Get Mystery Box with random crypto!

የታክስ ማሻሻያ ከተደረገ በኋላ ከ7,000 በላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ገብተዋል ተ | TradeUp

የታክስ ማሻሻያ ከተደረገ በኋላ ከ7,000 በላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ገብተዋል ተባለ።

በመስከረም ወር የገንዘብ ሚኒስቴር ካደረገው በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች የታክስ ማሻሻያ በኋላ፣ ከ7,000 በላይ ተሽከርካዎች ሀገር ውስጥ እንደገቡ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የትራንስፖርት ዘርፍ አገልግሎት ሚኒስትር ደኤታ አቶ በርኦ ሐሰን ገልጸዋል።

ሚኒስቴሩ በአስር ዓመት ዕቅዱ 48,000 የብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ የኤሌክትሪክ አውቶብሶችን፣ እንዲሁም 148,000 የኤሌክትሪክ አውቶሞቢሎችን አገር ውስጥ እንዲገቡ ማድረግ እንደሆነ ጠቁመዋል።

በዚህም በኤሌክትሪክ የሚሠሩ 1,300 የብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አውቶብሶችን ከውጭ አቅራቢዎች በዱቤ ለመግዛት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጋር መግባባት ላይ መደረሱንና በቅርቡ ወደ ሀገር ቤት እንደሚገቡ ሚኒስቴር ዴኤታው ገልጸዋል።

‹‹አውቶቡሶቹን የማስገባት ሒደትና አስመጪዎቹን የማወዳደር ኃላፊነት ለከተማው መስተዳደር ሰጥተን እንዲከታተል አድርገናል፤›› ሲሉ ሒደቱ አልቆ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቀጣይ ኃላፊነቶች እንደሚቀሩ ተናግረዋል፡፡

ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያና ለሌሎች የመሠረተ ልማት ሥራዎች የግሉ ባለሀብት ተሳትፎ ፍላጎት ከአሁኑ እየታየ እንደሆነ ገልጸው፣ ቻርጅ ማድረጊያዎችን በአዲስ አበባና በሌሎች የክልል ከተሞች ለመገንባት ፍላጎት ካሳዩት መካከል በነዳጅ ንግድ ሥራ የተሰማራው ታፍ ኦይል (TAF Oil) ኩባንያ አንደኛው እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

Source : Ethiopian Reporter, Michael Tewelde

For more click the link
https://t.me/+SjcIYocNGQSfeI3c