰብና ችግሩን መቀልበስ ሰይውሉ ሳያድሩ አሁኑኑ የሚያስፈልግ ይሆናል፡፡

ይህ በመሰረቱ የሳምንታቱ አፈጻጸም በእጅጉ የሚያሳስበን የባንክ ሥራችንን በተሟላ መንገድ ተጠናክረን ከመጀመራችን ጋር የሚያያዝ በመሆኑ ነው፡፡ ቀደም ሲል እንደ አብቁተ የነበረን አስተሳሰብ ስለትርፍና ትርፋማነት፣ ስለቁጠባና ብድርን በቁጠባ የመሸፈን አቅም፣ ሰለብድር ጥራትና NPL% እና ብቃት (efficiency) ያለን ግንዛቤ በጣም አናሳ ከመሆኑ የተነሳ እንደመለኪያና መወዳደሪያ አጥብቆ በመያዝና በመጠቀም ዙሪያ ክፍተት ይታያል፡፡ በዚህም ለአመታት አትራፊ ሳይሆኑ በርካታ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የተቋሙ አካል ሆነው እንዲኖሩ እድል ፈጥረናል፡፡ የሆኖ ሆኖ ይህ እንደ ፀደይ ባንክ ፍፁም የማይሰራና ተቀባይነት የሌለው ነው፡፡ ዛሬ በእጃችን ያሉ 160 ኪሳራ ያስመዘገቡ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የተወሰኑ ወራት ግብ (አንድ ሩብ አመት) ተቀምጦላቸው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከኪሳራ እንዲላቀቁ ይደረጋል፡፡ ሌሎች ጤነኛ ቅርንጫፍ ቅ/ጽ/ቤቶችም ኪሳራ የማስመዝገብ እጣ ፈንታቸው ዝግ ይሆናል፡፡ በሌሎቹም መለኪያዎቻችን /በNPL%፣ ብድርን በቁጠባ የመሸፈን፣…/ እንደድሮው የምናጠባጥበው ወይም እየሰረዝን እየደለዝን የምናስተካክለው ምንም አይነት አሰራርና መመሪያ አይኖርም፡፡ ሲጠቃለል እንደ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የባንኩ አካል ሆኖ እኔ ከነዚህ መለኪያ አኳያ የት ላይ ነኝ ብሎ መጠየቅ፣ ማስላትና ደረጃን አውቆ ጉድለት ከተፈጠረ በፍጥነት ማስተካከል የእለት ተዕለት ሥራችን ይሆናል፡፡

አሁን ባለንበት የአፈጻጸም ደረጀ ከ160 ያላነሱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ኪሳራ ያሰመዘገቡ ከመሆናቸውም በላይ በትርፋማነታችን ላይ ያሳደሩት አሉታዊ ተፅዕኖ ላቅ ያለ ነው፡፡ እነዚህ ጽ/ቤቶች አመቱን በbreak-even እንኳ ቢያጠናቅቁ ኖሮ በትርፋችን ላይ ከብር 500 ሚሊዮን ያላነሰ ተጨማሪ ገቢ ማግኘት ይቻል ነበር፤ ይህ ግን ሊሆን አልቻለም፡፡ እንደ ባንክ ትርፍ አለማስመዝገብ ለሰራተኛው የሚያጓድለው የደመወዝ ጭማሪ፣ የቦነስ ክፍያ፣ እድገት እና የመሳሰሉትን ብቻ ሳይሆን በእጁ የያዘውን የሥራ እድል ጭምር ነው፡፡ ሌላው አሁን ያለን ብድርን በቁጠባ የመሸፈን አቅም ወደ 97% እያሽቆለቆለ ነው፡፡ ይህንን ባጠረ ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ወደ ባንኩ ስታንዳርደ ማምጣት ይጠበቅብናል፡፡ የብድር ጥራትና NPL%ን በተመለከተ በጁን 30/2022 በፀደይ ደረጃ 7.22% ሲሆን ይህም ከዝቅተኛው የጥራት ምጣኔ አኳያ ሲመዘን እጅግ በጣም ትልቅ ነው፡፡ በዚህ አፈጻጸም ውስጥ አራቱ ዲስትሪክቶች (ፍኖተ ሰላም- 0.78%፣ ደብረማርቆስ- 2%፣ እንጂባራ- 2.86% እና ደብረብርሃን- 2.65%) ከቅርንጫፍ ጽ/ቤት- ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሚኖረው ልዩነት እንደተጠበቀ ሆኖ በዲስትሪክት ደረጃ መስፈርቱን አሟልተዋል፡፡ የቀሩት ዲስትሪክቶች በሙሉ ችግር ላይ ቢሆኑም ጎንደር፣ ደሴ (ከምሴን ጨምሮ) ገንደዉሃ እና ሰቆጣ እጀግ ከፍተኛ የሆነ ትኩረት የሚፈልጉ ናቸው፡፡ ደብረታቦርና ወልዲያም ቢሆኑ በቀሩት ባጠረ ጊዜ ውስጥ ተንቀሳቅሰው ከነ ፍኖተ ሰላም ጎራ መቀላቀል የግድ ይላቸዋል፡፡ ጠቅለል ብሎ ሲታይ የባንኩ ጅማሮ በሁላችን የፀደይ ቤተሰብ አባላት ላይ የወደቀ ሃላፊነት በመሆኑ ከጽ/ቤት ስታንዳርድ ማሟላት፣ ፖሊሲ ፕሮሲጀር ማኑዋል አጠናቆ ከማፀደቅ፣ መዋቅሩን ከደመወዝ ስኬል ጋር ወደ ሥራ የማስገባት፣ ሥለጠና አካሂዶ ማጠናቀቅ ጋር ተደምሮ ሁሉም በተሳካ መልኩ ፍጻሜውን እንደሚያገኝ ጥርጥር የለንም፡፡

ፀደይ ባንክ እንደተቋም በአዲሱ በጀት አመት 3ኛው (2022/2023) ሳምንት ላይ በሁለቱም ሥራዎቹ አልተሳካለትም፡፡ ቁጠባ በብር 262.3 ሚሊዮን ሲቀንስ የውዝፍ ብድርም በብር 1.6 ሚሊዮን ጨምሯል፡፡ ቁጠባን አስመልክቶ ሁለት ዲስትሪክቶች (ደብረብርሃን- በብር7.7 ሚሊዮን እና ሰቆጣ- በብር4.06 ሚሊዮን) ብቻ ሲጨምሩ የቀሩት ዘጠኝ ዲስተሪክቶች (ባህርዳር- በብር111.3 ሚሊዮን፣ ፍኖተ ሰላም- በብር44.12 ሚሊዮን፣ደሴ- በብር27.22 ሚሊዮን/ከምሴን ጨምሮ/፣ጎንደር- በብር21.72 ሚሊዮን፣ እንጂባራ- በብር17.52 ሚሊዮን፣ ደብረታቦር- በብር16.21 ሚሊዮን፣ደበረማርቆስ- በብር14.9 ሚሊዮን፣ ገንደዉሃ- በብር11.81 ሚሊዮን እና ወልዲያ- በብር9.2 ሚሊዮን) ባንኩን በማይመጥንና ወቅታዊነት በሌለው መንገድ ቀንሰዋል፡፡

የውዝፍ ብድር በተመለከተም በሳምንቱ አራት ዲስትሪከቶች (ጎንደር- 1.7 ሚሊዮን፣ እንጂባራ- በብር853.6ሺ፣ ገንደዉሃ- በብር259ሺ እና ባህርዳር- 128.6ሺ) ሲቀንሱ ቀሪዎቹ ሰባቱ ዲስትሪክቶች(ደብረብርሃን- በብር 1.6 ሚሊዮን፣ ደብረታቦር- በብር1.43 ሚሊዮን፣ሰቆጣ- በብር658.8ሺ፣ደብረማርቆስ-በብር445.1ሺ፣ፍኖተሳላም- በብር281.4ሺ፣ወልዲያ- በብር60.6ሺ እና ደሴ በብር50.03ሺ) ወቅቱን በማይመጥን መልኩ ጨምረዋል፡፡
4.1K viewsB G, 13:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 20:33:42
5.2K viewsB G, 17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 20:33:36
4.9K viewsB G, 17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 20:33:24
4.4K viewsB G, 17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 09:27:20
7.5K viewsBeamlak Girmaye, 06:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 11:33:29 Follow Like comment share http://tiktok.com/@tsedeybank
9.6K viewsBeamlak Girmaye, 08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 22:36:41 በመጀመሪያ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት በተለይም የአማራ ክልልን ህዝብና መንግስት ከብድርና ቁጠባ ተቋምነት እስከ ግዙፍ የባንክ ባለቤትነት እንዲደርስ ለተደረገልን ትልቅ ትብብርና አብሮነት ምስጋናን እያቀረብን ድርጅታችን የማህበረሰባችንን የዘመናዊ የባንክ ችግርን ለመቅረፍ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የሚጠበቅበትን ሀላፊነት ለመወጣት እናም የባንኩን ምስረታ ለማህበረሰቡ በሰፊው ለማስተዋወቅ "ቤተሰባችንን ይቀላቀሉ Program "

በዚህም መሰረት የYOU TUBE Channel የቴሌግራም ቻናላችንን ለሚቀላቀሉ እና ወደ ግሩፓችን ዘመድ ወዳጆቻቸውን ለሚጋብዙ የቴሌግራም ተጠቃሚዎች የሆነ ተዘጋጅቷል።

........ T S E D A Y B A N K S C.........

ይሳተፉ

ልብ ይበሉ፦ በእድሉ ተጠቃሚ ለመሆን እነዚህን 3 መንገዶች በጥንቃቄ ይከተሉ።

1. ከታች በሚገኘው ማስፈንጠሪያ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/tsedey_bank_office
2. ከታች በሚገኘው ማስፈንጠሪያ የይቲዩብ ቻናላችንን ይቀላቀሉ።




3. በመቀጠል ይህንን መልዕክት ለ50 ሰዎች ያስተላልፉ።

4. ከዚያም በመወያያ ግሩፓችን ላይ

https://t.me/+dUlUVoLKoohlYjQ0
5. የቲክ ቶክ አካውንት Follow
tiktok.com/@tsedeybank
Tseday Bank Official
11.6K viewsBeamlak Girmaye, 19:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 18:44:15 Follow Like comment share http://tiktok.com/@tsedeybank
8.6K viewsBeamlak Girmaye, 15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ